ሻ/ቃ ዳዊት ወ/ጊወርጊስ ስለራሳቸው የጻፉት ።
Dawit W/Giorgis |
የአማራ ሕዝባዊ ግንባር የውጭ ድጋፍ ሰጪ ግብረ ሀይልን እዚህ ለማድረስ ቁልፍ ሚና በመጫወቴ ደስተኝ ነኝ:: ይህንን እድል ለሰጠኝ ወደር ለሌለው ጀግና እስክንድር ነጋ ምስጋናዬን እቀርባልሁ:: ይህንን ግዙፍ ሀላፊነት ለመወጣት ከሚታወቀው በላይ ያለ እረፍት ሌት ተቀን የሰሩትን የስራ ባልደረቦቼን እደንቃለሁ:: አመሰግናለሁ::
እኔ የስራ ሰው ነኝ:: የእወቀትም ሰው ነኝ:: ታሪካዊና ትምህርታዊ የሆኑ አራት መፅሀፎችም ፅፌአለሁ:: በእንግሊዝኛም በአማርኛም::አልቀረብኝም:: ቁጥራቸው በጣም ብዙ የሆኑ ምሁራዊ ፅሁፎችን አሳትሜአለሁ::ከአውስትራሊያ አውሮፓና አሚሪካ ካናዳ የተለያዩ ሚዲያዎች ላይ ለብዙ አመታት ቀርቤአለሁ:: ፅሁፎቼም በ CNN ሳይቀር ወጥተውልኛል::
አገልግሎቴን ግን የምመዝነው በተግባሬ ነው:: እውቀቴን በተግባር በማዋል የተመሰከረልኝ ነኝ:: እውቀትና ተግባርን በማያያዝ በውትድርና ሙያ፣ በኤርትራ አስተዳዳሪነት፣ በዲፕሎማሲ፣ በተባበሩት መንግስታትና ለተለያዪ መንግስታት በችሎታ አማካሪ ሆኜ አገልግያለሁ::
ሰውም የሚያውቀኝ : እኔም እራሴን የማውቀው እንደ ተግባር ሰው ነው::እውቀቴን ለተግባሬ መሳሪያ እድርጌ የኖርኩ ከጦርሜዳ እስክ ህይወት ማዳን ታላላቅ ዘመቻዎች (humanitarian operations) በእውቀትና በኩራት ያገለግልኩ ነኝ:: ለኢትዮጵያ አንድነትና ለአገሬ ህዝብ ፍቅሬን በደሜ አስመክሬአለሁ::
በውጊያ ቆስያለሁ:: አድር ባይ ሆኜ በደርግ የፖለቲካ ሥርዓት መቆየት ስችል ከሥርዓቱ መራቅ ብቻ ሳይሆን ወጥቼ ስርአቱን ለማስለወጥ ረዥምና ውስብስብ ትግል ውስጥ የነበርኩ ነኝ:: ለዚሁ ትግል በሱዳንና በኬንያ ጠረፎች አድርገን አንዳንድ ሁኔታዎችን ለማስተባበር አገር ቤት በድብቅ በእግር ገብቻለሁ:: በጊዜው እድሜዬም ትንሽ አልነበረም::
ደርግ ስሜን ለማጥፋት ያደረገውን ዘመቻ በህግ ሀሰት መሆኑን እስመስክሬአለሁ::
በአንድ ህይወት ይህንን ያህል የሥራ ውጤት ያካበተ ብዙም ሰው አይገኝምብል ማጋነን አይሆንብኝም። ለዚህም እግዚአብሄርን ከማመስገን አላቋርጥም::ለእዚህ ነው የመጨረሻውን መፅሀፌን “What a Life” ያልኩት:: ብዙ ድካምና ጊዜ የወሰደ መፅሀፍ ነው:: የሶስቱም መፅሀፎች ሽያጭ ለበጎ ስራ የተሰጡ ናቸው:: ማሳተሚያውን በግሌ ነው የከፈልኩት:: የመጨረሻው ግን በአስተዋፅኦ ነው የተከፈለው::
አማራ ሲጎዳ፣ የዘር ማጥፋት ወንጀል ሲፈፅምበት ከጎኑ ቆሜአለሁኝ:: አብይንና የወንጀሉ እስፈፃሚዎችን በኢንተርናሽናል ፍርድ ቤት ለማቅረብ ሌሎች ስራዎቼን እቁሜ ለሁለት አመት በጎደኞቼ ድጋፍ ጥናቱን አጠናቀን ለፍርድ ቤት አቅርበናል:: የኢንተርናሽናል ፖለቲካ መሰናክል እጋጥሞን አብይ አህመድ ፍርድ ቤት ገና አልቀረበም:: ከዚያም በሁዋላ ብዙ ወንጀሎች ስለ ተፈፅሙ ተጭማሪ ስራዋች ይጠይቃል:: በጊዜው ከነበረችው የፍርድ ቤቱ አቃቤ ሕግ ( ICC prosecutor general) ጋር ለዚህ ጉዳይ በቀጥታ የተገናኘ ሌላ ኢትዮጵያዊ አላውቅም:: ከእኔ ጋር በቀጥታ ተፃፅፈናል:: በእሷ ሥር ከነበሩ የህግ አዋቂዋችና የክፍል ሃላፊዋች ጋር ክሱን በተመለከተ ፕሮፌሽናል ውይይት እድርገናል:: ጥናቱም ሆነ ለዚህ ጥረት ተብሎ የተሰበሰበው ገንዘብ በቤተ ክህነቱ አካውንት ይገኛል::
