Skip to main content

"ከእኛ ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህ?" በዴቭ ዳዊት

"ከእኛ ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህ?"
"ከእኛ ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህ?" ይህ ምስል የዴቭ ዳዊት ስራ ነው!

June 6, 2020 የተፃፈ

ከሰሞኑ የአማራ ህዝብ ትግል ከሁለት አመት በፊት በይፋ ተጠልፎ አማራዊ ብሔርተኝነትን ለማዳከምና ለማጥፋት ሲባል ብአዴናዊ ብሔርተኝነት መፈጠሩን፤ እንዲሁም ብአዴናዊው ብሔርተኝነት መገለጫ ባህርይው ምን እንደሚመስል በዝርዝር ተመልክተን ነበር። ከዚያም ጎን ለጎን በአማራ ህዝብ ትግል ውስጥ በአማራዊ ብሔርተኝነት እና በብአዴናዊ ብሔርተኝነት መካከል ግልፅ መስመር ባለመሰመሩ ምክንያት ከፍተኛ የሆነ የጎራ መደበላለቅ መፈጠሩን፥ይህንንም አጋጣሚ ተጠቅሞ በጎጣዊ ውግንና የገነገነው ብአዴናዊው ብሔርተኝነት፥ አማራዊ ብሔርተኝነቱን ለማደብዘዝና ለማፈን ሰፊ ዕድል እንደተፈጠረለት ተመልክተናል።

እነሆ ዛሬ ጊዜ እንደፈቀደ የአማራ ህዝብ ብቸኛ መዳኛ የሆነው ግን በብዙ አቅጣጫ ጦርነት ተከፍቶበት ያለው አማራዊ ብሔርተኝነት ውስጣዊ ጠላቱ ስለሆነው ብአዴናዊ ብሔርተኝነት እንዲሁም ብአዴናዊው ብሔርተኝነት በአማራዊው ብሔርተኝነት ላይ የከፈተበትን የጦርነት ስልትና ይዘት እንፈትሻለን። መልካም ንባብ።

የአማራ ሕዝብ የዘመናት ትግል የሆነው አማራዊ ብሔርተኝነት፥ እንደ አማራ አቆጣጠር በ1980ዎቹ መጨረሻ የመጀመሪያው የመጠለፍ አደጋ ሲገጥመው የተፈፀመው ደባ ቢኖር #የመሪ_አታጋይ_ድርጅቱን_ህልውና_ማሳጣት /የመዐሕድን/ ነበር።

ሁለተኛው ዙር ህዝባዊ ተጋድሎ እየሰፋና ፍሬ ወደ ማፍራቱ ደረጃ ሲደርስ ደግሞ ትግሉ ገና #ሙሉ_ዕድገቱን_የጨረሰ_መሪ_ድርጅት ከመውለዱ በፊት፥ በህዝባዊ ማዕበሉ ከመበላት ለማምለጥ ሲል ብአዴን የአማራን ትግል ጠለፈው። 

አማራዊው ብሔርተኝነት የራሱን ሰንደቅ የሚሸከም/Standard bearer/ መሪ ድርጅት ሳይፈጥር የአማራ ሕዝብ ትግል በብአዴን መጠለፉ፥ በብአዴናዊ ብሔርተኝነት እና በአማራዊ ብሔርተኝነት መካከል የሚኖረውን አሰላለፍ ኢ-ተመጣጣኝ /asymmetric/ አድርጎታል። ይኸውም አማራዊው ብሔርተኝነት ራሱን የሚያቅፍበት ድርጅታዊ ቁመናም ይሁን የፓርቲ መዋቅር የሌለው በመሆኑ ድምፁ የተበታተነ ሲሆን፥በአንፃሩ ብአዴናዊው ብሔርተኝነት መንግስታዊ ቁመና ያለው ነበር። ይህም ብአዴንን የአማራ ህዝብ ትግል መሪና የብሔርተኝነቱም ዋና መሐንዲስ መስሎ እንዲታይ አስቻለው።

