Skip to main content

ፋሺስቱ ኦህዴዳዊው ስርአት

አሜሪካ - የፋሺስቱ ኦህዴዳዊው አፓርታይዳዊው ስርአት - የከረፋ ወንጀሉን መደበቂያና የህዝብን ድጋፍ መዝረፊያ ፈፅሞ አትሆንም! በወንድወሰን ተክሉ

አሜሪካንን ፀረ ኢትዮጲያ የሚያደርግ ክስተትም ሆነ ፀረ አሜሪካዊ ኃይል በዛሬይቱ ኢትዮጲያ አለ?

በኢትዮጲያነት ስሜት የተሰራው የእስከዛሬው ወንጀል ስቃይና መከራ ከእንግዲህ ላይቀጥል መበጣጠስ ያለበት አሁን ዛሬ ነው:: ፋሺስቱ የአቢይ መራሹ አፓርታይዳዊ ስርአት ከጀሌዎቹ ኢዜማ ጋር በመሆን አሜሪካ ኢትዮጲያን እንደሊቢያ ልታደርግ የተነሳች ቀንደኛ ጭራቅ ናት በማለት የህዝብን attention እና ድጋፍ mobilize ለማድረግ ሲንቀሳቀሱ ታይቷል:: መንጋውም - በተለይ በተለይ ምንም መማር ያልቻለው በስሜት ጋላቢ መንጋ ይህንን መንግስት መር ፕሮፖጋንዳን በማስተጋባት ፈጥኖ ሲሰለፍ ታይቷል::

የግራፊክ ምስሉ ጸሃፊውን አይወክልም!


በእርግጥ አሜሪካ ኢትዮጲያን የመበትን አላማ እቅድና ፍላጎት አላትን ? ካላትስ ለምን እና እንዴት  ብሎ ከመጠየቅ የተወረወረለትን አጥንት ለቀም አድርጎ እንደሚሮጥ ውሻ እነዚህ መሰሪዎች የወረወሩለትን የሴራና የፈጠራ ወሬን ብድግ አድርገው ሲያራግቡ ይታያል:: ተመልከቱ ይህ ለብልፅግና መንግስት እነ XYZ የፖለቲካ ኃይሎች ይመቱ በሽብርተኝነት ይፈረጁ ሚዲያዎች ይዘጉ እያለ ጥናት በማቅረብ የኢትዮጲያን ሀገረ ዴሞክራሲን ግንባታን በማደናቀፍ ቀንደኛ ጨፍጫፊ ፋሺስት ስርአትን እየፈጠረ ያለው የኢዜማው ስብስብ ሀገር ወዳድ መስሎ እና እራሱን ለሀገር ተቆርቋሪ አድርጎ አሜሪካንን እየጠራ ሲፎክር አይታችሁ እንኳን መረዳት አትችሉምን?

የኢትዮጲያን ህልውና አደጋ ላይ የጣለው የአሜሪካ ተፅእኖ ሳይሆን የአቢይና ኢዜማ ፋሺስታዊ አምባገነንነት ሆኖ ሳለ ዛሬ እነዚሁ ስብስቦች ሀገር በአሜሪካ ጣልቃ ገብነት ልትፈርስ ነው ብሎ ሲያራግቡ እንዴት ነው በጭፍን ተቀብለን ልናስተጋባ የምንችለው? 

በግብፅና በሱዳን ተጠቅመው ተጠቅመው የፈለጉትን ታርጌት አላመታ ሲላቸው ሌላ ውጪያዊ ጠላት የሚደረግ ኃይለኛ ኃይል ፈለጉና ሰሞኑን በምርጫ ጉዳይ በትግራይ ጉዳይና በሀገሪቱ ውስጥ ባለው የሰብአዊ መብት አያይዝ ላይ ጠንከር ያለ አቋም ያንፀባረቀችውን አሜሪካንን ስም ብድግ በማድረግ ሀገሬ በአሜሪካን ጣልቃ ገብነት እንደሊቢያ አትሆንም ብሎ ማናፋት የህዝባችንን ንቃተ ግንዛቤን ከመናቅና የራሳቸውንም desperate የሆነን ድድብና የወለደው ጭንቀታቸውን ከማሳየት የዘለለ አንዳችም እውነታ አያሳይም

የአሜሪካ በኢትዮጲያ ላይ የከፈተችው ዲፕሎማሲያዊ ተጽእኖ መንስኤ ምንድነው? 