ዛሬም ከእስክንድር ሌላ ጥሪ ሲመጣብኝ ስራዬን ሙሉ ለሙሉ አቁሜ ተቀላቅየዋለሁኝ:: ራሴን ጡረታ ካስወጣሁ በሁዋላ The Africa Institute for Strategic and Security Studies (AISSS) www. aisss.org አፍሪካ ምድር አቋቁሜ የድርጅቱ ዋና ስራ እስኪያጅ ሆኜ በመስራት ያለሁበትን ትቼ አለክፍያ ሙሉ ለሙሉ ጊዜዬን ለፋኖ ትግል ስጥቻለሁ:: የፋኖ እንቅስቃሴ ከተጀመረ በሁዋላ በአለም ደረጃ ትግላችን እንዲታወቅ የተደረገው ከግንባሩ ምስረታ በሁዋላ ነው::በኢንትርሽናል ደረጃ በአውሮፖና በአሜሪካ በአፍሪካ ( በዲፕሎማሲ ዘርፍ) በይፋ ከተነገሩት ሌላ በግንባሩ ስም እኔ የፈፅምኳቸው ጊዜው ሲደርስ ይገለፃሉ::
በአስራ ስባት አመቴ ወታደርነት የታጨሁ: ሶስት አመት ከታወቀው የቀኃስ ወታደራዊ አካዳሚ የሰለጠንኩ: አንድ አመት አሜሪካን አገር 10 ወር ሌላም ቦታ ለጥቂት ወራት ተጨማሪ ልዩ ስልጠና የፈፅምኩ ኩሩ ወታደር ነኝ:: አራት አመት ቀኃስ ዪኒቨርስቲ: (LLB) ከዚያ ሁለት ዓመት ኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ ( JD – Doctor of Jurisprudence) ቀጥሎ SMU ቴክሳስ ለPhD ቆይቼ የእናት አገር ጥሪን ተቀብዬ በደርግ ጊዜ አገሬ ተመልሻለሁ::ከዚህም በላይ በሶስት ታላላቅ ዩኒቨርሲቲዋች ( Princeton, Universty of Cape Town,Boston University, African Studies Center) በተለያዩ ጊዚያት Visting Scholar ሆኜ ተስይሜ ምርምር ስራዎች ውስጥ ተሳትፌአለሁኝ::
እንደ ዛሬው ሳይሆን በቀድሞ አባቶቻችን አርበኝነት ስሜትና ሥነስርአት ተኮትኩቼ እዚህ የደረስኩ: የዘመኑ ትምህርትና ምቾት ያልለወጠኝ ኩሩ ልበ ሙሉ ኢትዯጵያዊ ነኝ:: የእኔ አማራነት፣ የእኔ እስተዋፅኦ፣ የእኔ ኢትዮጵያዊነት በጥቂት የሴራ ፓለቲከኞች፣ ቡድንተኞችና ምቀኞች የሚተች አይደለም:: በጠባብ እውቀት: እዚህ ግባ በማይባል ልምድ: ወይንም አለምንም ልምድ: ድንበር በዘለለ ምቀኝነት: የእኔን ምንነትና ማንነት ማንቋሸሽ ጊዜው እልፎአል:: ህይወቴ ሲፈተሽ ኖሮአል:: ምክትል ሚኒስትር፣ በሚኒስትር ደረጃ ኮሚሽነር፣ የኤርትራ ክፍለሀገር ዋና ተጠሪ የነበርኩ፤ ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት በሁዋላ ያልታየ ታላቅ ኢንተርናሽናል የረሀብ ዘመቻ የመራሁ፣ በብዙ አለም አቀፍ ፅሁፎችና መድረኮች የተጠቀስኩ፣ ከብዙ መንግስታት መሪዋች ጋር በልኡካን መሪነት ቀጥሎም ከ25 ዓመት በላይ በኢንተርናሽናል አማካሪነት አፍሪካ የስራሁ፣ ለመሪዎች ጥናት ያቀረብኩ፣ ከታላላቅ ስዎች ጋር የተወያየሁ፣ ብዙ የተመስገንኩና የተከበርኩ ሰው ነኝ::
አማራን ለማደራጀትና ማህበራቱ በአንድ ጃንጥላ ስር ሆነው እንዲታገሉ የዛሬ ስምንት ዓመትና ከዚያም በሁዋላ ከቅርብ የትግል ወዳጆቼ ጋር ( አቶ ሃይለ ገብርኤል እስረስና ፕሮፌስር ጌታቸው በጋሻው) ብዙ እልህ አስጨራሽ ስብስባዎች መርቻለሁ:: በመጨረሻም “አንድ አማራ” የሚለውን ድርጅት አዋልደናል:: አብይ ስልጣን ላይ ሲወጣ ድርጅቱ ከሰመ:: አሁን ያለው “አንድ አማራ” ከቀድሞው ጋር የተያያዘ አይደለም::
Comments