Skip to main content

Posts

ስርነቀል ለውጥ ማምጣት የአማራ ብሄርተኝነት የህልውና ትግል ብቸኛ ግብ ነው። በ Alen Kassahun

ምስሉ ጸሃፊውን አይወክልም፡፤ ከ50 አመታት በላይ የተተከለውንና በተግባር እየተፈፀመ ያለውን አማራን ማጥፋትና ኢትዮጵያን ማፍረስ ከስሩ በመንቀል #4ኪሎን ተቆጣጥሮ ስርነቀል ለውጥ ማምጣት የአማራ ብሄርተኝነት የህልውና ትግል ብቸኛ ግብ ነው። ፋኖ በሚያደርገው የህልውና ትግል አማራ ጠልነት የወለደውን የአማራን ዘር ማጥፋት፤ ማፅዳት፤ የሰባዊ መብት ጥሰትና አገር ማፍረስ አለምአቀፍ ወንጀል ከስሩ ነቅሎ ሊቀብረው #በዋዜማው ላይ እንገኛለን። ስለሆነም ፋኖ እያደረገ ያለውን የህልውና ትግል #በድል እንዳይቋጭ  በድርድር፣ በእርቅና በምክክር ሰበብ የፋኖን ድል ለመቀልበስና ለመንጠቅ ከአሜሪካ እስከ አዲስ አበባና መቀሌ ድረስ በሚሸረብ ሴራ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ፤ በስልታዊ አማራነትም ሆነ በአማራ ጠልነት የተሰለፉ ቅጥረኞች ደፋ ቀና እያሉ እንደሚገኙ ግልፅ ነው። ፋኖ #አራት ኪሎን በመቆጣጠር ስርነቀል ለውጥ ለማወጅ በድል ዋዜማ ላይ ሆኖ እያደረገ ያለውን የመጨረሻውን ትንቅንቅ ለማሰናከልና ድሉን ለመሸጥ ተቀጥራችሁ ስለ ድርድር፣ ሽግግር፣ እርቅ፣ ውይይትና በመሳሰሉ አጀንዳዎች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ እየሰሩ የሚገኙ ቅጥረኞችን ከቀጣሪዎች እኩል ማሸነፍና ማስወገድ የህልውና ትግላችን ብቻኛ አማራጭ መሆኑ ለማንም ግልፅ ሊሆን ይገባል። ስለሆነም የዜግነት ፓለቲካ አቀንቃኝ የ3ኛ ወገን ቅጥረኞችን ከጀርባው አሰልፎ የአማራን ብሄርተኝነት የማድፈቅ አጀንዳቸውን አዝሎ ከአማራ ህልውና ትግል መሀል የተገኘው #እስክንድር ነጋ ከአማራ ህልውና ትግል ጓዙን ጠቅልሎ እንዲወጣ ማድረግ ለነገ የሚባል አይደለም። የእስክንድር ነጋ #የእየሱስ ክርስቶስነት ገፀ ባህሪ በሂደት እየተገፈፈ መምጣት አማራ ጠል ሀይሎችን ወደ እቅድ ሁለት ሴራ እንዲገቡ እያስገደደ በመሆኑ የአማራ ብሄርተኛ #እስክንድ...

በጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)

