(Grand operation requires either grand & noble cause or grand pretext‼‼‼)
* 32ኛው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዴልኖ ሩዝቬልትና የፔንታገን የጦር አማካሪዎቻቸው በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በፓስፊክ ውቅያኖስ Pearl harbor የነበረው የአሜሪካ የባህር ኃይል ቤዝ ለጥቃት የተጋለጠ መሆኑን ከማወቅም በላይ በዚያ ልክ ተጋላጭ እንዲሆን ያደረጉት ሆን ብለው ነበር። ከዚያም ተሻግረው በ double agent ሰላዮቻቸው አማካኝነት መረጃው ለጃፓን አመራሮች እንዲደርስም አድርገዋል። የሚፈለገው አላማ ጃፓን ጥቃት እንድትሰነዝርና፥ "ራስን ከጥቃት ለመከላከል" በሚል ሽፋን የአሜሪካን ህዝብ ጎትተው ጦርነት ውስጥ ለመክተት ነበር፥ ያም ተሳካላቸው።
* በ ማርች 1998 ዓ.ም የኢራቁ ፕሬዝደንት ሳዳም ሁሴን የአሜሪካን ጆሮ ጭው የሚያደርግ ዜና ይዞ ብቅ አለ። የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክርቤት በኢራቅ ለአስር ዓመታት ጥሎት የነበረው የነዳጅ ሽያጭ ማዕቀብ እየተገባደደ በመሆኑ ማዕቀቡ ሲነሳ ኢራቅ ራሷን ከPetro-Dollar system እንደምታወጣና ሽያጩንም በሌሎች ሀገራት currency እንደምታደርግ ሳዳም ገለፁ። ይህ የሳዳም መግለጫ በአሜሪካ global dominance ላይ የተቃጣ አደገኛ ጥቃትና ይዞት የሚመጣው መዘዝም ከባድ በመሆኑ ዋይት ኋውስ፣ ማንሀተንና ፔንታገን በር ዘግቶ መከረ። መክሮም ሲጨርስ ሳዳም መወገድ ብቻ ሳይሆን ኢራቅም ለሌሎች የ Petro-Dollar እስረኛ የገልፍ ሀገራት መማሪያ መሆን አለባት። ይህንን ለማድረግ ደግሞ grand and noble cause አልያም grand pretext ያስፈልጋል። የመጀመሪያውን ማግኘት ስለማይቻል ብቸኛው አማራጭ የአሜሪካዊያንን እና የአለምን ህዝብ ልብና ጆሮ ጭው የሚያደርግ incident መፍጠር ነው። ለዚህም ይሆን ዘንድ ዲክ ቼኒና ዶናልድ ራምስፊልድን የመሣሠሉ Neu-Conservatives-ን ያቀፈ "Project for New American Century" የተሰኘ ኢ-መደበኛ ድርጅት የአሜሪካን global full spectrum dominance ለማስቀጠል የግድ "The New Pearl Harbor" ሊኖር እንደሚገባ በ1999 ዓ.ም በ50 ገፅ አስገራሚ ፅሁፉ ጠቅሶ ነበር። ከሁለት አመት ባነሰ ጊዜ ውስጥም ይኸው ኃይል ጆርጅ ዊሊያም ቡሽን ከፊት በፕሬዝደንትነት በማሰለፍ የሀገሪቱ መሪ ሆኖ ብቅ አለ።
"The New Pearl Harbor" የመፍጠሪያው ካርድ ደግሞ ለዘመናት የሲ.አይ.ኤ. ተልዕኮ አስፈፃሚ ሆኖ ሲያገለግል የኖረው ፅንፈኛ እስላማዊ ቡድንን ወጥመድ ውስጥ በማስገባት የሚሰራ ድራማ ነው።
