Skip to main content

"ከአሁን በሆላ ፋኖ ወደ አንድነት መምጣት አለባቸው የሚባለው አካሄድ አይሰራም" :: በወዳጄ/ቤተ አማራ ወሎ

ከአሁን  በሆላ  ፋኖ  ወደ  አንድነት    መምጣት  አለባቸው  የሚባለው  አካሄድ  አይሰራም::  ክህደት   ከተፈፀመ  በሆላ  አንዱ  ቡድን  ከሌላው  ስር  ሆኖ  ይቀጥላል  ማለት  የማይቻል   ነው::  ምክኒያቱም

1ኛ:- 27  ቀን  ቁጪ  ብለው   መክረዋል :: እያንዳንዱ  አደረጃጄት  ሰነድ  ፅፈው  አቅርበዋል::  በቀረበው  ሰነድ  ላይ  ከፍተኛ  ውይይት  ተደርጎበት  የሚወድቀው  ወድቆ  የሚፈለገው  ፀድቋል::ቃለ  መሀላ  ፈፅመው   ወደ  ምርጫ   ለመግባት  ተስማምተዋል:: እጃቸውን  አውጥተው   ከመረጡ  በሆላ    ግን    "ጨዋታ  ፈረሰ  ዳቦ  ተቆረሰ"   የሚል  የህፃን  ልጂ  ጨዋታ  ውስጥ  መግባት   የአማራን  ህዝብም  ሆነ  የፋኖን  ትግል  መናቅ  ነው:: ይህ  አልበቃ  ብሎ   "ምርጫው  ከኛ  እውቅና  ውጪ  ነው  እኛ  አናውቀውም"  የሚል   የውሸት    የህፃን  ልጂ  ፕሮፓጋንዳ   እንዲሰራጪ  አድርገዋል::ከዚህ  በሆላ   ይህ  ቡድን  የታላቁ  እና  የጠቢቡ   የአማራ  ህዝብ  መሪ  ነኝ    ብሎ   አይኑን   በጨው   አጥቦ  ለመምጣት  እንዴትስ  ይደፍራል ????  

የድምጽ ቅንብሩ ጸሃፊውን አይወክልም።


 2ኛ:- የፋኖ  ወታደራዊ  ጦር  ዋና  አዛዢ   የሆነው  ሻለቃ  ዝናቡ  የራሳቸውን   ድክመት  እና  ሴራ  በአማራ  ህዝብ  ላይ  ለማሸከም   የአማራን  ህዝብ  በጂምላ    ይህ   "ጎጃም  ጠልነት  ነው"   ብሎ  ከወነጄለ  በሆላ   ይቅርታ  ሳይጠየቅበት   በጋራ  ለአንድ  አላማ  እንዴትስ     መስራት  ይቻላል???  የአማራ   ጪምብላቸውን  አውልቀው  እንዴትስ  በመቅፅበት  ወደ  ጎጣቸው   ተወርውረው  ሊገቡ  ቻሉ???  አጄንዳቸው   እንዴትስ  የጎጥ  አጄንዳ  ሊሆን  ቻለ??? ወደ  ትግሉ  የገቡትስ  ለጎጥ  አላማ  ነወይ??  

 3ኛ:-  ይህ  ቡድን  በዲያስፖራ   ቃል  አቀባያቸው   አማክይኚነት    ሚስተር  X ካልተመረጠ   አማራነታችንን  እንተዋለን    በማለት  የጎጃምን  አማራ  ከሌላው  ወንድሞቹና  እህቶቹ  ለመለየት  ከፍተኛ  ስራ  ከተሰራ  በሆላ   እንዴት  አብሮ  መስራት  ይቻላል??

 4ኛ:-   ከሰፈራቸው  ውጪ  ያለውን  አማራ   መጤ  :  ሰፋሪ  :  አማራዊ  ስነ  ልቦና  የሌለው  : በመጤ  አንመራም  :  የሚል  ፋሺስታዊ     ፕሮፖጋንዳ    ከተሰራጨ  በሆላ  እንደ  አማራ  ከዚህ  ፋሺስት  ቡድን  ጋር  በጋራ   መቀጠል  ይቻላል  ወይ???

