Skip to main content

Posts

“Fano: A living saviour of the Amhara people And the Ethiopian spirit” – Written by Pro. Girma Berhanu, Sweden.

Pro. Girma Berhanu, Sweden "Fano: A living saviour of the Amhara people And the Ethiopian spirit -  ፋኖን እወዳለሁ፥ ፋኖንስ አልጠላ፣  ተኳሽ እወዳለሁ፥ ተኳሽም አልጠላ፣  Introduction  Fano is a historical term used in Ethiopian struggles against injustice and foreign invaders. It is mainly shown as a youth movement that has played a significant role in preserving the concept of Ethiopian nationhood. As a youth group, it has emerged from within the Amhara ethnic group and has features of reminiscent of classical political, religious, or even social movements that drive youthful frustrations into acts of agitation until they achieve a measure of reform. Traditionally, the Fano struggle had focused on fending off attacks against Ethiopia. In recent years, Fano has become a household name and a crucial movement tasked with saving the very existence of the Amhara population as well as the integrity of Ethiopia. In this, it differs from other similar youth movements in the country, whose aim is to dismember th

"ምኗ ላይ ተቀምጣ በሽንቷ ሰፌድ ትሰፋላች":- አዲሱ የአቢይ ካቢኔ አሰያዬም ፤ በሸንቁጥ አየለ

ችግሩ ያለዉ የጎሳ ፖለቲካ ርዕዮተ ፍልስፍናዉ ላይ ነዉ::ኢትዮጵያዉያንን ሀገር አልባ ያደረገዉን የጎሳ ፖለቲካ ፍልስፍና መሰረት ላይ የቆመ ካቢኔ ምንም አይነት መልካም ግለሰቦችን ሰብስብቦ ቢያቅፍ ከቶም የሀገር መድሃኒት አያመጣም:: ሆኖም የዚህ ስርዓት የጥቅም ተጋሪዎች እና እግር አጣቢዎች ይሄን የጎሳ ፖለቲካ አስተሳሰብ የተለያዬ የማስመሰያ መቀባቢያ በመቀባት ጸረ ሰዉ የሆነዉን የጎሳ ፖለቲካ አስተሳሰብ ለማስቀጠል እና ህዝብን ለማምታታት ብዙ ሲዳክሩ ይሰተዋላል::በአዲሱ የአቢይ ካቢኔ አሰያዬም የተከናወነዉ ድራማም ይሄዉ ነዉ:: እከሌ ከኦህዴድ:እከሌ ከብአዴን:እንትና ከአብን : እንቶኔ ከኢዜማ: እንቶኔ ደግሞ ከትግራይ ብልጽግና ተሾሙ እያሉ ብዙ የጥቅም ተጋሪዎች እና የአገዛዙ ሚዲያ ብዙ ይቀባጥራሉ::በደስታም እንኳን ደስ አለህ ይባባላሉ::ኢትዮጵያዉያን ግን አሁንም ሀገር አልባ ናቸዉ:: የኢትዮጵያ የችግር ምንጭ ሁሉ አንድ ነዉ::ይሄዉም የጎሳ ፖለቲካ ፍልስፍና ነዉ::መለስ ዜናዊ የሀገሪቱን ጥፋት ያመጣዉ የጎሳ ፖለቲካ ፍልስፍና በማራመድ ነበር::መለስ ዜናዊ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሆኖ በስሩ ብዙ በግለሰብ ደረጃ መጥፎ የማይባሉ ሰዎችን በካቢኔዉ ዉስጥ ሰግስጎ ነበር:: ሆኖም የመለስ ዜናዊ ካቢኔ እያንዳንዱ የሚመራበት መርህ በጎሳ ፖለቲካ ፍልስፍና እና ቀመር ስለሆነ የሚሰሩ ስራዎች ሁሉ በዚሁ መርዛማ ህሳቤ ዙሪያ የሚሽከረከሩ ነበሩ:: አሁንም አቢይ የሾማቸዉ ሰዎች መጥፎ ናቸዉ ጥሩ ናቸዉ የሚለዉ አይደለም ጥያቄዉ:: ወይም ደግሞ ሰዎች ከዬትኛዉ ፓርቲ ተመርጠዉ ተሾሙ አይደለም ጥያቄዉ:: አቢይ የሚመራበትም የፖለቲካ ፍልስፍና እንደ መለስ ዜናዊ ሁሉ የጎሳ ፖለቲካ ፍልስፍና ነዉና ያዉ ዉሃ ቢወቅጡት እንቦጭ ነዉ::ስለዚህ የተሿሚዎቹ መልካምነት ወይም የመጡበት የፓርቲ ቁም ነገ

