Skip to main content

በጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)

ሻለቃ ዳዊትን በተለያዩ ምክንያቶችና ወቅቶች እንደ እኔ የተቻቸው ፈልጋችሁ አታገኙም። ያ ወቅት ሌላ ፤ ዛሬ ሌላ፤- ያ ዘመን ከ2010 ዓ.ም በፊት ነው። ሰው የነበረውን መስመር አስተካክሎ ባዲስ አካሄድ ወቅቱ በሚጠይቀው ጎዳና ከተራመደ ሌላ ምን ይፈለጋል? ዛሬ ግን ሻለቃው “ኢምፖስተር” በማለት የሚጠሩት ህቡእና ግልጽ ነብሰገዳይ ቡድን አሰማርቶ ነብስን የሚቀጭና የሚሰውር <<የወያኔ የነገድ አስተዳዳር አስቀጣዩ የኦሮሙማው የጋጠወጥ ማፍያዎች መሪ>> አብይ አሕመድ ከነገሠ ወዲህ ግን “ሻለቃው” አብይ አሕመድን እንቅልፍ ካሳጡት አርበኞች አንዱ ሆነው ብቅ ብለዋል።

ያንን በማድረጋቸው “ጥበብ ሳሙኤል” የተባለ የአብይ አሕመድ አለቅላቂና ፀረ አማራና የሕግ ሙያ ትምሕርተ አለበት ተብሎ የሚነገርለት (?) ጋዜጠኛ:- አብይ አሕመድን በመደገፍ በሻለቃው ላይ ያለ ዕረፍት ረዢም ጊዜ ሲዘልፋቸው ያስገረመኝ ያህል፤ ሰሞኑን ደግሞ በሻለቃ ዳዊት ወ/ልደጊዮርጊስ ላይ አዳዲስ ዘላፊዎች ብቅ ብለዋል።

“ሻለቃ ሆይ! በትግሉ ውስጥ ዛሬ ይኑሩ አይኑሩ አማራውን ለመታደግ ከፍታዎትን አሳይተዋል ፤የበኩልዎን አድርገዋል ለዚህም <<በአክብሮት ባርኔጣየን አነሳለዎታለሁ፤ አንኳን ደስ አለዎት !!!!>>

አርበኛ ብቅ ባለ ቁጥር ሱሪውን የሚጎትቱ ብዙ የፖለቲካ ተውሳኮች አሉ። ሻለቃው በዛው ዕደሜአቸው የሚቻላቸውን በማድረጋቸውና ከፍታቸውን በማሳየታቸው ፤ ይህን በማድረጋቸው ዓይናቸው ከቀላ ውስጥ አንዱ ወደ “ጥንት ትፋቱ” የተመለሰው፤ በቅርቡ ከወያኔም ከኦነጎችም እየተወዳደሰ መተፋፋግ የጀመረው የወያኔው አሽከር “ኤርሚያስ ለገሰ” እና ዶ/ር አምሳሉ የተባለ “ከጎንደሬዎች እጅህን አንሳ” እያለ ሲከራከረኝ የነበረው እስከ ቅርብ ጊዜ ወዲህ የአብይ አሕመድ አወዳሽ የነበረው “ከጠ/ቅላይ ሚኒስትሩ በታች ያሉት እንጂ እሳቸው ተገቢው ሥራቸው እየሰሩ ነው…>> እያለ አየሩን ሲየቆሽሽ የነበረው (በቅርቡ ደግሞ ከኔ አልፎ ዘመድኩን በቀለ (ነጭ ነጭዋን) ጋር የተጣመደው “ጎንደር ለጎንደሬዎች” ባዩ ዶ/ር አምሳሉ የተባለው በሻለቃው ላይ አፉን የሚከፍተውና እና ሌለው ደግሞ እንዲሁ በወያኔ ዘመን “የኦነግ ባንዴራም የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማም እኩል አሸብርቁ” እያለ ሲያውከን የነበረው ዛሬ የአብይ አሕመድ ካድሬ ሆኖ “የሃቅና ሳቅ” ዩቱብ አዘጋጅ “አበበ ቶላ” (ቶኩቻው) የተባለው እንግሊዝ አገር የሚኖሮው <<የፖለቲካ ባለጌ>> ፤ ባልተገራ ምላሱ በውትድርና እና በትምህርት እንዲሁም አገራቸውን ያገለገሉበት የውትድርና ማዕርጋቸውን በማንኳሰስ “ሹሉቃ” እያለ የመንደር ስድብ ሲዘልፋቸው መስማት እጅግ ከገረመኝ የሰሞኑ ክስተት አንዱ ነው። ሌሎችም አሉ።

ሻለቃ ዳዊትን ብቻ ሳይሆን የተጠመዱት <<ታላቁ አርበኛ እስክንድር ነጋንም>> ሳይቀር “እስክንድር ያለ ቦታው ነው የገባው፤ እዛ በረሃ ጠመንጃ ይዞ ከመታገል ይልቅ እዚህ መጥቶ ለተጋዮቹ የንዋይ (የገንዘብ) ድጋፍ ሰጪ ቢሆን የረባ አስተዋጽኦ ያደርግ ነበር>> ሲል ያደመጥኩት እጅግ የማከብረው ተመራማሪው ወጣት ምሁሩ የጥንቱ ወዳጄ <<አቻምየለህ ታምሩ>> እንዴት ወደ እዚህ ዓይነት የወረደ ግምገማ እንደገባ አስደግጦኛል። ምሁሩ ፕሮፌሰር ሃብታሙም በበኩሉ “የእስክንድር ዓላማ ምንድነው?” ሲሉ አቻምየለህ ታምሩ ጋር አብረው ጠይቋል። እስክንድር ለምን ተገፍቶ ፤ ተገፍቶ ፤ ተገፍቶ ፤ እኛ እና ጠያቂዎቹ ያልተቀበልነው መከራ የተቀበለ አስገራሚ የዘመናችን አርበኛ እስክንድር “ኣላማው ምንድነው?” ትበሎ ሲጠየቅ እውነት እስክንድር ለምን ተገፍቶ እዛ ጫካ እንደገባ ዓላማው ለምን እና ለማን ተብሎ ፍዳውን እያየ እንዳለ “ሰሚ አጥቶ ለነበረው ለአማራው ተስፋ ; መመኪያ ፤ የሞራልና የጉልበት አለኝታ እየሆነ እንደሆነ እውን ይጠፋቸዋል? ዓለማው ምንድነው!? ደጋግሞ እስክንድር ያዳመጠ ሰው እንዴት ዓላማው እስካሁን አልበራለትም? ከጥፋት ራስን መከላከል እንዴት የዓላማ ጥያቄ ያስነሳል? ወይ ከዚህ ከዲያስፖራ ምቾት ለቅቀን እዛው ጫካ እራሳችንን እናግኝ ካልሆነ “መከራቸውን እያዩ ላሉ ራሳቸውን ከመጠቃት ለማዳን የሚታገሉ ዜጎችን ጥያቄ ውስጥ ማስገባት ነውር ነው። በዙርያቸው ለግንጠላ እየሄዱ ባሉ ታጣቂዎች የተከበበው የአማራ ሕዝብና ሕዝባቸው በጥቃት ቀለበት የገባባቸው ታጋዮች፤ ዓላማቸው ምንም ይሁን ምን ለጥያቄ የሚቀርቡ አይደሉም።