የተፈጠረውን ብዥታ እንደመልካም አጋጣሚ የቆጠረው የብአዴን አመራርም ከወራት በፊት የአማራ ሰላማዊ ልጆችን በጠራራ ፀሐይ እየተኮሰ ያልገደለና የአማራን ርስት ለዘመናት ሲሸጥ ያልነበረ ያህል፥ የብአዴን-wood /like Holywood, Bollywood, it's ብአዴንwood/ የጀብድ ተረታዊ ፊልሞችን እየፈበረከ፥ ሳይበር ላይ በውጭና በሀገር ውስጥ ባሰማራቸው ካድሬዎቹ አማካኝነት የገፅታ ግንባታ ማድረግ ጀመረ። Back hand spring ተገልብጠው ከሳሙራ የኑስ ሽጉጥ የሚያስጥሉ፣ ደብረፅዮንን 'ቁጭ ብድግ' የሚያሰሩ፣ጌታቸው አሰፋን አንቀው የሚጠፈጥፉ፣ስብሀት ነጋን በግልምጫ የሚያነስሩ ጀብደኞች መሆናቸውን በከዳሚ ካድሬዎቻቸው ነግረውን ሲያበቁ፥ የወያኔ ትግሬን ወደ መቀሌ ማፈግፈግ እንደመጨረሻ ግብ በመቁጠር ከገጠር ቀበሌ እስከ ክልሉ ከተማ የዘለቀ የረጅም ባንድራ ፉክክር በሚመስል ሰልፍ ህዝባችንን ሲያሰቃዩት ከቆዩ በኋላ፥ ራሳቸው ከፈጠሩት የቅዠት ዓለም ሲነቁ፥ "የኢትዮጵያ ሱሴ" ፋሽስታዊው የኦሮሞ ቡድን ባንኩንም ታንኩንም ጠቅልሎ ወስዶ አየር ላይ ሲያንሳፍፋቸው፥ "ቁዘማ ላይ ነን"፣ " ስልጣን ጋር ስንደርስ ተሽኮረመምን" ብለው በማያወላዳ ሁኔታ አከርካሪ አልባ፣ከመላላክ ውጪ በራሳቸው መቆም የማይችሉ የስልብ ስነልቦና ተጠቂዎች መሆናቸውን አስመሰከሩ።

ብአዴንም እንደ ድርጅት የብሔርተኝነቱ መሪ-ድርጅት መስሎ ቢቀርብም፥ ለአማራ ህዝብ ጥያቄ መፍትሔ ሊሰጥ ቀርቶ፥ ቅይዷን እንደበጠሰች ደንባራ በቅሎ እርስበርሱ ሲራገጥ ከርሞ የሰኔው_የብአዴን_ቀውስ አጋጠመው። ከዚያች ቅፅበት በኋላም ለአስራ አምስት ወራት በጭምብል አጥልቋት የነበረችውን "አማራነት" አውልቆ፥ወደ እውነተኛ ባህርይው፥ወደ ከፋፋይ ጎጣዊ አሰላለፍ ወርዶ ልክ የአማራ ሕዝብ፣ አማራዊነትና የአማራ ብሔርተኝነት የብአዴንን የሰኔው ቀውስን የፈጠሩት ይመስል፥ ይህ ጎጣዊ ውግንና ያለው የብአዴናዊ ብሔርተኝነት ሠራዊት ጠርዝ የወጡ ተፃራሪ ዋልታዎች ላይ ቆሞ የአማራ ሕዝብ የዘመናት ትግልን በአፍጢሙ ደፍቶ ለመቅበር በማሰብ በአማራዊ ብሔርተኝነት ላይ ግልጽ ጦርነት አወጀ።

እንደ አንድ የአማራ ህዝብ ሊያቆሙን የሚችሉ አምዶችን በሙሉ ፥ቀን በቀን ከመደብደብ አልፎ፥የአካባቢ ስሞችን ልክ ደማዊ ማንነት በማስመሰል፥ በህቡዕ አልፎ አልፎም በግላጭ ያንን ከመስበክ አልፎ የመሰባሰቢያ Cause አደረገው። የብአዴንን የሰኔው ቀውስንም፥ከድርጅቱ አውጥቶ ህዝባዊ ቅርፅ ለማስያዝ 'እንበለ ትካት' ተግቶ መስራት ጀመረ።

ይህ ጎጣዊ ውግንና ያለው የብአዴናዊ ብሔርተኝነት ሠራዊት ግቡ አካባቢዎችን ማዕከል ያደረገ የግል ጥቅም፣ የዝርፊያ፣የፖለቲካ ስልጣን ማስጠበቂያ እና ማግኚያ፣ለሰራቸው ወንጀሎች መደበቂያና ደጋፊ ማሰባሰቢያ በመሆኑ የአማራ ሕዝብ አንድ ሆኖ እንዲቆም አይፈልግም። የአማራ ህዝብ አንድ ሆኖ መቆም፥ ጠባብ ጎጣዊ የግል ጥቅሙን እንደሚያሳጣው፣ የህዝባችን ውዝፍ ጥያቄዎችም ምላሽ የሚሹ በመሆናቸውና እነዚህ የህዝብ ጥያቄዎችን ለመመለስ አቅምም ይሁን ፍላጎት የሌለው ከመሆኑ አንፃር፥ የአማራ ሕዝብን በአካባቢ ከፋፍሎና የእኔ የሚለውን ጎጥ በአረንጓዴ፣ጠላት ባላንጣዬ የሚለውን ጎጥ በቀይ፣እንዲሁም ቀሪውን በአጫፋሪነት በቢጫ ቀለም ወክሎና አስምሮ መርዙን ከፌደራል የሚንስትር መስሪያቤት እስከ ክልል ከዚያም እስከ ባህር ማዶ የሳይበር አውድ ሲረጭ ይውላል። 

