Skip to main content

ስርነቀል ለውጥ ማምጣት የአማራ ብሄርተኝነት የህልውና ትግል ብቸኛ ግብ ነው። በ Alen Kassahun

ምስሉ ጸሃፊውን አይወክልም፡፤


ከ50 አመታት በላይ የተተከለውንና በተግባር እየተፈፀመ ያለውን አማራን ማጥፋትና ኢትዮጵያን ማፍረስ ከስሩ በመንቀል #4ኪሎን ተቆጣጥሮ ስርነቀል ለውጥ ማምጣት የአማራ ብሄርተኝነት የህልውና ትግል ብቸኛ ግብ ነው።

ፋኖ በሚያደርገው የህልውና ትግል አማራ ጠልነት የወለደውን የአማራን ዘር ማጥፋት፤ ማፅዳት፤ የሰባዊ መብት ጥሰትና አገር ማፍረስ አለምአቀፍ ወንጀል ከስሩ ነቅሎ ሊቀብረው #በዋዜማው ላይ እንገኛለን።

ስለሆነም ፋኖ እያደረገ ያለውን የህልውና ትግል #በድል እንዳይቋጭ  በድርድር፣ በእርቅና በምክክር ሰበብ የፋኖን ድል ለመቀልበስና ለመንጠቅ ከአሜሪካ እስከ አዲስ አበባና መቀሌ ድረስ በሚሸረብ ሴራ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ፤ በስልታዊ አማራነትም ሆነ በአማራ ጠልነት የተሰለፉ ቅጥረኞች ደፋ ቀና እያሉ እንደሚገኙ ግልፅ ነው።

ፋኖ #አራት ኪሎን በመቆጣጠር ስርነቀል ለውጥ ለማወጅ በድል ዋዜማ ላይ ሆኖ እያደረገ ያለውን የመጨረሻውን ትንቅንቅ ለማሰናከልና ድሉን ለመሸጥ ተቀጥራችሁ ስለ ድርድር፣ ሽግግር፣ እርቅ፣ ውይይትና በመሳሰሉ አጀንዳዎች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ እየሰሩ የሚገኙ ቅጥረኞችን ከቀጣሪዎች እኩል ማሸነፍና ማስወገድ የህልውና ትግላችን ብቻኛ አማራጭ መሆኑ ለማንም ግልፅ ሊሆን ይገባል።

ስለሆነም የዜግነት ፓለቲካ አቀንቃኝ የ3ኛ ወገን ቅጥረኞችን ከጀርባው አሰልፎ የአማራን ብሄርተኝነት የማድፈቅ አጀንዳቸውን አዝሎ ከአማራ ህልውና ትግል መሀል የተገኘው #እስክንድር ነጋ ከአማራ ህልውና ትግል ጓዙን ጠቅልሎ እንዲወጣ ማድረግ ለነገ የሚባል አይደለም።

የእስክንድር ነጋ #የእየሱስ ክርስቶስነት ገፀ ባህሪ በሂደት እየተገፈፈ መምጣት አማራ ጠል ሀይሎችን ወደ እቅድ ሁለት ሴራ እንዲገቡ እያስገደደ በመሆኑ የአማራ ብሄርተኛ #እስክንድር ነጋን ባደረሰው ኪሳራና ጥፋት በጊዜው የሚጠየቅ መሆኑን አስምሮ ከህልውና ትግሉ #ባስቸኳይ በማባረር የእስክንድር ነጋ ተደራዳሪነት ሴራ ካልተሳካ በቀጣይነት ሊመዘዝ የተያዘውን የሴራ እቅድ ለማክሸፍ የአማራ ብሄርተኛ ከመቸውም ጊዜ በበለጠ በንቃትና በንስር አይን በመከታተል ለማክሸፍና እርምጃ ለመውሰድ የህልውና ትግሉ ያስገድዳል።