"ከእኛ ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህ?" በዴቭ ዳዊት

"ከእኛ ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህ?" ይህ ምስል የዴቭ ዳዊት ስራ ነው! June 6, 2020 የተፃፈ ከሰሞኑ የአማራ ህዝብ ትግል ከሁለት አመት በፊት በይፋ ተጠልፎ አማራዊ ብሔርተኝነትን ለማዳከምና ለማጥፋት ሲባል ብአዴናዊ ብሔርተኝነት መፈጠሩን፤ እንዲሁም ብአዴናዊው ብሔርተኝነት መገለጫ ባህርይው ምን እንደሚመስል በዝርዝር ተመልክተን ነበር። ከዚያም ጎን ለጎን በአማራ ህዝብ ትግል ውስጥ በአማራዊ ብሔርተኝነት እና በብአዴናዊ ብሔርተኝነት መካከል ግልፅ መስመር ባለመሰመሩ ምክንያት ከፍተኛ የሆነ የጎራ መደበላለቅ መፈጠሩን፥ይህንንም አጋጣሚ ተጠቅሞ በጎጣዊ ውግንና የገነገነው ብአዴናዊው ብሔርተኝነት፥ አማራዊ ብሔርተኝነቱን ለማደብዘዝና ለማፈን ሰፊ ዕድል እንደተፈጠረለት ተመልክተናል። እነሆ ዛሬ ጊዜ እንደፈቀደ የአማራ ህዝብ ብቸኛ መዳኛ የሆነው ግን በብዙ አቅጣጫ ጦርነት ተከፍቶበት ያለው አማራዊ ብሔርተኝነት ውስጣዊ ጠላቱ ስለሆነው ብአዴናዊ ብሔርተኝነት እንዲሁም ብአዴናዊው ብሔርተኝነት በአማራዊው ብሔርተኝነት ላይ የከፈተበትን የጦርነት ስልትና ይዘት እንፈትሻለን። መልካም ንባብ። የአማራ ሕዝብ የዘመናት ትግል የሆነው አማራዊ ብሔርተኝነት፥ እንደ አማራ አቆጣጠር በ1980ዎቹ መጨረሻ የመጀመሪያው የመጠለፍ አደጋ ሲገጥመው የተፈፀመው ደባ ቢኖር #የመሪ_አታጋይ_ድርጅቱን_ህልውና_ማሳጣት /የመዐሕድን/ ነበር። ሁለተኛው ዙር ህዝባዊ ተጋድሎ እየሰፋና ፍሬ ወደ ማፍራቱ ደረጃ ሲደርስ ደግሞ ትግሉ ገና #ሙሉ_ዕድገቱን_የጨረሰ_መሪ_ድርጅት ከመውለዱ በፊት፥ በህዝባዊ ማዕበሉ ከመበላት ለማምለጥ ሲል ብአዴን የአማራን ትግል ጠለፈው።  አማራዊው ብሔርተኝነት የራሱን ሰንደቅ የሚሸከም/Standard bearer/ መሪ ድርጅት ሳይፈጥር የአማራ ሕዝብ ትግል በብአዴን መጠለፉ

ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የተጸነሰው ሴራ ይፋ ሆነ ፤ ኢትዮጵያን ከመፈራረስ ለመታደግ በአንድነት መቆም ነው— በዶ/ር አክሎግ ቢራራ