ብአዴናዊ ብሔርተኞች በብአዴን ወቅታዊ አቋም መሠረት ስለሚተነፍሱ፥ ብአዴን ደግሞ ጎጣዊ ውግንና ባላቸው አንጃዎች የተከፋፈለ በመሆኑ፥ ብአዴናዊ ብሔርተኝነትም ይሁን ብአዴናዊ ብሔርተኞች ዋነኛ ማጠንጠኛቸው ጎጣዊ ውግንና (ያውም ለመደበቂያነትና ደጋፊ ለማፍራት ብቻ) ሲሆን፤ ቀንደኛ ጠላታቸው ደግሞ አማራዊነትና አማራዊ ብሔርተኝነት ነው።

***** የጥፋት ተልዕኮዎች ********

የብአዴናዊው ብሔርተኝነት ሠራዊቶች ራሳቸውን የጎጥ መሳፍንትና መኳንንት አድርገው የሾሙ ዕቡያን ከመሆናቸው የተነሣ፥ አንድ የአማራዊ ብሔርተኝነት አቀንቃኝ እነሱ "የእኛ" ስለሚሉት አካባቢ እንዲናገር ፈቃድ ሰጪና ፈቃድ ነሺ ሆነው ለመቅረብ ሁሉ ይዳዳቸዋል። ከዚህም አልፎ #"የእኛ"_የሚሉትን_ህዝብ_ከቀሪው_የአማራ_ህዝብ_ነጥለው_ለመጋለብ ይረዳቸው ዘንድ የአማራን ህዝብ አንድ አድርገው ያስተሳሰሩ ሐረጎችን ለመበጣጠስ ቀን ከሌሊት ተግተው ይሰራሉ። በዋናነት ኢላማ ያደረጉትም ፦

1. የአማራ ህዝብ የጋራ የሆኑ ማህበራዊ-ባህላዊና የሞራል ስሪቶችን ማፈራረስ /dismantling the socio-cultural and moral fabric of the Amhara people/

2. በአማራ ህዝብ መካከል የጋራ ፖለቲካዊ ቁርጠኝነት እንዳይኖር ዕንቅፋት መሆን /Obstructing the development of collective-political-will/

3. የአማራ ህዝብ የሚጋራው እሴትና የጋራ ራዕይ እንዳይኖረው ከፋፋይ መርዞችን ማሰራጨት ናቸው። / disseminating venomous propaganda among our people to kill common good and shared goal in the society./

****** ማስፈፀሚያ መሣሪያ ******

የመጀመሪያው የብአዴን ትውልድ፥ አስቀድሞ መለስ ዜናዊ በመተካካት ስም፣በኋላም በሀይለማርያም ዘመን በጡረታ የተገለለ ወንጀለኛ ቡድን ሲሆን ዛሬ ላይ በፖለቲካ መድረኩ ላይ የለም። 

ከዚያ ይልቅ እንደ አማራ አቆጣጠር ከ1981/82 ጀምሮ የወያኔ ትግሬ ኮሾሮና ዱቄት በመሸከም ስራውን የጀመረው ሁለተኛው የብአዴን ትውልድ፥ አበክሮ በመላላኩና ለአማራ ህዝብ ጥፋት መንገድ መሪና አስፈፃሚ በመሆኑ ሹመትና ስልጣን እየተደረበለት፣ የዕውቀት አክፍሎተኞች ማምረቻ በሆነው 'ሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ' እንዲማርና የበለፀጉ ሀገራት ለሶስተኛው ዓለም ሀገራት በሚሰጡት ነፃ የትምህርት ዕድል ተጠቃሚ ሆኖ "ማዕረግ" የደረበ፥ የብአዴንን የስልጣን ማማ የወረሰ ሀይል ነው። 

በአንፃሩ ደግሞ ሶስተኛው የብአዴን ትውልድ በታችኛው መዋቅር እየታቀፈ ያለ፣ በውጪ ሀገርና በሀገር ውስጥ የሚኖር፥ ኮንደሚኒየም፣ መሬት፣ስልጣን ቃል የሚገ'ባለትና የተፈፀመለት፣ አልፎ አልፎም በእነዚህ መደለያዎች ተገዝቶ ሌላ ከፍ ያለ ስጦታን በተስፋ እንዲጠብቅ የተነገረው፣ ዋና ተግባሩም የብአዴንን የስልጣን ማማ የተቆጣጠረውን ሁለተኛው የብአዴን ትውልድን ስልጣንና ጥቅም ለማስጠበቅ ደጀን የሚሆን ሠራዊት ነው። 