የወሎ/ ቤተ አማራ ;  የጎንደር :  የሸዋ ;  እና  30 ሚልዮን  ከክልሉ  ውጪ  የተወለደን  አማራ  መጤ  ነው  የአማራ  ስነልቦና  የለውም  በነሱ  አንመራም  ያለን  አካል  እንዴትስ  አንደ  አማራ   መቀበል  ይቻላል???? ይህ  ባእዴናዊ  እና   ኦነጋዊ  አካሄድ  አይደለም  ወይ??  ከሰፈሬ  ውጪ  ያለውን  አማራ  የምንታገልለት  ሳይሆን  የምንታገለው  ነው  ማለትስ  አይደለም ወይ??? ይህ  ብአዴናዊ  መርህ  ለምን  ተፈለገ???  

 ይህ  ፋሺስት  ቡዲን   ሌላውን  የአማራ    ህዝብ  እኛና  እነሱ ብሎ  identify   እድርጎ  አስቀምጧል::  ይህ  ማለት  already  የመጄመሪያውን   የጄኖሳይድ    መስፈርት  አሞልተዋል:: ይህ  ቡድን  እድሉን  ቢያገኝ  እኛና  እነሱ  ብሎ  identify ያደረገውን  አካል  ነው    መጄመሪያ  የሚያጠፋው::   ከአብይ  አህመድ  ኦነጋዊ  ኦሮሙማ  የዳነውን  አማራ   እንደገና  በዚህ  ፋሺስት  ቡድን  ላለመጥፋት  ምን  ጋራንቲ  አለን???? ይሰመርበት  ይህን  ፋሺስታዊ   አካሄድ  በቃላሉ  አናየውም  በቀላሉ  አናልፈውም!!!!

በመሆኑም    ይህ  ቡድን   በአማራ  ህዝብ  ላይ  ቀላል  የማይበል  የስነ  ልቦና  ቀውስ    አድርሷል    እርስ  በርሱ  እንዲወዛገቡ  አድርጏል:: በአስራጨው  ውዢንብር  እና  ፋሺስታዊ    ንግግር    መሰረት   በማህበረሰባችን    ላይ  ብዙ   ጉዳት  ደርሷል:: የስነ  ልቦና  ቀውስ  አስከትሎል::  ***** ይህን   የስነ  ልቦና  ቀውስ  ለመጠግን   የአማራን  ህዝብ   በይፋ  ይቅርታ  በመጠየቅ    ልብ  የሚያሞቅ  ሁሉንም  የአማራ  ህዝብ  አንድ  የሚያደርግ  speech ማድረግ    አለበት::

 ይቅርታ  ከተጠየቀ    እና  የህዝባችንን  አንድነት  ካረጋገጥን  በሆላ   የመጣንበትን  የትግል  ጉዞ  ገምግመን ሁለቱ  አደረጃጄቶች  በጋራ  ለመስራት   የጋራ  ስትራቴጂክ  መንደፍ  ያስፈልጋል::

Comments

Popular posts from this blog

ስርነቀል ለውጥ ማምጣት የአማራ ብሄርተኝነት የህልውና ትግል ብቸኛ ግብ ነው። በ Alen Kassahun

ምስሉ ጸሃፊውን አይወክልም፡፤ ከ50 አመታት በላይ የተተከለውንና በተግባር እየተፈፀመ ያለውን አማራን ማጥፋትና ኢትዮጵያን ማፍረስ ከስሩ በመንቀል #4ኪሎን ተቆጣጥሮ ስርነቀል ለውጥ ማምጣት የአማራ ብሄርተኝነት የህልውና ትግል ብቸኛ ግብ ነው። ፋኖ በሚያደርገው የህልውና ትግል አማራ ጠልነት የወለደውን የአማራን ዘር ማጥፋት፤ ማፅዳት፤ የሰባዊ መብት ጥሰትና አገር ማፍረስ አለምአቀፍ ወንጀል ከስሩ ነቅሎ ሊቀብረው #በዋዜማው ላይ እንገኛለን። ስለሆነም ፋኖ እያደረገ ያለውን የህልውና ትግል #በድል እንዳይቋጭ  በድርድር፣ በእርቅና በምክክር ሰበብ የፋኖን ድል ለመቀልበስና ለመንጠቅ ከአሜሪካ እስከ አዲስ አበባና መቀሌ ድረስ በሚሸረብ ሴራ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ፤ በስልታዊ አማራነትም ሆነ በአማራ ጠልነት የተሰለፉ ቅጥረኞች ደፋ ቀና እያሉ እንደሚገኙ ግልፅ ነው። ፋኖ #አራት ኪሎን በመቆጣጠር ስርነቀል ለውጥ ለማወጅ በድል ዋዜማ ላይ ሆኖ እያደረገ ያለውን የመጨረሻውን ትንቅንቅ ለማሰናከልና ድሉን ለመሸጥ ተቀጥራችሁ ስለ ድርድር፣ ሽግግር፣ እርቅ፣ ውይይትና በመሳሰሉ አጀንዳዎች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ እየሰሩ የሚገኙ ቅጥረኞችን ከቀጣሪዎች እኩል ማሸነፍና ማስወገድ የህልውና ትግላችን ብቻኛ አማራጭ መሆኑ ለማንም ግልፅ ሊሆን ይገባል። ስለሆነም የዜግነት ፓለቲካ አቀንቃኝ የ3ኛ ወገን ቅጥረኞችን ከጀርባው አሰልፎ የአማራን ብሄርተኝነት የማድፈቅ አጀንዳቸውን አዝሎ ከአማራ ህልውና ትግል መሀል የተገኘው #እስክንድር ነጋ ከአማራ ህልውና ትግል ጓዙን ጠቅልሎ እንዲወጣ ማድረግ ለነገ የሚባል አይደለም። የእስክንድር ነጋ #የእየሱስ ክርስቶስነት ገፀ ባህሪ በሂደት እየተገፈፈ መምጣት አማራ ጠል ሀይሎችን ወደ እቅድ ሁለት ሴራ እንዲገቡ እያስገደደ በመሆኑ የአማራ ብሄርተኛ #እስክንድ...