ይህ ፅንፈኛ እስላም ቡድን ሶቭየት አፍጋኒስታንን ስትወርር በሳዑዲዓረቢያ እና በሲ.አይ.ኤ. እየተመለመለ ከአፍጋኒስታን ተዋጊዎች ጎን በመቆም የተፋለመ፤ በኋላም ሲ.አይ.ኤ በራሱ አውሮፕላን እያመላለሰ ዩጎዝላቪያን ለመበተን በቦስኒያና በኮሶቮ ጦርነት ያሳተፈው ኃይል ሲሆን (ዶክተር አይማን አልዘዋሪ ክሮሺያ ውስጥ ሲ.አይ.ኤ ቢሮ ከፍቶለት ዘመቻውን ይመራ እንደነበር ልብ ይሏል) ይህ ኃይል በአሜሪካኖቹ አይን expendable የሚሆንበት ጊዜ ስለደረሰ በቅፅበት ከወዳጅነት ወደ ጠላትነት፣ ከቤተኛነት ወደ አሳዳጅ-ተሳዳጅነት ተቀየረ። እነ ምናላቸው ስማቸው እንደሚያሰሙት ባዶ ቀረርቶ ይህ ቡድን የሚያደርገው በተለይም በመሪው ኦሳማ ቢን ላደን የሚሰሙ ፉከራዎች ለአሜሪካ መንግስት ቀጣይ ወጥመድ Clean Alibi የሚፈጥር ነበር። "አሸባሪዎች አደጋ ደቅነውብናል" የሚለውን ፕሮፓጋንዳ ለማስተጋባት ጥሩ ማሳያ ሆኖ አገለገለ። በመጨረሻም የአሜሪካው Deep State በሴፕቴምበር 11, 2001 ዓ.ም በኒዮርክ twin towers እና በቨርጂኒያ የፔንታገን ህንፃ ላይ ጥቃት የሚመስል በድራማ የታጀበ አሳዛኝ ክስተት ፈፀመ፣ አስፈፀመ። የ PNAC አባል ሆነው "The New Pearl Harbor" ሲሉ የነበሩት ዲክ ቼኒና ዶናልድ ራምስፌልድ የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝደንትና የአሜሪካ የመከላከያ ሚንስትር ሆነው በተግባር አስፈፀሙት። አሁን ጦርነት የማስጀመሪያው Casus Belli ( 'ኬሰስ ቤላይ' ) እውን ሆኗል። ከዚህ በኋላ የሚቀረው ሊበሉ ያሰቧቸውን ሀገራት እየመረጡ መውረር ነው። አፍጋኒስታን ቀደመች፣ በኋላም ዲክ ቼኒ የ PNAC አባል እያለ "Iraq is the Prize" ሲላት የነበረችው ኢራቅ በሶስት ሳምንት ጦርነት ተፈታች። የሽግግር መንግሥቱ ሲመሰረት የመጀመሪያ ስራው ያደረገው የቀድሞውን የ Petro-Dollar ስምምነት restore ማድረግ ነበር። ሳዳም ከወራት በኋላ ተያዘ፣ በአሰልቺ የፍርድ ቤት ድራማ ሲሰቃይ ቆይቶ በመጨረሻም አንገቱ ለገመድ ሲሳይ ሆነ። ቀሪው የአረብ ምድር "ሳዳምን ያየህ ተቀጣ" ተባለ። ጋዳፊም ለአመታት የሰበሰበውን የዩሬኒየም yellow cake እና መሰል የቤተሙከራ ቁሳቁሶቹን በመርከብ አስጭኖ ለአሜሪካ ላከ፤ ኮንዲም (ኮንዶሊዛ ራይስ) ትሪፖሊ ድረስ ተጉዛ የጋዳፊ እንቁ እንግዳ ሆነች። ከአምስት አመታት በኋላ ጋዳፊም የአሜሪካ ሰለባ እንደሚሆን አለማወቁ ለጊዜው ሠላም ያገኘ መሰለው።
* ሁሌም Grand pretext ስታዘጋጅ ፥ ሌሎች ፈፅሞ ሊጠረጥሩህ ከማይችሉበት አልያም "ራሱማ በዚህ መጠን ራሱን ሊጎዳ አይችልም" በሚል እንዲጠራጠሩ በሚያስችል ሁኔታ ነው። የአሜሪካ Deep State The twin towers እና ፔንታገንን ኢላማ ሲያደርግ መልዕክቱ ብዙ ነው። The Twin Towers የአሜሪካ Economic Might መገለጫ symbols ሲሆኑ ፔንታገን ደግሞ የ Military Might Symbol መሆኑን እያንዳንዱ አሜሪካዊ ጠንቅቆ ያውቀዋል። የእነዚህ ህንፃዎች መመታት እያንዳንዱ አሜሪካዊ ለመሪዎቹ Blank Cheque ለመስጠት አቅም እንደሚሰጥ ያውቁታል። ሲቀጥልም the vast majority-ው ይህ ጥቃት an inside job ነው ብሎ ለማመን ይቸገራል። የአረቦቹ ባዶ ድንፋታና ፉከራም በቀላሉ ጣቶች ኸደ እነሱ እንዲቀሰር ምክንያት ሆኗል።
የኦሮሙማው መንግስትም ግርማ የሺጥላ ዋነኛ ተላላኪ ባንዳው እንደሆነ ያውቀዋል። "እጁን በእጁ አይቆርጥም" በሚያስብል ደረጃ የኦሮሙማው መንግሥት ግርማ የሺጥላን አይገድልም እንዲባልም ምቹ ነው። በአንፃሩ የእነ ምናላቸው ሰሞንኛ ግርማ የሺጥላን በሚዲያ ማብጠልጠላቸው ለኦሮሙማው መንግሥት Clean Alibi የፈጠረ ነው። ከዚህ በኋላ ነገሩን የምንመዝነው በሶስት መሠረታዊ ሚዛኖች ነው፦ Motive, Opportunity and Means‼