ስለዚህ ሁለተኛውና ሦስተኛው የብአዴን ትውልድ ከፌደራል ሚኒስቴር መስሪያ ቤት እስከ ክልልና ባህር ማዶ የሳይበር አለም በዘረጋው ሰንሰለት ከላይ ያስቀመጥናቸውን ሶስት የጥፋት ተልዕኮዎች ለመፈፀም፣አማራዊነትን አኮስሶ፥ለድጋፍና መደበቂያነት የሚፈልገውን ጎጣዊ አርተፊሻል ማንነትን ለመትከል፣ አማራዊ ብሔርተኝነትን አክስሞ፥ብአዴናዊ ብሔርተኝነትን ለማንገስ ሰንሰለታዊ ባህርይ ያለው ጦርነት /net-centric warfare/ በአማራዊነትና በአማራ ብሔርተኝነት ላይ ከፍቷል። አሳዛኙ ነገር አማራዊ ብሔርተኛውና በአማራዊነት ብቻ የሚያምነው ሀይል፥ እንዲህ አደገኛ የሆነ ጦርነት ታውጆብን እያለ፥ አንድም ጦርነት እንደተከፈተብን በበቂ አልተገነዘብነውም፥አልያም ጭራሹኑ ጦርነት እንደተከፈተብን አላወቅንም። ይህ ባይሆን ኖሮ በብአዴን ብሔርተኞችና በአማራዊ ብሄርተኞች መካከል ግልፅ መስመር ማስመር በቻልን ነበር። ይህ የመሆን ወይም ያለመሆን ጉዳይ ነው። ወይ ከእኛ ወገን አልያም ከጠላቶቻችን ወገን የምንልበት የባለሁለት ቀለም አለም ነው። ብአዴናዊ ብሔርተኝነት እና አማራዊ ብሔርተኝነት የሚጠፋፉ አስተሳሰቦች እንጂ የሚደጋገፉ አልያም አብረው መቆም የሚችሉ አስተሳሰቦች አይደሉም!!! 

ከፌደራል ሚንስቴር መስሪያቤት እስከ ክልል፥ ከዚያም እስከ ባህር ማዶ የሳይበር ዓለም የተዘረጋው፣ተፃራሪ ዋልታን ረግጦ በጎጥ ውግንና የቆመው፣በሁለተኛውና በሦስተኛው የብአዴን ትውልድ ጥምረት የሚዘወረው ሰንሰለታዊ ጦርነት /net-centric war/ አማራዊነትን አውድሞ፥ ጎጣዊ ውግንና ያለውን ብአዴናዊ ብሔርተኝነት ለማንበር ከፍተኛ ስራውን የሚሰራው ዘርፈ ብዙ የፕሮፓጋንዳ ስልቶችን በመጠቀም ሲሆን በፌደራል ሚንስቴር መስሪያ ቤትና በክልል ከፍተኛ የመንግሥት መዋቅር ባለውና በባህር ማዶ በሳይበር በተሠማራው የብአዴናዊ ብሔርተኝነት ሠራዊት መካከል ከፍተኛ የሆነ የዐውደ ውግያ የጋራ ግንዛቤ /high level of shared battlespace awareness/ ፈጥሮ ይንቀሳቀሳል።

የጥፋት ተልዕኳቸውን ለማስፈፀምም ፕሮፓጋንዳንና ቅስቀሳን /intensive propaganda and agitation/ በዋና መሣሪያነት እየተጠቀሙ የሚገኝ ሲሆን ለአብነት ያህልም:-

ሀ. በቃልና በተግባር የሚገለፁ ፕሮፓጋንዳዎችን ማሰራጨት /Propaganda by word and by deed/

ለ. ነገሮችን አግዝፎና ለጥጦ ማሳየት /hyperbolic propaganda/:- ለምሳሌ የብአዴንን የሰኔ ቀውስ ልክ የህዝብ ለህዝብ ጉዳይ አስመስለው የሚያቀርቡበት ትርክት፣ ልክ ብአዴን የአማራ ብሔርተኝነት መሪ ድርጅት ይመስል፥ የብአዴንን የሰኔ ቀውስ፥የአማራ ብሔርተኝነት መክሸፍ አስመስለው የሚያላዝኑት ሁሉ የዚህ ነገሮችን ከእውነታው ባፈነገጠ መልኩ ለጥጦ የማሳየት አባዜ ነው። 

ሐ. ብርቱው ህዝባችን በተለይ በብአዴኑ የሰኔ ቀውስ ምክንያት በተጠቂነት ስሜት እንዲቆዝም ለማድረግ መሞከር /instilling victimhood mentality/. 