አለም አቀፍ የፋኖ ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ነኝ የሚለው ቡድን ዓላማ ምንድነው ? በወንድወሰን ተክሉ

ይህ ምስል ጸሃፊውን አይወክልም! «...አማራ ለ450 ዓመታ መንፈሱ የተሰበረ ገበሮ ሕዝብ ነው..» ሀብታሙ ተገኝ (ፕ/ር) « እኔ እስክንድር  የአማራ ሕዝብ ከደረሰበት የህልውና አደጋ እኩል የሚሆን ዓላማ አለው ብዬ አላምንም» አቻምየለህ ታምሩ፤ አለም አቀፍ የፋኖ ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ነኝ የሚለው ቡድን ዓላማ ምንድነው ? በወንድወሰን ተክሉ እራሱን አለም አቀፍ የፋኖ ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ነኝ የሚለው ቡድን የዙም ውይይት ፕሮግራም ክፍል ሁለትን የተመለከተ ምልክታ:- ባለፈው  ወር ብቻ ሳይሆን ባለፈው ዓመት ዴሴምበር 2023 ( ዛሬ ጃንዋሪ 1 ቀን 2024 ነን)  እራሱን አለም አቀፍ የፋኖ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ብሎ የሚጠራው ቡድን «ጸረ አማራ ኢትዮጲያዊነት» በሚል አርእስት ስር ሀብታሙ ተገኝ (ፕ/ር) ዋና ተናጋሪ ተጋባዥ የሆነበትን  የዙም ውይይት አካሂዶ የነበረ ሲሆን የዚህ ውይይት ክፍል ሁለት  ባሳለፍነው ወር ዴሴምበር 23ቀን በማዘጋጀት አቻምየለህ ታምሩና ሀብታሙ ተገኝ (ፕ/ር) ተናጋሪ እንግዳ በማድረግ አካሂዷል። በእርግጥ  ከዚህ ከሁለተኛው የውይይት ፕሮግራም በፊት በተክሌ ይሻው በኩል የዙም ሊንክ ተልክሎኝ በሰዓት ጥበት ምክንያት መገኘት ባልችልም ዛሬ ግን በቻናላቸው ላይ የጫኑትን ይህን ክፍል ሁለት ውይይት ከተመለከትኩ በኋላ ይህን ምልክታዬን  አንባቢው ሊረዳ በሚያስችል መልኩ አንድ ሰዓት ከሰላሳ ደቂቃ የፈጀን ውይይት ይዘት በመጭመቅ እንደሚከተለው አቅርቤያለሁ። ይህ ምስል ጸሃፊውን አይወክልም! 1ኛ - ውይይቱን አዘጋጅን ማንነት በተመለከተ፦  አለም አቀፍ የፋኖ ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ባለፈው መስከረም ወር ላይ  በጌታቸው በየነ ሰብሳቢነት ተመሰረትኩ ብሎ እራሱን ያስተዋወቀ ሲ...