Skip to main content

Posts

Showing posts with the label ኢትዮጵያ አትፈርስም እያሉ በተጨባጭ ግን እያፈረሷት ነው

ኢትዮጵያ አትፈርስም እያሉ በተጨባጭ ግን እያፈረሷት ነው፤ በዶ/ር ሽፈራዉ ገሰሰ

ምስሉ ጸሃፊውን አይወክልም! ኢትዮጵያ ማለት አገር ናት፣ አንድ አገር ደግሞ አገር ለመባል መሬቱ፣ ጫካው፣ ወንዙ፣ ሸንተረሩ፣ ባህሩ፣ ሀይቁ፣ ተራራው፣ ሜዳው፣ደጋው፣ ቆላው፣ ወይናደጋው፣ በረሀው በጠቅላላው መልክዓምድሩ ብቻ ሳይሆን ሌሎች ብዙ ነገሮችን ያጠቃልላል። አገር ሲባል መሬቱ፣ ውሃ ሀብቱ፣ አየሩ፣ ሉዓላዊነቱ ብቻ ሳይሆን ዋነኛው በውስጡ የሚኖረው የአገሪቱ ባለቤት የሆነው ህዝብ ባህሉ፣ ቋንቋው፣ ወጉ፣ ልማዱ፣ ሃይማኖቱ፣ታሪኩ፣ ሰንደቅ አላማው፣ ብሔራዊ መዝሙሩ፣ መለያ አርማው፣ስርዓተ መንግሥቱ፣ አንድነቱ ስርዓተ ትምህርቱ፣ ስነ ጥበቡ፣ ስነ ህንፃው፣ ታሪካዊ ቅርሶቹ፣ ማህበራዊ መስተጋብሩ፣ ብሔራዊ በዓላቱ፣ ጀግኖቹ፣ የጦር ድሎቹ፣ የነፃነትተጋድሎ ታሪኩ፣ ምግብና የምግብ ስርዓቱ፣ኢኮኖሚው ወዘተ የሚያጠቃልል ነው። ኢትዮጵያ የብዙ ሺህ አመታት ስርዓተ መንግሥት ያላት፣ በቅኝ ያልተገዛች ከዓለማችን ቀደምት ስልጣኔወች ካላቸው ጥቂት አገሮች ውስጥ አንዷ ስትሆን በአሁኑ ወቅት ግን ከፍተኛ አደጋ ውስጥ ትገኛለች። ጠቅላይ ሚኒስቴሩን ጨምሮ ሌት ከቀን በሚዲያ እየወጡ ኢትዮጵያ አትፈርስም እያሉ እየለፈፉ በተቃራኒው ግን አገሪቱን እንመራለን ብለው የተሰየሙ ባለስልጣኖች፣ የእነርሱ አላማ ተባባሪ የሆኑ የፓለቲካ ድርጅቶችና ሌሎች አደረጃጀቶች በጋራ በመሆን በተጨባጭ ኢትዮጵያን እያፈረሷት ይገኛሉ። እየሆነ ያለውን ከላይ ከዘረዘርኳቸው የአገር ምልክቶች ውስጥ ጥቂቶቹን ወስጀ ለማሳየት እሞክራለሁ። ሉዓላዊነት አንድ ሉዓላዊ ወይም ነፃ የሆነ አገር የራሱ የሆነ በዓለም አቀፍ ህግ የታወቀ የየብስ የባህርና የአየር ክልል አለው። ይህ አገር ከሚሰጠው ፈቃድ በስተቀር በማንኛውም አገር ወይም አገሮች ሊደፈር ወይም ሊጣስ አይችልም። ነገር ግን በአሁኑ ሰዓት የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት በሰሜን ምዕራብ...