እኔ እስከማውቀው ድረስ፤ የምእራብ አገሮች ለጥቁር አፍሪካ ሕዝቦች ሰላም፤ እርጋታ፤ ክብር፤ ነጻነት፤ ፍትሃዊና ዘላቂ ልማት ቆመው አያውቁም። በተለይ፤ ለመላው የጥቁር ሕዝብ ክብርና ነጻነት ተምሳሌ የሆነችውን የኢትዮጵያን ግዛታዊ አንድነት፤ ሉዐላዊነት፤ የስብጥር ሕዝቧን አብሮነት፤ ሰላም፤ እርጋታ፤ ፍትሃዊ፤ ዘላቂ ብልጽግና ደግፈው አያውቁም። የኢትዮጵያ ጠንካራና አገር ወዳድ መንግሥት ለነሱ ብሄራዊ ጥቅም ስጋት ፈጣሪ ነው። ይኼን ሃቅ በአጼ ኃይለ ሥላሴና በደርግ መንግሥት ወቅትም አይተናል።  ህወሓት/ትህነግ ጆ ባይደን በተመረጡበት ማግስት ክህደት፤ እልቂት ከፈጸመበትና ጦርነት ከጀመረበት አንድ ሳምንት በኋላ ለዚህ አጥፊ፤ ከሃዲና የውጭ ኃይሎች አገልጋይና አሽከር የሆነ ቡድን ግዙፍ ድጋፍ ይሰጡት የነበሩት የምእራብ “ዲሞክራሲ” ነን የሚሉ ባለሥልጥናት ሴራቸውን በምስጢር ቀየሱ።  ኢላማቸው ሁለት አስኳል ጉዳዮች ነበሩ፤ አንድ የጠቅላይ ሚንስትር ዶር ዐብይ አሕመድን መንግሥት መገልበጥና ባለሥልጣናትን ልክ እንደ ሰርቦች ለፍርድ ማቅረብ፤ ሁለት፤ ኢትዮጵያ ልክ እንደ ዩጎስላቭያና እንደ ሶማልያ እንድትበታተን ማድረግ።  እኛ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን በተደጋጋሚ ለምእራብ አገሮች ባለሥልጣናት፤ በተለይ ለአሜሪካ ምክር ቤት አባላት በተደጋጋሚ እባካችሁ ሚዛናዊ አቋም ያዙ፤ በመሬት ላይ ያለውን ሃቅ አንጸባርቁ፤ የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል የትግራይ ሕዝብ ጠላት አይደለም፤ የብሄር ማጥፋት ዘመቻ አያካሂድም፤ የኢትዮጵያ መንግሥት 70 በመቶ የሚሆነውን ሰብአዊ እርዳታ እየሰጠ ነው ወዘተ እያልን ብንጮህም ሰሚ አላገኘነም ነበር። ብዙዎቻችን ግራ ተጋብተን ነበር ለማለት እችላለሁ። ለምን ጀሩቸውን አይከፍቱም፤ አይናቸውን አይገልጡም? እንል ነበር፡ ከጀርባ በረቀቀ ምስጢር የሚካሄደውን ሴራ

JOURNALISM IS NOT CRIME

የአማራ ሚዲያ ማዕከል ጋዜጠኛ  ለድምጽ አልባው ወገናችን ፤ ድምፅ በመሆን የሚታወቀው ጋዜጠኛ አባይ ዘውዱ በነውረኛው የአማራ ብልጽግና ፓርቲ እና በአብይ አህመድ  አፋኝ ቡድኖች አሳፍነው ወዳልታወቀ ቦታ ወስደውታል።  Abay Zewdu, AMC reporter & Journalist Free Abay Zewdu   ድምጽን ለማፈን መሞከር ከቶውንም አይቻልምና ፤ በአስቸኳይ ጋዜጤኛ አባይ ዘውዱን ፍቱት!  Free AMC Journalist

“እውነትን በማፈን ፍትሃዊ መምሰል አችይልም- ፍትሃዊ አሰራርን በመከተልና በመፈፀም እንጂ”! በወንድወሰን ተክሉ

የአቢይ  መንግስት ፀረ አማራዊ ጋዜጠኞች አክትቪስቶችና ተሟጎቾች ዘመቻ! የአቢይ መራሹ  የብልፅግና  መንግስት  የመከላከያ  ሰራዊቱን  ቅሌታዊ  ሽንፈትን  ተከትሎ  በአስር ሺህ  የሚቆጠሩ  የመከላከያ  አባላትንና  ብሎም ሲቪል  ባለሙያዎችንና የዩንቨርስቲ  ተማሪዎችን  አዘርክርኮ  ከትግራይ  በፈረጠጠ  ማግስት በአማራ  አክትቪስት ጋዜጠኞችና የሰብአዊ  መብት  ተሟጋቾች  ላይ  በመዝመት  ጋሽ ታዲዮስ  ታንቱን  ጨምሮ  ከአስር  በላይ ጋዜጠኞችን  በኢትዮጲያ  አፍሶ  ያሰረ  ሲሆን በተመሳሳይ  ቁጥር  የሚሆኑ  የማህበራዊ ሚዲያ  አንቂዎችን አካውንትን በዘመቻ  መልክ ለማስዘጋት  መቻሉን ማወቅ  ተችሏል:: ይህ የግራፊክ ምስል ጸሃፊውን አይመለከትም ከጋዜጠኛ  Getachew Shiferaw ሺፈራው  ጀምሮ ጋዜጠኛና አክትቪስት Wondwossen Teklu Wondelove የሰብአዊ መብት ተሟጋች  ቤተልሄም ዳኛቸው Yodith Gideon Dave Dawit Asaminew Tsige Follower  Melkamu Shumye Loul Mekonnen Bahailu_Tessema  Tina Belay bahailu_tessema Kidist_Garumha እና የመሳሰሉትን  በርካታ አማራዊ አካውንቶች በአጭር  ተመሳስይ  ቀናት  ውስጥ  ማዘጋት  የመቻሉ ጉዳይ  የአቢይ  መራሹን  መንግስት በአማራ  ጉዳይ  ላይ የመዘዘውን አዲስ  ሰይፍ  ያመላክታል:: አማራዊያን ጋዜጠኞች  አክትቪስቶችና የሰብአዊ  መብት ተሟጏቾች  በአቢይ  ጥርስ  ውስጥ  እንዲገቡ ያደረጋቸውና አቢይ ከህዝብ ጆሮ  ለመደበቅ  የፈለገው  ምንድነው? የአቢይ  መራሹ  የኦህዴድ  ብልፅግና መንግስት  የመከላከያ ሰራዊቱን እያክለፈለፈ  ከትግራይ ያወጣበት ሂደት  ምክንያትና  ብሎም  በክስተቱ  ግንባር  ቀደም  ተጠቂና  የውሳኔው 

