Skip to main content

የማንቂያ ድዎል‼️ በ Alen Kassahun

የአማራ ህልውና ከመጥፋት ድኖ ዘላለማዊነቱ የሚረጋገጠው፤ ሌሎች ኢትዮጵያውያን ነገዶች ተጨፍጭፈው ከመጨፍለቅና ከመጥፋት የሚድኑት እና ኢትዮጵያ ከመፍረስና መበታተን ድና ታላቋ ትግራይና ታላቋ ኦሮሚያ በአማራ #መቃብር በኢትዮጵያውያን አፅመርስት ላይ መወለድ ቅዠት የሚሆኑት #ፋኖ አራት ኪሎን በቀጥታ በአሸናፊነት ተቆጣጥሮ  #ስርነቀል ለውጥ በኢትዮጵያ ምድር ሲያውጅ ብቻና ብቻ ነው።

ፋኖ በአሸናፊነት 4ኪሎን በመቆጣጠር ስርነቀል ለውጥ ከማወጅ #በፊት የሚታሰብ ውይይት፣ ድርድር፣ የሽግግር መንግስት ምስረታ ወዘተረፈ የፋኖን ግብ በማሰናከል የአማራን ህልውና ትግል ከአሸናፊነት ለማጨናገፍ የሚቆመር ሴራና ድራማ ነው‼️ 

ይህን የአማራ ህልውና መዳኛ ብቸኛ መርህ በስነ ልቦናችንና አዕምሮአችን በማስረፅ ቀጥዬ ያቀረብሁትን የማንቂያ ድዎል ተግባራዊ እናድርግ‼️

ዘመነ ካሴ እያቀፈ የሚያስተዋውቃቸው የብአዴን ልጆች እነ #አስረስ፣ #ማርሸትና ቡድናቸው በተለያየ ክፍለ አገር የሚገኙ ግብረአበሮቻቸውን አስተባብረው የፋኖ አንድነት መሰረትን ለማለት ማታለያ ድራማቸውን #በመጨረስ ላይ ይገኛሉ።

ፎቶው ጸሃፊውን አይወክልም!


አስረስ ማረ ዳምጤ በአስተባባሪነት የሚመራው ይሄ #የብአዴን ፋኖ ቡድን ግልፅ አላማው የፋኖ አንድነት መሰረትን በማለት #የሰላም ኮሚቴ ተብሎ በብአዴን ከተሰየመው የሰለጠኑ ካድሬዎች ስብስብ ጋር በአጠቃላይ የፋኖ አንድነት በሚመስል ስም #ለውይይትና ቀጥሎም #ለድርድር ለመሰየም አማራውን ለማታለል የሚያስችለው ሴራ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ እንደሆነ ተደርሶበታል። 

ስለዚህ መላው የአማራ ህዝብና የታጠቀው ፋኖ በሙሉ ፋኖ #4ኪሎን በመቆጣጠር ስርነቀል ለውጥ ለማወጅ የሚያደርገውን የመጨረሻ ትንቅንቅ በዋዜማው ለማሰናከል የሚሸረብ #ፀረአማራ ተልኮ አስፈላጊውን እርምጃ በመውሰድ #ለማክሸፍ ከፍተኛ ክትትል ሊደረግባቸው ይገባል።

"ይናገራል ፎቶ" የሚባለው አባባል ከመናገር አልፎ እየጮኸ ሲመሰክር ከታች ባሉ ፎቶዎች ማረጋገጥ ይቻላል‼️


አማራነት ያሸንፋል‼️

ፋኖ ይነግሳል‼️

Comments

Popular posts from this blog

"ከአሁን በሆላ ፋኖ ወደ አንድነት መምጣት አለባቸው የሚባለው አካሄድ አይሰራም" :: በወዳጄ/ቤተ አማራ ወሎ

ከአሁን  በሆላ  ፋኖ  ወደ  አንድነት    መምጣት  አለባቸው  የሚባለው  አካሄድ  አይሰራም::  ክህደት   ከተፈፀመ  በሆላ  አንዱ  ቡድን  ከሌላው  ስር  ሆኖ  ይቀጥላል  ማለት  የማይቻል   ነው::  ምክኒያቱም 1ኛ:- 27  ቀን  ቁጪ  ብለው   መክረዋል :: እያንዳንዱ  አደረጃጄት  ሰነድ  ፅፈው  አቅርበዋል::  በቀረበው  ሰነድ  ላይ  ከፍተኛ  ውይይት  ተደርጎበት  የሚወድቀው  ወድቆ  የሚፈለገው  ፀድቋል::ቃለ  መሀላ  ፈፅመው   ወደ  ምርጫ   ለመግባት  ተስማምተዋል:: እጃቸውን  አውጥተው   ከመረጡ  በሆላ    ግን    "ጨዋታ  ፈረሰ  ዳቦ  ተቆረሰ"   የሚል  የህፃን  ልጂ  ጨዋታ  ውስጥ  መግባት   የአማራን  ህዝብም  ሆነ  የፋኖን  ትግል  መናቅ  ነው:: ይህ  አልበቃ  ብሎ   "ምርጫው  ከኛ  እውቅና  ውጪ  ነው  እኛ  አናውቀውም"  የሚል   የውሸት    የህፃን  ልጂ  ፕሮፓጋንዳ...

