ይህ ጊዜ የአማራ ሕዝብ ከጨለማ ዘመን ወደባሳ የጨለማ ዘመን የገባበት ዘመን ነው ። በሕዝባችን ላይ በታወጀው የጥፋት አዋጅ ፣ በርካቶች በአማራነታቸው የታረዱበት ፣ ቤት ንብረታቸውን በትነው ለዘመናት ከኖሩባቸው አካባቢዎች የተፈናቀሉበትና በአገራቸው ባይተዋር ሆነው እንዲኖሩ የተወሰነበት የክፉ ዘመን መጀመሪያ ነው። የአማራ ሕዝብ በጨካኝ ቡድኖች ታይቶና ተሰምቶ በማይታወቅ መልኩ መጠነ ሰፊ ውርጅብኝ እየወረደበትና በግልጽ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየተፈጸመበት ይገኛል ። ለሕዝባችን የሚጮህለት ኃይል የለም። የሕዝባችን በደል የሚገደው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅትም አልተገኘም ። የአብይ አህመድ አሸባሪ መንግስት ወዳጅ የሆኑ ኃያላን አገሮችም በሕዝባችን ላይ የታወጀውን የዘር ፍጅት እያዩ እንዳላዩ ማለፍን መርጠዋል። በአጭሩ ለአማራ ሕዝብ ከራሱ ውጪ ማንም እንደማይጮህለት፣ ማንም እንደማይገደው በሚገባ ተረጋግጧል። ለዚህ ነው ሕዝባችን በሕዝብ ደረጃ ተደራጅቶ ከመታገል ውጪ ምርጫ የለውም የምንለው። ከዘመነ ወያኔ ጅምሮ እስከ ዘመነ ኦህዴድ/ብልጽግና እንደአማራ ሕዝብ የተበደለ፣ እንደአማራ ሕዝብ በጠላትነት የተፈረጀና ስትራቴጂ ተነድፎ እንዲዳከም የተሠራበት ሕዝብ የለም ። በአማራ ላይ ሲደርስ የቆየውንና አሁንም የቀጠለውን መከራ የሚዘግብ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃንም ሆነ የሰብአዊ መብት ተንከባካቢ ተቋም አልተገኘም። ሆኖም ባለመደራጀታችን ምክንያት ይህን በሕዝባችን ላይ ሲፈጸም የቆየውን እና አሁን እየተፈጸመ ያለውን የዘር ማጥፋት ጥቃት ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ማስገንዘብ አልቻልንም። ስለዚህ በአስቸኳይ እንደሕዝብ ተደራጅተንና ሁላችንም የሕዝባችን ዲፕሎማቶች ሆነን ፤ በማያቋርጥ ትግልና ውትወታ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰ...
Welcome to TBF Blog Chanel! እንኳን በደህና መጡ ወደ TBF Blog Chanel