ሻለቃ ዳዊትን በተለያዩ ምክንያቶችና ወቅቶች እንደ እኔ የተቻቸው ፈልጋችሁ አታገኙም። ያ ወቅት ሌላ ፤ ዛሬ ሌላ፤- ያ ዘመን ከ2010 ዓ.ም በፊት ነው። ሰው የነበረውን መስመር አስተካክሎ ባዲስ አካሄድ ወቅቱ በሚጠይቀው ጎዳና ከተራመደ ሌላ ምን ይፈለጋል? ዛሬ ግን ሻለቃው “ኢምፖስተር” በማለት የሚጠሩት ህቡእና ግልጽ ነብሰገዳይ ቡድን አሰማርቶ ነብስን የሚቀጭና የሚሰውር <<የወያኔ የነገድ አስተዳዳር አስቀጣዩ የኦሮሙማው የጋጠወጥ ማፍያዎች መሪ>> አብይ አሕመድ ከነገሠ ወዲህ ግን “ሻለቃው” አብይ አሕመድን እንቅልፍ ካሳጡት አርበኞች አንዱ ሆነው ብቅ ብለዋል። ያንን በማድረጋቸው “ጥበብ ሳሙኤል” የተባለ የአብይ አሕመድ አለቅላቂና ፀረ አማራና የሕግ ሙያ ትምሕርተ አለበት ተብሎ የሚነገርለት (?) ጋዜጠኛ:- አብይ አሕመድን በመደገፍ በሻለቃው ላይ ያለ ዕረፍት ረዢም ጊዜ ሲዘልፋቸው ያስገረመኝ ያህል፤ ሰሞኑን ደግሞ በሻለቃ ዳዊት ወ/ልደጊዮርጊስ ላይ አዳዲስ ዘላፊዎች ብቅ ብለዋል። “ሻለቃ ሆይ! በትግሉ ውስጥ ዛሬ ይኑሩ አይኑሩ አማራውን ለመታደግ ከፍታዎትን አሳይተዋል ፤የበኩልዎን አድርገዋል ለዚህም <<በአክብሮት ባርኔጣየን አነሳለዎታለሁ፤ አንኳን ደስ አለዎት !!!!>> አርበኛ ብቅ ባለ ቁጥር ሱሪውን የሚጎትቱ ብዙ የፖለቲካ ተውሳኮች አሉ። ሻለቃው በዛው ዕደሜአቸው የሚቻላቸውን በማድረጋቸውና ከፍታቸውን በማሳየታቸው ፤ ይህን በማድረጋቸው ዓይናቸው ከቀላ ውስጥ አንዱ ወደ “ጥንት ትፋቱ” የተመለሰው፤ በቅርቡ ከወያኔም ከኦነጎችም እየተወዳደሰ መተፋፋግ የጀመረው የወያኔው አሽከር “ኤርሚያስ ለገሰ” እና ዶ/ር አምሳሉ የተባለ “ከጎንደሬዎች እጅህን አንሳ” እያለ ሲከራከረኝ የነበረው እስከ ቅርብ ጊዜ ወዲህ የአብይ አሕመድ አወዳሽ የነበ...

ሻ/ቃ ዳዊት ወ/ጊወርጊስ ስለራሳቸው የጻፉት ።ከታች ያለውን የሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዎርጊስን የግል ፅሁፍ እንመልከት ።

ሻ/ቃ ዳዊት ወ/ጊወርጊስ ስለራሳቸው የጻፉት ።  Dawit W/Giorgis የአማራ ሕዝባዊ ግንባር የውጭ ድጋፍ ሰጪ ግብረ ሀይልን እዚህ ለማድረስ ቁልፍ ሚና በመጫወቴ ደስተኝ ነኝ:: ይህንን እድል ለሰጠኝ ወደር ለሌለው ጀግና እስክንድር ነጋ ምስጋናዬን እቀርባልሁ:: ይህንን  ግዙፍ ሀላፊነት  ለመወጣት ከሚታወቀው  በላይ ያለ እረፍት ሌት  ተቀን  የሰሩትን የስራ ባልደረቦቼን እደንቃለሁ:: አመሰግናለሁ::  እኔ የስራ ሰው ነኝ:: የእወቀትም ሰው ነኝ:: ታሪካዊና ትምህርታዊ  የሆኑ አራት  መፅሀፎችም ፅፌአለሁ:: በእንግሊዝኛም በአማርኛም::አልቀረብኝም:: ቁጥራቸው በጣም ብዙ የሆኑ ምሁራዊ  ፅሁፎችን አሳትሜአለሁ::ከአውስትራሊያ አውሮፓና አሚሪካ ካናዳ የተለያዩ ሚዲያዎች ላይ  ለብዙ አመታት ቀርቤአለሁ:: ፅሁፎቼም በ CNN ሳይቀር ወጥተውልኛል::  አገልግሎቴን ግን የምመዝነው በተግባሬ ነው:: እውቀቴን  በተግባር   በማዋል የተመሰከረልኝ  ነኝ:: እውቀትና ተግባርን በማያያዝ በውትድርና ሙያ፣ በኤርትራ  አስተዳዳሪነት፣ በዲፕሎማሲ፣ በተባበሩት መንግስታትና ለተለያዪ መንግስታት በችሎታ አማካሪ ሆኜ  አገልግያለሁ::  ሰውም የሚያውቀኝ : እኔም እራሴን የማውቀው እንደ  ተግባር  ሰው ነው::እውቀቴን ለተግባሬ መሳሪያ እድርጌ የኖርኩ ከጦርሜዳ እስክ ህይወት  ማዳን ታላላቅ  ዘመቻዎች (humanitarian operations) በእውቀትና በኩራት ያገለግልኩ ነኝ:: ለኢትዮጵያ  አንድነትና ለአገሬ ህዝብ ፍቅሬን በደሜ አስመክሬአለሁ:: በውጊያ ቆስያለሁ:: አድር ባይ ሆኜ  በደርግ ...