እኛ በተደንደላቀቀ አልጋ ተኝተን ግማሹ እስር ቤት በካቲና ታስሮ ግማሹ በየጫካው በጥይት እየተቆላ እኛ ዩ ቱብ ላይ በጋለ ብረት በሚጠበሱ በታሰሩትና በጥይት በሚቆሉት ላይ ዓላማን ማስነሳት ዕብደት ወይስ እውቀት? እነ መስከረም አበራ እና በሺዎቹ እመጫቶች ልጆቻቸውን ጥለው በጭለማ ታስረዋል፤ እነዚህን ለማስለቀቅ በሚጥሩ አርበኞች ላይ መሳለቅና ዓላማቸውን መጠየቅ የተመቻቸው ሰዎች ጥያቄ ነው። እግዚአብሔርን እንፍራ እንጂ። እኔ ትግሬ ነኝ፤ ትግራይ ምድር ውስጥ በየአዳራሹ የሚነገረው ስለግንጠላ ነው፤ ብታደምጧቸው ትደነግጡና ዕብደት ወይስ ድንቁርና ትላላችሁ። ጉዟቸው ስለ ግንጠላ ዛቻ እንጂ ስለ አንድነት አይደለም። ኦሮሞዎቹም እንደዚያ፤ በነዚህ መሃል እንደ “ሳንድዊች” የታጠፈው ሕዝብ እንደሚዳቓ ያለ ተከላካይ ቆሞ በሁለም እቅጣጫ ይለቅ? የነዚህ ታጋዮች ዓላማ መጠየቅ ፈጣሪን የደፈርነው መስሎ አልታያችሁም?

መስክሩላቸው ብንባል <<አፋቸው ማይክሮፎን ላይ መትከል እንጂ “ተግዳሮትን” (ቻለንጅን) መቋቋም የማይችሉትን እንደ እነ ኤርምያስ ለገሰ እና የፖለቲካ ባለጌው “አበበ ተላ” (ቶኪቻው) በሻለቃውና በእስክንድር ትግል ላይ “ከስራ መልስ የድብርታቸው ማስወገጃ በማድረግ” በየዩቱቡ ተድጠው የነዚህ ሰዎች ትግልና ማዕረጋቸውን ማብጠልጠል ስናደምጥ ‘ዩ ቱብ’ የሚባለው እጅግ ሲበዛ የፖለቲካ ባለጌዎችን የልብ ልብ ሰጥቷቸው በታጋዮች ላይ ሲቀልዱ ማድመጥ እውነትም <<ኢትዮጵያ አገሬ መኝ ነሽ ተላላ የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ>> የሚባለው እውነት ነው።

Comments

Popular posts from this blog

ኪራላይሶን…!

 በዘመድኩን በቀለ "…ሲላ ዱኤ ጂራ… ትላለች ሴቷ ተናጋሪ… ሞቷል እኮ ነው የምትለው። ከሞተ በኋላ ለምን እንዲህ ማድረግ አስፈለገ? የሚል ድምፀት ያለው ቃል ነው የምታሰማው በኦሮሚኛ። …ዐማራ ገዳዩ የአብይ ሽመልስ ሸኔ ደግሞ አስከሬን ላይ ቆሞ ያላግጣል። ሌላኛው ደግሞ የሞተው ዐማራ አስከሬን ፊት ላይ ድንጋይ ይጭንበታል። "…ቪድዮ ቀራጩም እንዲህ ይላል። ሲንሙሊሱ… ማለትም አላሳይህም። መልክህን እንዲታይ አላደረኩም ነው የሚለው። አስከሬኑ ላይ የቆመው ባለ ጊዜም እንዲህ ይላል። ረኮን ኢንጂሩ። ችግር የለም። ብታይስ ምን ሊመጣ? ከሳሽ የለ? ጠያቂ የለ? ጊዜው እኮ የእኛ ነው እንደማለት ነው።  "…አስተውላችሁ ከሆነ አቢይ አሕመድ ሥልጣን ላይ ከወጣ ጊዜ ጀምሮ የኦርቶዶክስ በዓላትን ጠብቆ አሰቃቂ አረመኔያዊና ጭካኔ የተመላበትን ዘግናኝ ድርጊት ይፈጽማል። በዓለ መስቀልን፣ ጥምቀትን፣ ስቅለትን፣ ትንሣኤን፣ ዕርገትንም ጠብቆ እንዲሁ ነው። በወይራ ጢስ የመጣ አጋንንታም የጠንቋይ የዲያብሎስ የግብር ልጇ ስለሆነ ኦርቶዶክሳውያን በዓልን ተረጋግተው አሳልፈው አያውቁም። እስከመቼ እንዲህ እንደሚቀጥል ግን አላውቅም። "…ይሄን ዘግናኝ ጭፍጨፋ ለመቀልበስ፣ ያለፍርድም አልሞትም ማለት ለዐማራው አይፈቀድለትም። በሰሜን ሸዋ በጅብውኃ በኦሮሞ ሸኔ የተጨፈጨፉት ዐማሮች አስከሬን እስከአሁን አልተነሣም። መከላከያ በስፍራው ቢኖርም ድርጊቱን አይቃወምም። ሕዝቡም አስከሬን እንዳያነሣ ተከልክሏል። ይሄ ማለት ዐማሮች ይሄን እያዩ የሚያድናቸው ፓርቲ፣ የሚታደጋቸው መሪ ድርጅትም እንደሌላቸው ዐውቀው ሰጥ ለጥ ብለው በባርነት እንዲገዙ አልያም ያለ ከልካይ በዚህ መልክ እንደሚጨፈጭፉት መልእክት ለማስተላለፍ ነው። የእግዚአብሔር በቀል ግን ይከተላል።  • ዛሬ ለዐማራ ...