=> ሁሌም እንደምንናገረው የብአዴን የሰኔው ቀውስ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ህይወታቸውን ያጡበት አሳዛኝ ክስተት እንጂ የአራትና አምስት ሰው ሞት አይደለም። ከእነ ፖለቲካ አመለካከት ልዩነታችንም ቢሆን ሰዎች በዚህ መልክ ማለፋቸው እጅግ አሳዛኝ ነው። እንደ ህዝብ መላው የአማራ ህዝብ ከአብራኩ የወጡ በመቶዎች የሚቆጠሩ ልጆቹ በዚህ መልክ ማለፋቸው አሳዝኖታል። ከዚያ በዘለለ ከባህልና ዕሴታችን ባፈነገጠ ሁኔታ አንዱ አካባቢ የሚኖረው ህዝባችን ሀሴት የሚያደርግበት፥ ሌላኛው አካባቢ የሚኖረው ህዝባችን ደግሞ የሚቆዝምበት ተደርጎ የሚሳለው፥ ያው ያልተቋጨው የብአዴን ቀውስ ቅጥያ ፕሮፓጋንዳ እንጂ የአማራ ህዝብ የራስ ምታት አይደለም። ፍትህንም ማለትም እንደ ብአዴናዊያን የመረጣ-ፍትህን /selective justice/ ሳይሆን የተሟላ ፍትህን ህዝባችን ከዚህ የቆሸሸ ስርዓት እንደማያገኘው ጠንቅቆ ያውቀዋል። 

መ. ተፃራሪ ዋልታዎች ላይ ቆሞ በጅምላ መፈራረጅ /vilifying en masse/

ሠ. የማይገናኙ ትንተናዎችን ማቅረብ /Eclecticism/:-

=> ከላይ እንዳየነው የብአዴንን ቀውስ፥የአማራ ህዝብ መሠረታዊ ችግር አስመስሎ የማቅረብ፣ የብአዴንን ክሽፈት የአማራ ብሔርተኝነት ክሽፈት አድርጎ ማቅረብ አንዱ ስልታቸው ነው። ሌላው ቢቀር አሁን አሁን በአማራዊነት አስተሳሰባቸው ቁርጠኛ አቋም እንዳላቸው የምናስባቸው ወንድሞች ሳይቀር፥ የብአዴናዊያኑ ፕሮፓጋንዳ ሰለባ ሆነው፥ "የአማራ ህዝብ ትግልና ብሔርተኝነት ፈተና አድዋዊነት ነው" ይላሉ። አድዋዊነት የብአዴንና የብአዴናዊ ብሔርተኞች አደጋና ፈተና ሊሆን ይችላል፥ የአማራ ብሔርተኝነት አደጋም ፈተናም ግን አይደለም!!! ምክንያቱም የአማራ ብሔርተኝነት እኮ ሙሉ ዕድገቱን የጨረሰ መሪ ድርጅት እንኳን በቅጡ የለውም። ሙሉ ዕድገቱን የጨረሰ አማራዊ ድርጅት ለመኖሩ የመጀመሪያው መስፈርት በመላው የአማራ ርስቶች ላይ የሚኖረው ወ'ጥና ተመሳሳይ አቋም ነው፤ "መተከልና ደራ፥ራያና ወልቃይት የአማራ ነው" ሲል ይቆይና አዲስ አበባና ሸኖ /በነገራችን ላይ ሸኖ እንደ ደራ ሁሉ በወያኔ የክልል መስመር ሳይቀር "የአማራ ክልል" አካል የነበረ ሲሆን ብአዴን ነው ለኦሮሞ አሳልፎ የሰጠው/ ላይ ሲደርስ አንደበቱ የሚተሳሰር በአማራ ስም የተደራጀ ድርጅት ለእኔ የአማራ ህዝብ መሪ-ድርጅት ለመሆን ገና አልደረሰም። ወደ ጉዳያችን ስንመለስ አማራዊ መሪ ድርጅት በሌለበት፥ አካባቢን ማዕከል ያደረገ ገዢ መደብ /Core political group based on regionalism sentiment/ (አድዋዊነት) የአማራ ብሔርተኝነት ፈተናም አደጋም ሊሆን አይችልም። ብአዴንን እንደመሪ

ድርጅት የተቀበለ አካል ግን፥ "አድዋዊነት ችግሬ ነው" ብሎ በብአዴን ማዕቀፍ ውስጥ ሊናገር ይችላል። አድዋዊነት የብአዴን ችግር ነው ወይ? ለሚለው ግን ለጉዳዩ ቅርበት ያለው አካል በእርግጠኝነት ሊናገረው ይችላል። በእኛ ግምት ግን የብአዴን ጎጣዊ አንጃዎች ቀኑን ሙሉ ተጠላልፎ ለመጣጣል ሲሰሩ ስለሚውሉ፥ እንኳን አድዋዊነት፥ የፀሐይ በምስራቅ መውጣትም ሊያጣላቸውና ውስጣዊ ችግራቸው ሊሆን ይችላል። ያ ግን የእኛ ራስምታት አይደለም። የአማራ ራስምታት ብአዴን ራሱ ድርጅቱና መዋቅሩ ነው። በእኛ ግምገማ መሠረት ብአዴን የአማራ ህዝብ ትልቅ አደጋና ውስጣዊ ጠላት ነው!!! ብአዴንና የአማራ ብሔርተኝነት ተጠፋፊ በመሆናቸው፥ አብረው የሚጋሩት ምንም ነገር አይኖርም!!! የአማራ ብሔርተኝነት መለምለም የሚችለውም፥በብአዴን መቃብር ላይ ብቻ ነው!!! ስለሆነም የጠላት ብአዴን ውስጣዊ ቀውስም ይሁን ችግር አብሮ ከስርዓቱ ጋር ተመንግሎ የሚጣል አረም እንጂ አማራና አማራዊነት፥ የብአዴንን አድዋዊ ሸክሙን የሚጋሩለት፥አልያም ውርሱን የሚያስቀጥሉለት አይደለም። 