አለም አቀፍ የፋኖ ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ነኝ የሚለው ቡድን ዓላማ ምንድነው ? በወንድወሰን ተክሉ

ይህ ምስል ጸሃፊውን አይወክልም! «...አማራ ለ450 ዓመታ መንፈሱ የተሰበረ ገበሮ ሕዝብ ነው..» ሀብታሙ ተገኝ (ፕ/ር) « እኔ እስክንድር  የአማራ ሕዝብ ከደረሰበት የህልውና አደጋ እኩል የሚሆን ዓላማ አለው ብዬ አላምንም» አቻምየለህ ታምሩ፤ አለም አቀፍ የፋኖ ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ነኝ የሚለው ቡድን ዓላማ ምንድነው ? በወንድወሰን ተክሉ እራሱን አለም አቀፍ የፋኖ ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ነኝ የሚለው ቡድን የዙም ውይይት ፕሮግራም ክፍል ሁለትን የተመለከተ ምልክታ:- ባለፈው  ወር ብቻ ሳይሆን ባለፈው ዓመት ዴሴምበር 2023 ( ዛሬ ጃንዋሪ 1 ቀን 2024 ነን)  እራሱን አለም አቀፍ የፋኖ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ብሎ የሚጠራው ቡድን «ጸረ አማራ ኢትዮጲያዊነት» በሚል አርእስት ስር ሀብታሙ ተገኝ (ፕ/ር) ዋና ተናጋሪ ተጋባዥ የሆነበትን  የዙም ውይይት አካሂዶ የነበረ ሲሆን የዚህ ውይይት ክፍል ሁለት  ባሳለፍነው ወር ዴሴምበር 23ቀን በማዘጋጀት አቻምየለህ ታምሩና ሀብታሙ ተገኝ (ፕ/ር) ተናጋሪ እንግዳ በማድረግ አካሂዷል። በእርግጥ  ከዚህ ከሁለተኛው የውይይት ፕሮግራም በፊት በተክሌ ይሻው በኩል የዙም ሊንክ ተልክሎኝ በሰዓት ጥበት ምክንያት መገኘት ባልችልም ዛሬ ግን በቻናላቸው ላይ የጫኑትን ይህን ክፍል ሁለት ውይይት ከተመለከትኩ በኋላ ይህን ምልክታዬን  አንባቢው ሊረዳ በሚያስችል መልኩ አንድ ሰዓት ከሰላሳ ደቂቃ የፈጀን ውይይት ይዘት በመጭመቅ እንደሚከተለው አቅርቤያለሁ። ይህ ምስል ጸሃፊውን አይወክልም! 1ኛ - ውይይቱን አዘጋጅን ማንነት በተመለከተ፦  አለም አቀፍ የፋኖ ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ባለፈው መስከረም ወር ላይ  በጌታቸው በየነ ሰብሳቢነት ተመሰረትኩ ብሎ እራሱን ያስተዋወቀ ሲ...