አለም አቀፍ የፋኖ ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ነኝ የሚለው ቡድን ዓላማ ምንድነው ? በወንድወሰን ተክሉ

ይህ ምስል ጸሃፊውን አይወክልም! «...አማራ ለ450 ዓመታ መንፈሱ የተሰበረ ገበሮ ሕዝብ ነው..» ሀብታሙ ተገኝ (ፕ/ር) « እኔ እስክንድር  የአማራ ሕዝብ ከደረሰበት የህልውና አደጋ እኩል የሚሆን ዓላማ አለው ብዬ አላምንም» አቻምየለህ ታምሩ፤ አለም አቀፍ የፋኖ ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ነኝ የሚለው ቡድን ዓላማ ምንድነው ? በወንድወሰን ተክሉ እራሱን አለም አቀፍ የፋኖ ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ነኝ የሚለው ቡድን የዙም ውይይት ፕሮግራም ክፍል ሁለትን የተመለከተ ምልክታ:- ባለፈው  ወር ብቻ ሳይሆን ባለፈው ዓመት ዴሴምበር 2023 ( ዛሬ ጃንዋሪ 1 ቀን 2024 ነን)  እራሱን አለም አቀፍ የፋኖ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ብሎ የሚጠራው ቡድን «ጸረ አማራ ኢትዮጲያዊነት» በሚል አርእስት ስር ሀብታሙ ተገኝ (ፕ/ር) ዋና ተናጋሪ ተጋባዥ የሆነበትን  የዙም ውይይት አካሂዶ የነበረ ሲሆን የዚህ ውይይት ክፍል ሁለት  ባሳለፍነው ወር ዴሴምበር 23ቀን በማዘጋጀት አቻምየለህ ታምሩና ሀብታሙ ተገኝ (ፕ/ር) ተናጋሪ እንግዳ በማድረግ አካሂዷል። በእርግጥ  ከዚህ ከሁለተኛው የውይይት ፕሮግራም በፊት በተክሌ ይሻው በኩል የዙም ሊንክ ተልክሎኝ በሰዓት ጥበት ምክንያት መገኘት ባልችልም ዛሬ ግን በቻናላቸው ላይ የጫኑትን ይህን ክፍል ሁለት ውይይት ከተመለከትኩ በኋላ ይህን ምልክታዬን  አንባቢው ሊረዳ በሚያስችል መልኩ አንድ ሰዓት ከሰላሳ ደቂቃ የፈጀን ውይይት ይዘት በመጭመቅ እንደሚከተለው አቅርቤያለሁ። ይህ ምስል ጸሃፊውን አይወክልም! 1ኛ - ውይይቱን አዘጋጅን ማንነት በተመለከተ፦  አለም አቀፍ የፋኖ ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ባለፈው መስከረም ወር ላይ  በጌታቸው በየነ ሰብሳቢነት ተመሰረትኩ ብሎ እራሱን ያስተዋወቀ ሲ...