*** በየጎጡ አድፍጦ ብአዴናዊ ተልዕኮውን የሚወጣው የብአዴናዊ ብሔርተኝነት ሠራዊት፥ ከላይ ያየናቸውን አይነት የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ የሚያደርገው የሚከተሉትን ነጥቦች ለማሳካት ታሳቢ አድርጎ ነው:-

1. በአማራ ህዝብ ውስጥ እያበበ የመጣውን ደማዊ አማራዊ ማንነትና የብሔርተኝነት መንፈስ ለማክሰም /to dissolve the primordial ethnic identity consciousness and the spirit of the fast growing Amhara nationalism/.

=> ይህንን አድርጎ ህዝባችንን ካልከፋፈለ በስተቀር፥ የህዝባችንን ጥያቄዎች መመለስ የሚችልበት አቅምም ይሁን ፍላጎት ባለመኖሩ የስልጣን ዕድሜውን ማራዘምም ይሁን ዝርፊያውን ማስቀጠል አይችልም።

2. የአማራ ብሔርተኝነት አቀንቃኙን ንቁ ሀይል ተስፋ ለማስቆረጥ / to demoralize the Amhara Nationalism prime movers and active parts/

3. የአማራን ህዝብ የስነልቦና እሴት አምዶችንና ስሪቶች መቆጣጠር አልያም ማጥፋት/to seize or destroy the objects of the psychological value and make up of the Amhara people/:-

ይህንን ማድረግ ህዝባችንን ነገ እነሱ ለሚያልሙለት የጎጥ አሰላለፍ ምቹ እንዲሆን ይረዳናል ብለው በማስላታቸው ነው። ህዝባችንን በተጠቂነት ስሜትና እርስበርሱ በጥርጣሬ እንዲተያይ የማድረጉ ዘመቻ አላማ ህዝባችንን ለመነጣጠልና ለሠላሳ አመታት ሲሰሩት ለኖሩት ወንጀላቸው መሸሸጊያ ለማበጀት እንዲሁም ቋሚ ጭፍን ደጋፊ ለማፍራት ነው።

ዛሬ እኮ አንዱን የብአዴን ወደል ባለስልጣን/ካድሬ ብትተች፥ ህልቆ መሳፍርት የሌለው የብአዴናዊ ብሔርተኝነት ሠራዊት እንደ ግሪሳ ተጠራርቶ "የዚህ አካባቢ ህዝብ ተጠቃ" እያለ ይዘምትብሃል። የየዕለት ስራቸውም ይኸው ነው። ለማንኛውም፥ የየትኛውም አማራ አካባቢ ህዝብ በእነዚህ ሀገር ሻጭ ብአዴናዊያን ይወከላል ብሎ መቀበል ለእኔ የአማራን ህዝብ መሳደብ መሆኑ ሊሰመርበት ይገባል።

=========== ማጠቃለያ ============

* ብአዴንና ብአዴናዊ ብሔርተኝነት በአማራዊነትና በአማራ ብሔርተኝነት ላይ ግልፅ ጦርነት አውጀው ወደስራ ከገቡ ቆይቷል። በምላሹ በአማራዊነትና በአማራ ብሔርተኝነት የምናምን ሀይሎች ግልጽ ጦርነት ታውጆብን መሬት የረገጠ ስራ እየተሰራብን እንደሆነ ወይ ግንዛቤው የለንም፣አልያም ምን እንደምናደርግ ግራ ተጋብተን ቆይተናል። ከአሁን በኋላ ግን ውድቀትና ሽንፈታችንን ለማፋጠን ዝም ብለን የምናይበት ዘመን አብቅቷል። የተደበላለቀውን ጎራ በማጥራትና ሚናን በመለየት እንጀምራለን። ከብአዴናዊ ብሔርተኞች ጋር ጠላት እንጂ አጋር አልያም ወዳጅ አይደለንም!!!

መደበቂያ እና ድጋፍ ለማሰባሰብ የሚጠቀምበትን ጎጣዊ ውግንናን ዋነኛ መገለጫው ያደረገው ብአዴናዊ ብሔርተኛ፥ ከወያኔ ትግሬ /ትህነግ/፣ከፋሽስታዊ የኦሮሞ ፅንፈኛ ሀይሎች እንዲሁም ከተምኔታዊት "እምዬ ኢትዮጵያ" አምላኪ ሐሳዊ የውሸት-አንድነት አቀንቃኙ ሀይል እኩል በጠላትነት የምንፈርጀውና የምንዋጋው ሀይል መሆኑ ይሰመርበት!!! 