አማራነት ያሸንፋል‼️

ፋኖ ይነግሳል‼️

Comments

Popular posts from this blog

ዐማራን ወክሎ ከወያኔ ጋር ስለሰላምም ሆነ ስለትጥቅ ትግል አልፎም ስለመንግሥት መሥረታ መነጋገር ፈጽሞ አይቻልም

ዐማራን ወክሎ ከወያኔ ጋር ስለሰላምም ሆነ ስለትጥቅ ትግል አልፎም ስለመንግሥት መሥረታ መነጋገር ፈጽሞ አይቻልም፤ ዐማራ የተጨፈጨፈው በሦስት ዓመት ዕድሜ ውስጥ ብቻ አይደለም። በ17 ዓመት የወያኔ የሽፍተነት ዘመን፣ 27 ዓመት የወያኔ የመንግሥትነት ዘመን ወደኋላ ተጨምሮ ነው። ከውያኔ ጋር ሰላምን ወይም ትጥቅ ትግልን እናደርጋለን የሚሉ ሁሉ ውሾች ናቸው። "ውሻ ወደ ትፋቱ ይመለሳል" በምሣሌ 26፤11 እና 2ኛ ጴጥሮስ2፤22 የተጠቀሰውን መጽሐፋዊ ዘገባ በማንበብ ከውያኔ ጋር የመከሩትን የውሾች ባህሪ ለይቶ መረዳት ነው። ምስሉ ጸሃፊውን አይወክልም 1ኛ. የዐማራን ሕዝብ የመደብ ጠላት አድርጎ ወያኔን በደደቢት የመሠረተውና 17 ዓመት በትጥቅ ትግል 27 ዓመት በመንግሥትነት በደምሩ 44 ዓመት ከሰባት ሚሊዮን በላይ ዐማራን ሕዝብ ያለማቋረጥ ያስጨፈጨፈ፣ ርስቱን የነጠቀ በጀምላ የገደለ ያፈናቀለ፣ የትግራይን ሕዝብ ከኢትዮጵያዊ ቀዳሚ ሕዝብነቱና ማንነቱ ያስከዳ ስብሐት ነጋ ፤   2ኛ. ከዐማራ ሕዝብ ይልቅ የሱዳን ሕዝብ ይሻለናል ብሎ በማይካድራ በጭና ዐማራን በከፍተኛ መራር በሆነ ጭካኔ ያስጨፈጨፈው፣ በመጨረሻ ተረጋግቶ መኖር ሲችል ዕቅድና ዓላማ በሌለው ጦርነት አንድ ሚሊዮን የትግራይ ወጣት ያስጨፈጨፈ፣ የትግራይን ሕዝብም ሆነ የዐማራን ሕዝብ አዘቅት ውስጥ የከተተ ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ፤   3ኛ. የወያኔ ተሿሚ ሆኖ የዐማራን መሬት ፀገዴና ጠገዴ እያለ እየከፋፈለ ለወያኔ ያስረከበ፣ የግጨውን መሬት ለወያኔ በችሮታ ፈርሞ የሰጠ፤ እነ ዶክተር አባቸው ለማስገደል ቅድመ ሁኔታዎችን ከአመቻቸ በኋላ ወደ አሜሪካ ሀገር ሾልኮ ወጥቶ ከተገደሉ በኋላ ተመልሶ ጥቁር ለብሶ የዓዞ እንባ ሲያነባ ሲመጻደቅ የነበረ የሕወሀትም ሆነ የብልጽግና ቀንደኛና ፊ...

በጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)

ሻለቃ ዳዊትን በተለያዩ ምክንያቶችና ወቅቶች እንደ እኔ የተቻቸው ፈልጋችሁ አታገኙም። ያ ወቅት ሌላ ፤ ዛሬ ሌላ፤- ያ ዘመን ከ2010 ዓ.ም በፊት ነው። ሰው የነበረውን መስመር አስተካክሎ ባዲስ አካሄድ ወቅቱ በሚጠይቀው ጎዳና ከተራመደ ሌላ ምን ይፈለጋል? ዛሬ ግን ሻለቃው “ኢምፖስተር” በማለት የሚጠሩት ህቡእና ግልጽ ነብሰገዳይ ቡድን አሰማርቶ ነብስን የሚቀጭና የሚሰውር <<የወያኔ የነገድ አስተዳዳር አስቀጣዩ የኦሮሙማው የጋጠወጥ ማፍያዎች መሪ>> አብይ አሕመድ ከነገሠ ወዲህ ግን “ሻለቃው” አብይ አሕመድን እንቅልፍ ካሳጡት አርበኞች አንዱ ሆነው ብቅ ብለዋል። ያንን በማድረጋቸው “ጥበብ ሳሙኤል” የተባለ የአብይ አሕመድ አለቅላቂና ፀረ አማራና የሕግ ሙያ ትምሕርተ አለበት ተብሎ የሚነገርለት (?) ጋዜጠኛ:- አብይ አሕመድን በመደገፍ በሻለቃው ላይ ያለ ዕረፍት ረዢም ጊዜ ሲዘልፋቸው ያስገረመኝ ያህል፤ ሰሞኑን ደግሞ በሻለቃ ዳዊት ወ/ልደጊዮርጊስ ላይ አዳዲስ ዘላፊዎች ብቅ ብለዋል። “ሻለቃ ሆይ! በትግሉ ውስጥ ዛሬ ይኑሩ አይኑሩ አማራውን ለመታደግ ከፍታዎትን አሳይተዋል ፤የበኩልዎን አድርገዋል ለዚህም <<በአክብሮት ባርኔጣየን አነሳለዎታለሁ፤ አንኳን ደስ አለዎት !!!!>> አርበኛ ብቅ ባለ ቁጥር ሱሪውን የሚጎትቱ ብዙ የፖለቲካ ተውሳኮች አሉ። ሻለቃው በዛው ዕደሜአቸው የሚቻላቸውን በማድረጋቸውና ከፍታቸውን በማሳየታቸው ፤ ይህን በማድረጋቸው ዓይናቸው ከቀላ ውስጥ አንዱ ወደ “ጥንት ትፋቱ” የተመለሰው፤ በቅርቡ ከወያኔም ከኦነጎችም እየተወዳደሰ መተፋፋግ የጀመረው የወያኔው አሽከር “ኤርሚያስ ለገሰ” እና ዶ/ር አምሳሉ የተባለ “ከጎንደሬዎች እጅህን አንሳ” እያለ ሲከራከረኝ የነበረው እስከ ቅርብ ጊዜ ወዲህ የአብይ አሕመድ አወዳሽ የነበ...