ኢትዮጵያ አትፈርስም እያሉ በተጨባጭ ግን እያፈረሷት ነው፤ በዶ/ር ሽፈራዉ ገሰሰ

ምስሉ ጸሃፊውን አይወክልም! ኢትዮጵያ ማለት አገር ናት፣ አንድ አገር ደግሞ አገር ለመባል መሬቱ፣ ጫካው፣ ወንዙ፣ ሸንተረሩ፣ ባህሩ፣ ሀይቁ፣ ተራራው፣ ሜዳው፣ደጋው፣ ቆላው፣ ወይናደጋው፣ በረሀው በጠቅላላው መልክዓምድሩ ብቻ ሳይሆን ሌሎች ብዙ ነገሮችን ያጠቃልላል። አገር ሲባል መሬቱ፣ ውሃ ሀብቱ፣ አየሩ፣ ሉዓላዊነቱ ብቻ ሳይሆን ዋነኛው በውስጡ የሚኖረው የአገሪቱ ባለቤት የሆነው ህዝብ ባህሉ፣ ቋንቋው፣ ወጉ፣ ልማዱ፣ ሃይማኖቱ፣ታሪኩ፣ ሰንደቅ አላማው፣ ብሔራዊ መዝሙሩ፣ መለያ አርማው፣ስርዓተ መንግሥቱ፣ አንድነቱ ስርዓተ ትምህርቱ፣ ስነ ጥበቡ፣ ስነ ህንፃው፣ ታሪካዊ ቅርሶቹ፣ ማህበራዊ መስተጋብሩ፣ ብሔራዊ በዓላቱ፣ ጀግኖቹ፣ የጦር ድሎቹ፣ የነፃነትተጋድሎ ታሪኩ፣ ምግብና የምግብ ስርዓቱ፣ኢኮኖሚው ወዘተ የሚያጠቃልል ነው። ኢትዮጵያ የብዙ ሺህ አመታት ስርዓተ መንግሥት ያላት፣ በቅኝ ያልተገዛች ከዓለማችን ቀደምት ስልጣኔወች ካላቸው ጥቂት አገሮች ውስጥ አንዷ ስትሆን በአሁኑ ወቅት ግን ከፍተኛ አደጋ ውስጥ ትገኛለች። ጠቅላይ ሚኒስቴሩን ጨምሮ ሌት ከቀን በሚዲያ እየወጡ ኢትዮጵያ አትፈርስም እያሉ እየለፈፉ በተቃራኒው ግን አገሪቱን እንመራለን ብለው የተሰየሙ ባለስልጣኖች፣ የእነርሱ አላማ ተባባሪ የሆኑ የፓለቲካ ድርጅቶችና ሌሎች አደረጃጀቶች በጋራ በመሆን በተጨባጭ ኢትዮጵያን እያፈረሷት ይገኛሉ። እየሆነ ያለውን ከላይ ከዘረዘርኳቸው የአገር ምልክቶች ውስጥ ጥቂቶቹን ወስጀ ለማሳየት እሞክራለሁ። ሉዓላዊነት አንድ ሉዓላዊ ወይም ነፃ የሆነ አገር የራሱ የሆነ በዓለም አቀፍ ህግ የታወቀ የየብስ የባህርና የአየር ክልል አለው። ይህ አገር ከሚሰጠው ፈቃድ በስተቀር በማንኛውም አገር ወይም አገሮች ሊደፈር ወይም ሊጣስ አይችልም። ነገር ግን በአሁኑ ሰዓት የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት በሰሜን ምዕራብ...