ግርማ የሺጥላ => የኦሮሙማው መንግሥት "The New Pearl Harbor" (የመጨረሻው ክፍል) በ Dave Dawit

(Grand operation requires either grand cause or grand pretext‼‼‼) 2. Opportunity፦  ብአዴናዊውና የኦሮሙማ ፋሽስታዊ መንግሥት ተላላኪው ግርማ የሺጥላ በአብይ አህመድ በኩል በተደረገ ምደባ ከፍተኛ ጥበቃ ከሚካሄድላቸው ሹመኞች መካከል አንዱ ነው። በመሆኑም በዚህ ባንዳ ላይ ግድያ የመፈፀም ዕድል ሊኖረው የሚችል አካል፦  ሀ. Highly guarded የሆነን አካል የ security detail surpass ሊያደርግ የሚችል የ ambush drill የሰለጠነ፤ በተለይም በ killing zone መረጣ፣ after attack የ escaping route ዝግጅት፣ target የተደረገው አካል ሊገኝበት በሚችልበት ተሽከርካሪና አጠቃላይ እንቅስቃሴ የተሟላ የኢንተሊጀንስ እና insider information ያለው፣ ከግርማ የሺጥላ የግልና convoy guards ለሚሰነዘርበት የ counter ambush ጥቃት በተኩስና በስልት የበላይነት መያዝ የሚችል በዚህ የ ambush technique ስልጠናም የካበተ ስልጠናና ልምድ ያለው አካል ሊሆን ሲገባው፥ በዚህ ረገድ ተሳዳጁ የአማራ ወጣት በዚህ መጠን Centralized በሆነ የኢንተለጀንስ እና ወታደራዊ አደረጃጀት ባልተቋቋመበት ሁኔታ፣ የግርማ የሺጥላን security shield penetrate አልያም surpass አድርጎ ይህንን ይፈፅማል ማለት ከእውነታና ከአመክንዮ ጋር መጣላት ነው።  * ወደ ቀጣዩ ነጥብ ከማምራታችን በፊት ከቦታው በደረሰን መረጃ መሠረት የዕለቱ የዚህ ብአዴናዊ ሹመኛ የ security detail ምን እንደሚመስል እንመልከት።  ግርማ የሺጥላ ወደ ሰሜን ሸዋ ሲንቀሳቀስ በአራት አይነት መኪኖች በመታጀብ ነበር፦  1. አብይ አህመድ "የልዩ ጥ...

ግርማ የሺጥላ => የኦሮሙማው መንግሥት "The New Pearl Harbor" በ Dave Dawit

(Grand operation requires either grand & noble cause or grand pretext‼‼‼) * 32ኛው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዴልኖ ሩዝቬልትና የፔንታገን የጦር አማካሪዎቻቸው በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በፓስፊክ ውቅያኖስ Pearl harbor የነበረው የአሜሪካ የባህር ኃይል ቤዝ ለጥቃት የተጋለጠ መሆኑን ከማወቅም በላይ በዚያ ልክ ተጋላጭ እንዲሆን ያደረጉት ሆን ብለው ነበር። ከዚያም ተሻግረው በ double agent ሰላዮቻቸው አማካኝነት መረጃው ለጃፓን አመራሮች እንዲደርስም አድርገዋል። የሚፈለገው አላማ ጃፓን ጥቃት እንድትሰነዝርና፥ "ራስን ከጥቃት ለመከላከል" በሚል ሽፋን የአሜሪካን ህዝብ ጎትተው ጦርነት ውስጥ ለመክተት ነበር፥ ያም ተሳካላቸው። * በ ማርች 1998 ዓ.ም የኢራቁ ፕሬዝደንት ሳዳም ሁሴን የአሜሪካን ጆሮ ጭው የሚያደርግ ዜና ይዞ ብቅ አለ። የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክርቤት በኢራቅ ለአስር ዓመታት ጥሎት የነበረው የነዳጅ ሽያጭ ማዕቀብ እየተገባደደ በመሆኑ ማዕቀቡ ሲነሳ ኢራቅ ራሷን ከPetro-Dollar system እንደምታወጣና ሽያጩንም በሌሎች ሀገራት currency እንደምታደርግ ሳዳም ገለፁ። ይህ የሳዳም መግለጫ በአሜሪካ global dominance ላይ የተቃጣ አደገኛ ጥቃትና ይዞት የሚመጣው መዘዝም ከባድ በመሆኑ ዋይት ኋውስ፣ ማንሀተንና ፔንታገን በር ዘግቶ መከረ። መክሮም ሲጨርስ ሳዳም መወገድ ብቻ ሳይሆን ኢራቅም ለሌሎች የ Petro-Dollar እስረኛ የገልፍ ሀገራት መማሪያ መሆን አለባት። ይህንን ለማድረግ ደግሞ grand and noble cause አልያም grand pretext ያስፈልጋል። የመጀመሪያውን ማግኘት ስለማይቻል ብቸኛው አማራጭ የአሜሪካዊያንን እና የአለምን ህዝብ ልብና ...