ከዚህ ብአዴናዊ ብሔርተኛ ሀይል ጋር ምንም አይነት ማህበራዊ፣ ሀይማኖታዊ፣ ፖለቲካዊም ይሁን ኢኮኖሚያዊ ንክኪ ማድረግ አያስፈልግም። ህዝባችንም የዚህ እርምጃ አካል ንቁ ተሳታፊ እንዲሆን አበክረን እንቀሰቅሳለን። ህዝባችንን ለከፋ መከፋፈልና አደጋ ከሚሰጥ ሀይል በላይ ጠላት የለንም። ዛሬ በአማራ ህዝብ ጥያቄዎች ዙሪያ በጋራ እንዳንቆም ትልቅ እንቅፋት እየፈጠረ ያለው ይህ የብአዴናዊ ብሔርተኝነት ሠራዊት ነው!!!

በተረፈ ለአቅመ መሪ-ድርጅት ያልደረሱ ግን ህዝብ በስሱም ቢሆን እምነት የጣለባቸው አብንን የመሳሰሉ ድርጅቶች የጎደላቸውን ክፍተት ሞልተው፥ አማራ በርስቱ የማይደራደር ብርቱ ህዝብ መሆኑን ታሳቢ አድርገውና ግድፈታቸውን አርመው፣ ከብአዴንና ከብአዴናዊ ብሔርተኝነት አራማጆች ራሳቸውን አርቀው ታሪካዊ ድርሻቸውን እንዲወጡ ለማሳሰብ እንወዳለን።

===============ይቀጥላል=============

የአማራ ብሔርተኝነት ይለምልም!!!

ብአዴናዊ ብሔርተኝነት ይውደም!!!

ዴቭ ዳዊት።


Comments

Popular posts from this blog

"ከአሁን በሆላ ፋኖ ወደ አንድነት መምጣት አለባቸው የሚባለው አካሄድ አይሰራም" :: በወዳጄ/ቤተ አማራ ወሎ

ከአሁን  በሆላ  ፋኖ  ወደ  አንድነት    መምጣት  አለባቸው  የሚባለው  አካሄድ  አይሰራም::  ክህደት   ከተፈፀመ  በሆላ  አንዱ  ቡድን  ከሌላው  ስር  ሆኖ  ይቀጥላል  ማለት  የማይቻል   ነው::  ምክኒያቱም 1ኛ:- 27  ቀን  ቁጪ  ብለው   መክረዋል :: እያንዳንዱ  አደረጃጄት  ሰነድ  ፅፈው  አቅርበዋል::  በቀረበው  ሰነድ  ላይ  ከፍተኛ  ውይይት  ተደርጎበት  የሚወድቀው  ወድቆ  የሚፈለገው  ፀድቋል::ቃለ  መሀላ  ፈፅመው   ወደ  ምርጫ   ለመግባት  ተስማምተዋል:: እጃቸውን  አውጥተው   ከመረጡ  በሆላ    ግን    "ጨዋታ  ፈረሰ  ዳቦ  ተቆረሰ"   የሚል  የህፃን  ልጂ  ጨዋታ  ውስጥ  መግባት   የአማራን  ህዝብም  ሆነ  የፋኖን  ትግል  መናቅ  ነው:: ይህ  አልበቃ  ብሎ   "ምርጫው  ከኛ  እውቅና  ውጪ  ነው  እኛ  አናውቀውም"  የሚል   የውሸት    የህፃን  ልጂ  ፕሮፓጋንዳ...