ፋሺስቱ ኦህዴዳዊው ስርአት

አሜሪካ - የፋሺስቱ ኦህዴዳዊው አፓርታይዳዊው ስርአት - የከረፋ ወንጀሉን መደበቂያና የህዝብን ድጋፍ መዝረፊያ ፈፅሞ አትሆንም! በወንድወሰን ተክሉ አሜሪካንን ፀረ ኢትዮጲያ የሚያደርግ ክስተትም ሆነ ፀረ አሜሪካዊ ኃይል በዛሬይቱ ኢትዮጲያ አለ? በኢትዮጲያነት ስሜት የተሰራው የእስከዛሬው ወንጀል ስቃይና መከራ ከእንግዲህ ላይቀጥል መበጣጠስ ያለበት አሁን ዛሬ ነው:: ፋሺስቱ የአቢይ መራሹ አፓርታይዳዊ ስርአት ከጀሌዎቹ ኢዜማ ጋር በመሆን አሜሪካ ኢትዮጲያን እንደሊቢያ ልታደርግ የተነሳች ቀንደኛ ጭራቅ ናት በማለት የህዝብን attention እና ድጋፍ mobilize ለማድረግ ሲንቀሳቀሱ ታይቷል:: መንጋውም - በተለይ በተለይ ምንም መማር ያልቻለው በስሜት ጋላቢ መንጋ ይህንን መንግስት መር ፕሮፖጋንዳን በማስተጋባት ፈጥኖ ሲሰለፍ ታይቷል:: የግራፊክ ምስሉ ጸሃፊውን አይወክልም! በእርግጥ አሜሪካ ኢትዮጲያን የመበትን አላማ እቅድና ፍላጎት አላትን ? ካላትስ ለምን እና እንዴት  ብሎ ከመጠየቅ የተወረወረለትን አጥንት ለቀም አድርጎ እንደሚሮጥ ውሻ እነዚህ መሰሪዎች የወረወሩለትን የሴራና የፈጠራ ወሬን ብድግ አድርገው ሲያራግቡ ይታያል:: ተመልከቱ ይህ ለብልፅግና መንግስት እነ XYZ የፖለቲካ ኃይሎች ይመቱ በሽብርተኝነት ይፈረጁ ሚዲያዎች ይዘጉ እያለ ጥናት በማቅረብ የኢትዮጲያን ሀገረ ዴሞክራሲን ግንባታን በማደናቀፍ ቀንደኛ ጨፍጫፊ ፋሺስት ስርአትን እየፈጠረ ያለው የኢዜማው ስብስብ ሀገር ወዳድ መስሎ እና እራሱን ለሀገር ተቆርቋሪ አድርጎ አሜሪካንን እየጠራ ሲፎክር አይታችሁ እንኳን መረዳት አትችሉምን? የኢትዮጲያን ህልውና አደጋ ላይ የጣለው የአሜሪካ ተፅእኖ ሳይሆን የአቢይና ኢዜማ ፋሺስታዊ አምባገነንነት ሆኖ ሳለ ዛሬ እነዚሁ ስብስቦች ሀገር በአሜሪካ ጣልቃ ገብነት ልትፈርስ ነው