የጋራ ጠላታችንን ልናሸንፈው የምንችለው ብአንድነት ብቻ ነው:: ሻ/ቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ

ከዚህ መከፋፈል ነፃ ሆነን ፊትለፊት  እየወረረ : እየገደለን: ያለውን የጋራ ጠላታችንን ልናሸንፈው የምንችለው ብአንድነት ብቻ ነው:: ሻ/ቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ ሻ/ቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ በምናየው  ታላቅ  የፋኖ ትግል የዲያስፓራ ትልቁ ስራ ገንዘብ መስብስብ ነው:: እሱም እየቀዘቀዘ ሄዷል:: ጦርነቱን ያራዝምነው እኛው ነን:: ይህ ደግሞ ትልቁና ዋናው የጠላት ስትራተጂ ነው:: ጦርነቱን ማራዘምና ከአማራ ምድር እንዳይወጣ በማድረግ: ፋኖን በመከፋፈል አዳክመዋለሁ ! እበትነዋለሁ ! የሚል የአቢይ አህመድ ትልቁ  የወቅቱ ስትራተጂ መሆኑን ተረድተናል::: በዚህም ምክንያት በአጠረ ጊዜ  ሊጠናቀቅ የሚችለውን  ትግል  ዲያስፓራ በምቀኝነት: በቅናት: በሌለ  ስልጣን  ላይ በመፋተግ: በተቀጣሪነት: በጠባብ አስተሳስብ: ትግላችንን ወደኋላ  በመጎተትና  እንዲራዘም ብሎም እንዲዳከም በማድረግ ታሪካዊ ወንጀል እየስራ ነው:: ከዚህ መከፋፈል ነፃ ሆነን ፊትለፊት  እየወረረ : እየገደለን: ያለውን የጋራ ጠላታችንን ልናሸንፈው የምንችለው በአንድነት ብቻ ነው::  አሸናፊነት ትብብርና  የጋራ ስትራተጂ ይጠይቃል:: የተግባር ዲያስፓራ እንሁን:: አማራን እንደ  ህዝብ ኢትዮጵያንም እንደ ሀገር  ለማዳን  ዋናው መሳሪያችን  አንድነት ነው:: በውስጣችን ያለውን ልዩነት በመጠቀም  አገራችንን ለማጥፋት: በአካባቢያችን  ያለውን የሀይል አሰላለፍ ስንመለከት ፍፁም ፍፁም  አደገኛ  መሆኑን እንገነዘባለን:: በዲያስፓራ  መጨቃጨቅና መዘላለፍ  እንደ ባህልና እንደ ትልቅ   የጦርነት ስትራተጂ ተደር...

አለም አቀፍ የፋኖ ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ነኝ የሚለው ቡድን ዓላማ ምንድነው ? በወንድወሰን ተክሉ

ይህ ምስል ጸሃፊውን አይወክልም! «...አማራ ለ450 ዓመታ መንፈሱ የተሰበረ ገበሮ ሕዝብ ነው..» ሀብታሙ ተገኝ (ፕ/ር) « እኔ እስክንድር  የአማራ ሕዝብ ከደረሰበት የህልውና አደጋ እኩል የሚሆን ዓላማ አለው ብዬ አላምንም» አቻምየለህ ታምሩ፤ አለም አቀፍ የፋኖ ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ነኝ የሚለው ቡድን ዓላማ ምንድነው ? በወንድወሰን ተክሉ እራሱን አለም አቀፍ የፋኖ ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ነኝ የሚለው ቡድን የዙም ውይይት ፕሮግራም ክፍል ሁለትን የተመለከተ ምልክታ:- ባለፈው  ወር ብቻ ሳይሆን ባለፈው ዓመት ዴሴምበር 2023 ( ዛሬ ጃንዋሪ 1 ቀን 2024 ነን)  እራሱን አለም አቀፍ የፋኖ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ብሎ የሚጠራው ቡድን «ጸረ አማራ ኢትዮጲያዊነት» በሚል አርእስት ስር ሀብታሙ ተገኝ (ፕ/ር) ዋና ተናጋሪ ተጋባዥ የሆነበትን  የዙም ውይይት አካሂዶ የነበረ ሲሆን የዚህ ውይይት ክፍል ሁለት  ባሳለፍነው ወር ዴሴምበር 23ቀን በማዘጋጀት አቻምየለህ ታምሩና ሀብታሙ ተገኝ (ፕ/ር) ተናጋሪ እንግዳ በማድረግ አካሂዷል። በእርግጥ  ከዚህ ከሁለተኛው የውይይት ፕሮግራም በፊት በተክሌ ይሻው በኩል የዙም ሊንክ ተልክሎኝ በሰዓት ጥበት ምክንያት መገኘት ባልችልም ዛሬ ግን በቻናላቸው ላይ የጫኑትን ይህን ክፍል ሁለት ውይይት ከተመለከትኩ በኋላ ይህን ምልክታዬን  አንባቢው ሊረዳ በሚያስችል መልኩ አንድ ሰዓት ከሰላሳ ደቂቃ የፈጀን ውይይት ይዘት በመጭመቅ እንደሚከተለው አቅርቤያለሁ። ይህ ምስል ጸሃፊውን አይወክልም! 1ኛ - ውይይቱን አዘጋጅን ማንነት በተመለከተ፦  አለም አቀፍ የፋኖ ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ባለፈው መስከረም ወር ላይ  በጌታቸው በየነ ሰብሳቢነት ተመሰረትኩ ብሎ እራሱን ያስተዋወቀ ሲ...