ስርነቀል ለውጥ ማምጣት የአማራ ብሄርተኝነት የህልውና ትግል ብቸኛ ግብ ነው። በ Alen Kassahun

ምስሉ ጸሃፊውን አይወክልም፡፤ ከ50 አመታት በላይ የተተከለውንና በተግባር እየተፈፀመ ያለውን አማራን ማጥፋትና ኢትዮጵያን ማፍረስ ከስሩ በመንቀል #4ኪሎን ተቆጣጥሮ ስርነቀል ለውጥ ማምጣት የአማራ ብሄርተኝነት የህልውና ትግል ብቸኛ ግብ ነው። ፋኖ በሚያደርገው የህልውና ትግል አማራ ጠልነት የወለደውን የአማራን ዘር ማጥፋት፤ ማፅዳት፤ የሰባዊ መብት ጥሰትና አገር ማፍረስ አለምአቀፍ ወንጀል ከስሩ ነቅሎ ሊቀብረው #በዋዜማው ላይ እንገኛለን። ስለሆነም ፋኖ እያደረገ ያለውን የህልውና ትግል #በድል እንዳይቋጭ  በድርድር፣ በእርቅና በምክክር ሰበብ የፋኖን ድል ለመቀልበስና ለመንጠቅ ከአሜሪካ እስከ አዲስ አበባና መቀሌ ድረስ በሚሸረብ ሴራ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ፤ በስልታዊ አማራነትም ሆነ በአማራ ጠልነት የተሰለፉ ቅጥረኞች ደፋ ቀና እያሉ እንደሚገኙ ግልፅ ነው። ፋኖ #አራት ኪሎን በመቆጣጠር ስርነቀል ለውጥ ለማወጅ በድል ዋዜማ ላይ ሆኖ እያደረገ ያለውን የመጨረሻውን ትንቅንቅ ለማሰናከልና ድሉን ለመሸጥ ተቀጥራችሁ ስለ ድርድር፣ ሽግግር፣ እርቅ፣ ውይይትና በመሳሰሉ አጀንዳዎች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ እየሰሩ የሚገኙ ቅጥረኞችን ከቀጣሪዎች እኩል ማሸነፍና ማስወገድ የህልውና ትግላችን ብቻኛ አማራጭ መሆኑ ለማንም ግልፅ ሊሆን ይገባል። ስለሆነም የዜግነት ፓለቲካ አቀንቃኝ የ3ኛ ወገን ቅጥረኞችን ከጀርባው አሰልፎ የአማራን ብሄርተኝነት የማድፈቅ አጀንዳቸውን አዝሎ ከአማራ ህልውና ትግል መሀል የተገኘው #እስክንድር ነጋ ከአማራ ህልውና ትግል ጓዙን ጠቅልሎ እንዲወጣ ማድረግ ለነገ የሚባል አይደለም። የእስክንድር ነጋ #የእየሱስ ክርስቶስነት ገፀ ባህሪ በሂደት እየተገፈፈ መምጣት አማራ ጠል ሀይሎችን ወደ እቅድ ሁለት ሴራ እንዲገቡ እያስገደደ በመሆኑ የአማራ ብሄርተኛ #እስክንድ...

አለም አቀፍ የፋኖ ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ነኝ የሚለው ቡድን ዓላማ ምንድነው ? በወንድወሰን ተክሉ

ይህ ምስል ጸሃፊውን አይወክልም! «...አማራ ለ450 ዓመታ መንፈሱ የተሰበረ ገበሮ ሕዝብ ነው..» ሀብታሙ ተገኝ (ፕ/ር) « እኔ እስክንድር  የአማራ ሕዝብ ከደረሰበት የህልውና አደጋ እኩል የሚሆን ዓላማ አለው ብዬ አላምንም» አቻምየለህ ታምሩ፤ አለም አቀፍ የፋኖ ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ነኝ የሚለው ቡድን ዓላማ ምንድነው ? በወንድወሰን ተክሉ እራሱን አለም አቀፍ የፋኖ ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ነኝ የሚለው ቡድን የዙም ውይይት ፕሮግራም ክፍል ሁለትን የተመለከተ ምልክታ:- ባለፈው  ወር ብቻ ሳይሆን ባለፈው ዓመት ዴሴምበር 2023 ( ዛሬ ጃንዋሪ 1 ቀን 2024 ነን)  እራሱን አለም አቀፍ የፋኖ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ብሎ የሚጠራው ቡድን «ጸረ አማራ ኢትዮጲያዊነት» በሚል አርእስት ስር ሀብታሙ ተገኝ (ፕ/ር) ዋና ተናጋሪ ተጋባዥ የሆነበትን  የዙም ውይይት አካሂዶ የነበረ ሲሆን የዚህ ውይይት ክፍል ሁለት  ባሳለፍነው ወር ዴሴምበር 23ቀን በማዘጋጀት አቻምየለህ ታምሩና ሀብታሙ ተገኝ (ፕ/ር) ተናጋሪ እንግዳ በማድረግ አካሂዷል። በእርግጥ  ከዚህ ከሁለተኛው የውይይት ፕሮግራም በፊት በተክሌ ይሻው በኩል የዙም ሊንክ ተልክሎኝ በሰዓት ጥበት ምክንያት መገኘት ባልችልም ዛሬ ግን በቻናላቸው ላይ የጫኑትን ይህን ክፍል ሁለት ውይይት ከተመለከትኩ በኋላ ይህን ምልክታዬን  አንባቢው ሊረዳ በሚያስችል መልኩ አንድ ሰዓት ከሰላሳ ደቂቃ የፈጀን ውይይት ይዘት በመጭመቅ እንደሚከተለው አቅርቤያለሁ። ይህ ምስል ጸሃፊውን አይወክልም! 1ኛ - ውይይቱን አዘጋጅን ማንነት በተመለከተ፦  አለም አቀፍ የፋኖ ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ባለፈው መስከረም ወር ላይ  በጌታቸው በየነ ሰብሳቢነት ተመሰረትኩ ብሎ እራሱን ያስተዋወቀ ሲ...