ዐማራን ወክሎ ከወያኔ ጋር ስለሰላምም ሆነ ስለትጥቅ ትግል አልፎም ስለመንግሥት መሥረታ መነጋገር ፈጽሞ አይቻልም፤ ዐማራ የተጨፈጨፈው በሦስት ዓመት ዕድሜ ውስጥ ብቻ አይደለም። በ17 ዓመት የወያኔ የሽፍተነት ዘመን፣ 27 ዓመት የወያኔ የመንግሥትነት ዘመን ወደኋላ ተጨምሮ ነው። ከውያኔ ጋር ሰላምን ወይም ትጥቅ ትግልን እናደርጋለን የሚሉ ሁሉ ውሾች ናቸው። "ውሻ ወደ ትፋቱ ይመለሳል" በምሣሌ 26፤11 እና 2ኛ ጴጥሮስ2፤22 የተጠቀሰውን መጽሐፋዊ ዘገባ በማንበብ ከውያኔ ጋር የመከሩትን የውሾች ባህሪ ለይቶ መረዳት ነው። ምስሉ ጸሃፊውን አይወክልም 1ኛ. የዐማራን ሕዝብ የመደብ ጠላት አድርጎ ወያኔን በደደቢት የመሠረተውና 17 ዓመት በትጥቅ ትግል 27 ዓመት በመንግሥትነት በደምሩ 44 ዓመት ከሰባት ሚሊዮን በላይ ዐማራን ሕዝብ ያለማቋረጥ ያስጨፈጨፈ፣ ርስቱን የነጠቀ በጀምላ የገደለ ያፈናቀለ፣ የትግራይን ሕዝብ ከኢትዮጵያዊ ቀዳሚ ሕዝብነቱና ማንነቱ ያስከዳ ስብሐት ነጋ ፤ 2ኛ. ከዐማራ ሕዝብ ይልቅ የሱዳን ሕዝብ ይሻለናል ብሎ በማይካድራ በጭና ዐማራን በከፍተኛ መራር በሆነ ጭካኔ ያስጨፈጨፈው፣ በመጨረሻ ተረጋግቶ መኖር ሲችል ዕቅድና ዓላማ በሌለው ጦርነት አንድ ሚሊዮን የትግራይ ወጣት ያስጨፈጨፈ፣ የትግራይን ሕዝብም ሆነ የዐማራን ሕዝብ አዘቅት ውስጥ የከተተ ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ፤ 3ኛ. የወያኔ ተሿሚ ሆኖ የዐማራን መሬት ፀገዴና ጠገዴ እያለ እየከፋፈለ ለወያኔ ያስረከበ፣ የግጨውን መሬት ለወያኔ በችሮታ ፈርሞ የሰጠ፤ እነ ዶክተር አባቸው ለማስገደል ቅድመ ሁኔታዎችን ከአመቻቸ በኋላ ወደ አሜሪካ ሀገር ሾልኮ ወጥቶ ከተገደሉ በኋላ ተመልሶ ጥቁር ለብሶ የዓዞ እንባ ሲያነባ ሲመጻደቅ የነበረ የሕወሀትም ሆነ የብልጽግና ቀንደኛና ፊ...
ከዚህ መከፋፈል ነፃ ሆነን ፊትለፊት እየወረረ : እየገደለን: ያለውን የጋራ ጠላታችንን ልናሸንፈው የምንችለው ብአንድነት ብቻ ነው:: ሻ/ቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ ሻ/ቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ በምናየው ታላቅ የፋኖ ትግል የዲያስፓራ ትልቁ ስራ ገንዘብ መስብስብ ነው:: እሱም እየቀዘቀዘ ሄዷል:: ጦርነቱን ያራዝምነው እኛው ነን:: ይህ ደግሞ ትልቁና ዋናው የጠላት ስትራተጂ ነው:: ጦርነቱን ማራዘምና ከአማራ ምድር እንዳይወጣ በማድረግ: ፋኖን በመከፋፈል አዳክመዋለሁ ! እበትነዋለሁ ! የሚል የአቢይ አህመድ ትልቁ የወቅቱ ስትራተጂ መሆኑን ተረድተናል::: በዚህም ምክንያት በአጠረ ጊዜ ሊጠናቀቅ የሚችለውን ትግል ዲያስፓራ በምቀኝነት: በቅናት: በሌለ ስልጣን ላይ በመፋተግ: በተቀጣሪነት: በጠባብ አስተሳስብ: ትግላችንን ወደኋላ በመጎተትና እንዲራዘም ብሎም እንዲዳከም በማድረግ ታሪካዊ ወንጀል እየስራ ነው:: ከዚህ መከፋፈል ነፃ ሆነን ፊትለፊት እየወረረ : እየገደለን: ያለውን የጋራ ጠላታችንን ልናሸንፈው የምንችለው በአንድነት ብቻ ነው:: አሸናፊነት ትብብርና የጋራ ስትራተጂ ይጠይቃል:: የተግባር ዲያስፓራ እንሁን:: አማራን እንደ ህዝብ ኢትዮጵያንም እንደ ሀገር ለማዳን ዋናው መሳሪያችን አንድነት ነው:: በውስጣችን ያለውን ልዩነት በመጠቀም አገራችንን ለማጥፋት: በአካባቢያችን ያለውን የሀይል አሰላለፍ ስንመለከት ፍፁም ፍፁም አደገኛ መሆኑን እንገነዘባለን:: በዲያስፓራ መጨቃጨቅና መዘላለፍ እንደ ባህልና እንደ ትልቅ የጦርነት ስትራተጂ ተደር...