ኢትዮጵያ አትፈርስም እያሉ በተጨባጭ ግን እያፈረሷት ነው፤ በዶ/ር ሽፈራዉ ገሰሰ

ምስሉ ጸሃፊውን አይወክልም! ኢትዮጵያ ማለት አገር ናት፣ አንድ አገር ደግሞ አገር ለመባል መሬቱ፣ ጫካው፣ ወንዙ፣ ሸንተረሩ፣ ባህሩ፣ ሀይቁ፣ ተራራው፣ ሜዳው፣ደጋው፣ ቆላው፣ ወይናደጋው፣ በረሀው በጠቅላላው መልክዓምድሩ ብቻ ሳይሆን ሌሎች ብዙ ነገሮችን ያጠቃልላል። አገር ሲባል መሬቱ፣ ውሃ ሀብቱ፣ አየሩ፣ ሉዓላዊነቱ ብቻ ሳይሆን ዋነኛው በውስጡ የሚኖረው የአገሪቱ ባለቤት የሆነው ህዝብ ባህሉ፣ ቋንቋው፣ ወጉ፣ ልማዱ፣ ሃይማኖቱ፣ታሪኩ፣ ሰንደቅ አላማው፣ ብሔራዊ መዝሙሩ፣ መለያ አርማው፣ስርዓተ መንግሥቱ፣ አንድነቱ ስርዓተ ትምህርቱ፣ ስነ ጥበቡ፣ ስነ ህንፃው፣ ታሪካዊ ቅርሶቹ፣ ማህበራዊ መስተጋብሩ፣ ብሔራዊ በዓላቱ፣ ጀግኖቹ፣ የጦር ድሎቹ፣ የነፃነትተጋድሎ ታሪኩ፣ ምግብና የምግብ ስርዓቱ፣ኢኮኖሚው ወዘተ የሚያጠቃልል ነው። ኢትዮጵያ የብዙ ሺህ አመታት ስርዓተ መንግሥት ያላት፣ በቅኝ ያልተገዛች ከዓለማችን ቀደምት ስልጣኔወች ካላቸው ጥቂት አገሮች ውስጥ አንዷ ስትሆን በአሁኑ ወቅት ግን ከፍተኛ አደጋ ውስጥ ትገኛለች። ጠቅላይ ሚኒስቴሩን ጨምሮ ሌት ከቀን በሚዲያ እየወጡ ኢትዮጵያ አትፈርስም እያሉ እየለፈፉ በተቃራኒው ግን አገሪቱን እንመራለን ብለው የተሰየሙ ባለስልጣኖች፣ የእነርሱ አላማ ተባባሪ የሆኑ የፓለቲካ ድርጅቶችና ሌሎች አደረጃጀቶች በጋራ በመሆን በተጨባጭ ኢትዮጵያን እያፈረሷት ይገኛሉ። እየሆነ ያለውን ከላይ ከዘረዘርኳቸው የአገር ምልክቶች ውስጥ ጥቂቶቹን ወስጀ ለማሳየት እሞክራለሁ። ሉዓላዊነት አንድ ሉዓላዊ ወይም ነፃ የሆነ አገር የራሱ የሆነ በዓለም አቀፍ ህግ የታወቀ የየብስ የባህርና የአየር ክልል አለው። ይህ አገር ከሚሰጠው ፈቃድ በስተቀር በማንኛውም አገር ወይም አገሮች ሊደፈር ወይም ሊጣስ አይችልም። ነገር ግን በአሁኑ ሰዓት የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት በሰሜን ምዕራብ...