ዐማራን ወክሎ ከወያኔ ጋር ስለሰላምም ሆነ ስለትጥቅ ትግል አልፎም ስለመንግሥት መሥረታ መነጋገር ፈጽሞ አይቻልም፤ ዐማራ የተጨፈጨፈው በሦስት ዓመት ዕድሜ ውስጥ ብቻ አይደለም። በ17 ዓመት የወያኔ የሽፍተነት ዘመን፣ 27 ዓመት የወያኔ የመንግሥትነት ዘመን ወደኋላ ተጨምሮ ነው። ከውያኔ ጋር ሰላምን ወይም ትጥቅ ትግልን እናደርጋለን የሚሉ ሁሉ ውሾች ናቸው። "ውሻ ወደ ትፋቱ ይመለሳል" በምሣሌ 26፤11 እና 2ኛ ጴጥሮስ2፤22 የተጠቀሰውን መጽሐፋዊ ዘገባ በማንበብ ከውያኔ ጋር የመከሩትን የውሾች ባህሪ ለይቶ መረዳት ነው።
1ኛ. የዐማራን ሕዝብ የመደብ ጠላት አድርጎ ወያኔን በደደቢት የመሠረተውና 17 ዓመት በትጥቅ ትግል 27 ዓመት በመንግሥትነት በደምሩ 44 ዓመት ከሰባት ሚሊዮን በላይ ዐማራን ሕዝብ ያለማቋረጥ ያስጨፈጨፈ፣ ርስቱን የነጠቀ በጀምላ የገደለ ያፈናቀለ፣ የትግራይን ሕዝብ ከኢትዮጵያዊ ቀዳሚ ሕዝብነቱና ማንነቱ ያስከዳ ስብሐት ነጋ፤
![]() |
ምስሉ ጸሃፊውን አይወክልም |
2ኛ. ከዐማራ ሕዝብ ይልቅ የሱዳን ሕዝብ ይሻለናል ብሎ በማይካድራ በጭና ዐማራን በከፍተኛ መራር በሆነ ጭካኔ ያስጨፈጨፈው፣ በመጨረሻ ተረጋግቶ መኖር ሲችል ዕቅድና ዓላማ በሌለው ጦርነት አንድ ሚሊዮን የትግራይ ወጣት ያስጨፈጨፈ፣ የትግራይን ሕዝብም ሆነ የዐማራን ሕዝብ አዘቅት ውስጥ የከተተ ደብረጽዮን ገብረሚካኤል፤
3ኛ. የወያኔ ተሿሚ ሆኖ የዐማራን መሬት ፀገዴና ጠገዴ እያለ እየከፋፈለ ለወያኔ ያስረከበ፣ የግጨውን መሬት ለወያኔ በችሮታ ፈርሞ የሰጠ፤ እነ ዶክተር አባቸው ለማስገደል ቅድመ ሁኔታዎችን ከአመቻቸ በኋላ ወደ አሜሪካ ሀገር ሾልኮ ወጥቶ ከተገደሉ በኋላ ተመልሶ ጥቁር ለብሶ የዓዞ እንባ ሲያነባ ሲመጻደቅ የነበረ የሕወሀትም ሆነ የብልጽግና ቀንደኛና ፊታውራሪ ኮከብ አገልጋይ የዐማራን ሕዝብ ሲያጨፈጭፍ የኖረ፣ መጨረሻ ላይ ተጠቅመው ሱበቃቸው ስብዕናውን ገፈው በአዋርደው እንደ አሮጌ ቁና ወርውረው የጣሉት ገዱ አንድአርጋቸው፤
4ኛ. ዐማራን በሜንጫ ክፍ ብለህ አንገቱን ዝቅ ብለህ በአቱን ቁረጠው እያለ ሲያውጅ የነበረው እና በኦሮሚያ ክልል በዋናነት ወለጋን ጨምሮ በአርሲና በባሌ ቄሮን እያደራጀ ዐማራን ያስጨፈጨፈ OMN የሚል ሚዲያ ከፍቶ በዐማራ ሕዝብ ላይ ጥላቻን፣ መገለልንና መፈናቀል እንዲደርስበት ያደረገ፤ "ኦሮማራ" የተባለውን ያአድንነት የትግል የለውጥ ኃይል ያፈረሰ በምትኩ ጠላትነትን በስፋት የዘራ፤ የኢትዮጵያ ባንዲራን ያስረገጠ፤ የኦሮሞ ሕዝብ በአደዋ፣ በማይጨው፣ በካራማራ፣ በሱማሌ ጠረፍ ጦርነቶች ሁሉ ወያኔንና ሻቢያን ለመመከት አሥራ ሰባት ዓመት እየተዋደቀ ያቆያትን ሲሞት መግነዙ አድርጎ የተቀበረበትን ባንዲራ ያስረገጠና ከኦሮሞ ወጣት ልቦና ውስጥ የፋቀ፤ ኦሮሚያ ከኢትዮጵያ ውጭ እያለ አውጆ የኦሮሞ ወጣት ሀገሩን በጠላትነት እዲመለከት ያደረገ፤ የዐደዋ በዓል ሲከበር የወጣቱን አዕምሮ ለመቆጣጠር ምንልክ ጡት ቆርጧል እያለ የሐሰት ሐውሎት ሲጎበኝ የነበረ ጀዋር መሐመድ፤
5ኛ. እነ ፐሮፌሰር አሥራት ወልደኢየሱስን ያሳሰሠረ በመጨረሻም ለሕይዎታቸው ሕልፈት ምክንያት ከሆኑት መካከል በግንባር ቀደምነት ተጠቃሽ የሆነ፤ የዐማራን ውሳኝ ፓለቲካ ቅንጅት የትግል ድርጀቶች ከወያኔ ጋር ሆኖ ያፈረሰ፤ የዐማራ ሕዝብ በሚጨፈጨፍባት ምድር ላይ ሠላማዊ ዲሞክራሲያዊ መንግሥት ያለ በማስመሠል ደረጃ በተቃዋሚ ፓርቲ ስም ሳይመረጥ ፓርላማ ገብቶ የሐሰት ፕሮፓጋንዳ ደራማ በመሥራት የዐማራ ሕዝብ መጨፍጨፍ ለዓለም ማኅበረሰብ እንዳይገለጥ መጋረጃ ሆኖ የኖረ፣ የዐማራ የመከራ ዘመን እንዲራዘም ያደረገ መለስ ዜናዊ እራሱ በአደባባይ የመሠከረለት የወያኔ ታማኝ ቀኝ እጅ ልደቱ አያሌው፤
6ኛ. ለቁራጭ መሬት ብለን አንዘምትም በማለት የጎጃምን ወጣት ወደ ወልቃይት እንዳይዘምት ያስተባበረ፤ ጀነራል አሳምነው ፅጌን ሌት ተቀን ጎትጉቶና አዕምሮውን ተቆጣጥሮ ወንድሞቹን እነ ዶክተር አንባቸውን እንዲገድል በከፍተኛ ደረጃ ያነሳሳ ያስገደለ ግንባር ቀደም ተዋናኝ፤ ዐማራን የሠለጠነ የፓለቲካ ሞጋች ኃይልም ሆነ ወታደራዊ ብቃት ያለው የነቃ የሚያደራጅ አመራር እንዳይኖረው በአንድ ቀን በጀምላ ያመከነ ፤ እራሱን ከሕግ ተጠያቂነት ለመሸፈን ጫካ ገብቶ ፋኖ የሆነ እና መንደር ለመንደር እያውደለደለ፤ እሱ ታይቷል በሚባልበት የጎጃም አርሶ አደር ገበሬ በሠፈረበት ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ሁሉ የጎጃምን ሕዝብ ከፍተኛ የድሮን ጭፍጨፋ ሰላባ እንዲሆን ያደረገ፤ በወንድማማች ሕዝብ ጎንደርና ጎጃም መካከል መቃቃር እንዲፈጠር አበክሮ የሠራ፣ ጎንደርን ለሁለት በመክፈል በፈጸመው ወንጀል በቀል ይፈጸምብኛል በሚል በሥጋት የሚመለክታቸው በተለይም በደቡባዊ ጎንደር ክፍል ያሉትን በከፍተኛ ውጪ ገዳይ እየገዛ "እስኳድ" የሚል ስም ሰጥቶ የጎንደር አናብስት ጀግኖችን እየመረጠ የሚያስገድል፣ የጎጃም ቆራጥ ጀግኖችን ከትውልድ ሀገረቸው የሚያሳድድ፣ የዐማራ ፋኖ አንድ ወጥ አመራርና ማዕከላዊ ሰንሰለት እንዳይኖረው "እኔ ካልተመረጥኩ" በሚል ከፍተኛ የሥልጣን ጥማት ከሦስት ጊዜ በላይ የማዕከላዊ ድርጅታዊ ምርጫን ያጨናገፈና የከፋፈለ ዘመነ ካሴ፤