"ምኗ ላይ ተቀምጣ በሽንቷ ሰፌድ ትሰፋላች":- አዲሱ የአቢይ ካቢኔ አሰያዬም ፤ በሸንቁጥ አየለ

ችግሩ ያለዉ የጎሳ ፖለቲካ ርዕዮተ ፍልስፍናዉ ላይ ነዉ::ኢትዮጵያዉያንን ሀገር አልባ ያደረገዉን የጎሳ ፖለቲካ ፍልስፍና መሰረት ላይ የቆመ ካቢኔ ምንም አይነት መልካም ግለሰቦችን ሰብስብቦ ቢያቅፍ ከቶም የሀገር መድሃኒት አያመጣም:: ሆኖም የዚህ ስርዓት የጥቅም ተጋሪዎች እና እግር አጣቢዎች ይሄን የጎሳ ፖለቲካ አስተሳሰብ የተለያዬ የማስመሰያ መቀባቢያ በመቀባት ጸረ ሰዉ የሆነዉን የጎሳ ፖለቲካ አስተሳሰብ ለማስቀጠል እና ህዝብን ለማምታታት ብዙ ሲዳክሩ ይሰተዋላል::በአዲሱ የአቢይ ካቢኔ አሰያዬም የተከናወነዉ ድራማም ይሄዉ ነዉ:: እከሌ ከኦህዴድ:እከሌ ከብአዴን:እንትና ከአብን : እንቶኔ ከኢዜማ: እንቶኔ ደግሞ ከትግራይ ብልጽግና ተሾሙ እያሉ ብዙ የጥቅም ተጋሪዎች እና የአገዛዙ ሚዲያ ብዙ ይቀባጥራሉ::በደስታም እንኳን ደስ አለህ ይባባላሉ::ኢትዮጵያዉያን ግን አሁንም ሀገር አልባ ናቸዉ:: የኢትዮጵያ የችግር ምንጭ ሁሉ አንድ ነዉ::ይሄዉም የጎሳ ፖለቲካ ፍልስፍና ነዉ::መለስ ዜናዊ የሀገሪቱን ጥፋት ያመጣዉ የጎሳ ፖለቲካ ፍልስፍና በማራመድ ነበር::መለስ ዜናዊ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሆኖ በስሩ ብዙ በግለሰብ ደረጃ መጥፎ የማይባሉ ሰዎችን በካቢኔዉ ዉስጥ ሰግስጎ ነበር:: ሆኖም የመለስ ዜናዊ ካቢኔ እያንዳንዱ የሚመራበት መርህ በጎሳ ፖለቲካ ፍልስፍና እና ቀመር ስለሆነ የሚሰሩ ስራዎች ሁሉ በዚሁ መርዛማ ህሳቤ ዙሪያ የሚሽከረከሩ ነበሩ:: አሁንም አቢይ የሾማቸዉ ሰዎች መጥፎ ናቸዉ ጥሩ ናቸዉ የሚለዉ አይደለም ጥያቄዉ:: ወይም ደግሞ ሰዎች ከዬትኛዉ ፓርቲ ተመርጠዉ ተሾሙ አይደለም ጥያቄዉ:: አቢይ የሚመራበትም የፖለቲካ ፍልስፍና እንደ መለስ ዜናዊ ሁሉ የጎሳ ፖለቲካ ፍልስፍና ነዉና ያዉ ዉሃ ቢወቅጡት እንቦጭ ነዉ::ስለዚህ የተሿሚዎቹ መልካምነት ወይም የመጡበት የፓርቲ ቁም ነገ...