1. Motive
* motive እና bare-wish-ን በቅጡ መለየት የተሳናቸው "ተንታኞች" ነገሮችን ሲያደበላልቁ በእጅጉ ታዝበናል።
Motive ያላቸውን አካላት ስንመዝን ሁሌም ወደ ህሊናችን ቀድሞ መምጣት ያለበት ጥያቄ Cui bono (who benefits) የሚለው ነው። የአማራን ወጣት በማሳደድ ረገድ የኦሮሙማው መንግስት በፈረስነት የሚጋልበው ብአዴንን እንደ ድርጅት፤ ደመቀ መኮንን፣ ተመስገን ጥሩነህ፣ ብናልፍ አንዷለም፣ መላኩ አለበል፣ አገኘሁ ተሻገር፣ ይልቃል ከፋለ፣ ሰማ ጥሩነህ፣ ..........ወዘተ የተባሉ ተላላኪዎችን ደግሞ በመሪነት በመጠቀም ነው። ከዚህ ሁሉ ስብስብ ውስጥ የአንዱ ግርማ የሺጥላ መገደል የአማራን ወጣት መሳደድ እንደማያቆመው ግልፅ ሆኖ ሳለ፥ የአማራ ወጣት አንዳችም የተለየ ጥቅም በማያገኝበት ሁኔታ ግርማ የሺጥላ የተባለ ተላላኪን የመግደል የተለየ motive ሊኖረው አይችልም። የአማራ ወጣት ግርማ የሺጥላን በተለየ ሁኔታ የመግደል "Motive አለው" የሚል አካል ቢኖር እንኳ፥ የአማራ ወጣት ይህንን ለመፈፀም የሚያስችል በቀጣይ የምናያቸውን Opportunity and Means የሉትም‼
ከዚያ ይልቅ Chaos Fermentation-ንን እንደ way of governance የሚያየው ፋሽስታዊው የኦሮሙማ መንግሥት በአማራ ህዝብ ላይ ሊፈፅም አሰቦት ለነበረውና አሁን በአዋጅ እየተገበረው ላለው ወረራና መጠነ-ሰፊ ወታደራዊ ጥቃት፥ የአማራን ወጣት በፅንፈኛ ብሔርተኝነት መፈረጅና ማሳየት ግድ ይለዋል። ለዚህም ሲባል Grand pretext fabricate ማድረግ ይኖርበታል። የአማራ ወጣት የብሔርተኝነት ፅንፍ ጫፍ መርገጡን ማሳያና አደገኝነቱን ማመሳከሪያ ለማድረግም የራሱን "The New Pearl Harbor" መፍጠር ይኖርበታል። በዚህ ረገድ ራሱን እንዳይጠረጠር ለማድረግ ከራሱ ታማኝ አሽከሮች መካከል አንዱን በብላሽ ይሰዋዋል። ስለዚህ ከዚህ ትርፍ አንፃር የኦሮሙማው ፋሽስታዊ መንግስት hot motive አለው ማለት እንችላለን።
2. Opportunity
======== ይቀጥላል =======
Publisher’s note: views in the article reflect the views of the writer, not the views of TBF Blog Chanel
To Publish Article On TBF, please send submission to bitew@2tbf.org for consideration. Join the conversation. Follow us on twitter: https://twitter.com/BTisase
Facebook: https://www.facebook.com/btisase
Instagram: https://www.instagram.com/tisase71/?hl=en
LinkedIn: https://www.linkedin.com/in/bitew-t-03ba4827/
Pinterest: https://www.pinterest.com/tbfblog/ to get the latest Amhara news updates regularly. To share information or send a submission, use bitew@2tbf.org
Comments