7ኛ. "የትግራይ ሕዝብ ጦርነት ሠርጉ" ነው እያለ ወጣቱን ለጦርነት አነሳስቶ ያስፈጀ፤ በሕዝብ መካከል ልዩነትና እንዲፈጠር በትግራይ ሕዝብ ስም ሚዲያ ከፍቶ ሲቀሰቅስ የኖረ፤ ለትግራይ ሕዝብ መርጃ የተሰበሰበ 250 ሺህ ዶላር አጭበርበሮ የነጠቀ ፣ በራሱ ርዕስት በአባቶቹ መሬት የሰው ሳይቀማ የራሱን ሳይሰጥ የኖረውን የዐማራ ሕዝብ "ተስፋፊ" እያለ ሲያዋርድ የኖረ አሉላ ሌባው፤
8ኛ. ስለቴዎድሮስ መናገር አልችም "እባብን ልቡን ዓይቶ እግሩን ነሳው" ነውና እግዚያብሔር ያሸከመው ጨለማ ይበቀዋለ፤ እንጀራ ነውና ሳያይ ርዮት እያለ፤ ያላየውን እየመሰከረ ይኑር እሱን ተችቸ ከፈጣሪ ጋር አልጣላም ። እነዚህ ተስበስበው በኢትዮጵያ ሕዝብም ሆነ በተለይም በዐማራ ሕዝብ ላይ የመወሰን፣ የመወያየት፣ የመምከርና የመነጋገር አቅሙም፣ ውክልናውም፣ ሞራሉም ሆነ ስብዕናው ፈጽሞ የላቸውም።
በሕግ ይጠየቁ ከተባለ እነዚህ ሰዎች ሕግ ሊጠይቃቸው የሚገባ ወንጀለኞች መካከል ናቸው። እነዚህ ወደፊት በየትኛውም የሀገራችን የፓለቲካ ሕይዎት ውስጥ ምንም ዓይነት ሚና እንዳይኖራቸው ማድረግ አንዱ የትግል መሥመር ሆኖ ሊሠራበት የሚገባ ጉዳይ ነው።
የሀገሪቱ ፓለቲካ መመራት ያለበት ከየትኛውም ወያኔዊ ፓለቲካ ንክኪ ያልኖረው፣ የጠባብ ብሔርተኝነት፣ ክልላዊ ቡድነኝነት የሌለው በሕገ መንግሥታዊ ልውጥ ላይ የተመሠረት ሥር ነቀል ለውጥ ሀገርን የሚመራ ብቃት ያለው ሥልጡን ሕዝባዊ መሠረት የያዘ አዲስ የአመራር ግንዛቤ ስልት የቀየሰ፣ የሕዝብ በሕግ ፊት የተፈጥሮ እኩልነት የሚሰማው፣ የዜግነት መብት ሳይሸራርፍ የሚያስጠብቅ ሕግ ከሁሉ በላይ መሆኑን የሚረዳ ከወንጀል የጸዳ አዲስ የፓለቲካ ኃይል ሲተካ ብቻ ነው።
እውነት ተናግሬ መሞት ከአባቶች የወረስኩት አብሮኝ የሚቀበር ባህሪየ ነው።
ሌባ ሁላ! እኔ የጎደንር ሰው ነኝ! ዐማራ ነኝ ! ኢትዮጵያዊ ነኝ! እውነት ከእኔ ጋር ነው ያለው፤ የማነንም አጨብጫቢነት አልፈልግም። የማንም ማንኛውን እርጥባን አልጠይቅም ምን ታመጣለህ፤ ሀገር አጥፊ፣ ሌባ እና አጭበርባሪ ወንጀለኛ ሁሉ ከሰላም ጋር ምን አገናኘው። "ውሻን ምን አገባው ከእርሻ።
ምንጭ ፡ ሀፌስቡክ መድረክ
Comments