ሲጀመር አሜሪካንን ልክ የአጣዬንና የመተከልን አማራዊ መንደሮችን በጭካኔ ድምጥማጣቸውን እንዳጠፋው አቢይ መራሹ ሸኔ አይን አይቶ ሀገራችንን እንደሊቢያ ልታፈራርስ ነው ብሎ የጅል ሀሳብ ማሰብን ማቆም ተገቢ ነው፡፡

አሜሪካ የምታፈርስህም ሆነ የምትገነባህ ከሆነ ስለምትጠላህና ስለምትወድህ ሳይሆን በአንተ መፈራረስና በአንተ መገንባት የምታገኘውን ጥቅሟን ለማስጠበቅ ብላ የምታደርገው መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል፡፡ የአሜሪካን የውጪ ፖሊሲ እሚፈልቀው ከወዳጅነትና ከጠላትነት እሳቤ ሳይሆን ከአሜሪካን ጥቅም ኩሬ ውስጥ የሚቀዳ ፖሊሲ ያላት ሀገር ናት፡፡

በምስራቃዊው የአፍሪካ ቀንድ ባለ 117ሚ ህዝብ ባለቤት የሆነችውን ኢትዮጲያ ሀገራዊ ህልውና እና የተዋሃደች አንድ ሉአሏዊ ሀገርነቷ ይልቅ የፈራረሰችና የተበታተነች ኢትዮጲያ የአሜሪካን ጥቅም የሚከበርባት ናት ብሎ የሚያስብ ሰው ካለ ይህ ሰው አንድ ጅሉ ሞሞ ቂሎ ወይም ሞሮን አሊያም በአሜሪካን ማስፈራሪያነት ለመነገድ ያሰፈሰፈ አጭበርባሪ ሴረኛ ሰው ብቻ ሆኖ እናያለን፡፡

ዛሬ አቢይ መራሹ መንግስትና አሜሪካ በጥሩ ሁኔታ ላይ ያለመሆናቸው ጉዳይ እውነት ነው፡፡ የተጽእኖ መንስኤ -ማለትም አሜሪካንን በኢትዮጲያ ጉዳይ አሳስቦ ጣልቃ እንድትገባ ያደረጓት አስገዳጅ ነጥቦች 

1ኛ) በኢትዮጲያ ላይ የተጋረጠው የመፍረስ አደጋ 

2ኛ) ቀጠሮ የተያዘለት የምርጫው ጉዳይ

3ኛ) የትግራይ ጉዳይ ማለትም፦

  • በትግራይ ያለው የሻእቢያ ሰራዊት ጉዳይ

  • በትግራይ ያለው ርሃብና ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ረጋጣ ጉዳይ

  • በአማራ ልዩ ኃይል ጉዳይ

  • በትግራይ እየተካሄደ ስላለው የሽምቅ ውጊያ 

4ኛ) በአማራ በኦሮሚያ በቤኒሻንጉል ስለተፈጸመው ጭፍጨፋ ጉዳይ

5ኛ) በሱዳን እና ኢትዮጲያ እና በግድቡ ጉዳይ ላይ የአሜሪካን ስጋት ተንጸባርቋል፡፡

ከዚህ ውስጥ ስሰአማራ ልዩ ኃይል ጉዳይ ማለትም የአማራ ልዩ ኃይል ከወልቃይት ጠገዴ ራያ ይውጣ ከሚለው ስህተቷ በስተቀር ያቀረበቻቸው ስጓቶቿ በሙሉ ሁላችንም የምንጋራውና እያሳሰቡን ያሉ ሀገራዊ አደጋዎች መሆናቸው ግልጽና እውነት ነው፡

በዚህም መሰረት አሜሪካ ለሀገራችን አስባ ተጨንቃና ተቆርቁራ ሳይሆን ለራሷ ጥቅም ብላ የ117ሚ ህዝብ ሀገር የሆነችው ኢትዮጲያ መፍረስ የራሷን ጥቅም የሚጎዳ መሆኑን በመሆኑ ይህንን ሀገራዊ መፍረስን አደጋ ለማስቆምና ለማስቀረት ያግዛል ብላ የነደፈችውን ፕሮፖዛል ለአቢይ በማቅረብ እንዲተገብረው ተጽእኖ እያደረገች ያለች ሆኖ ሳለ እነቆርጦ ቀጥል ብልዜማዎች -ብልጽግና እና ኢዜማ ተብዬዎች ግን አሜሪካን ኢትዮጲያን ልክ እንደሊቢያ ለማፈራረስ እንደተነሳች አድርገው ሲያስተጋቡ ለመስማት ነው የተቻለው፡፡

ይህንን የአሜሪካንን ተጽእኖን እኛ የአማራ ልጆች በጥልቀት በጥንቃቄ በመከታተል ከምናደርገው የህልውና ትግል አኳያ ለትግላችን ለህዝባችን የሚጠቅም አቋምን በተናጥል መያዝ ይገባናል እንጂ እንደግሪሳ መንጋ ሀገር ተደፈረች በሚል ማጭበርበሪያዊ ጩህት ታውረን መንጋውን መቀላቀል ፈጽሞ አይገባንም-አይጠበቅብንምም፡፡

የእኛን የአማራን ህዝብ የህልውና ትግልና አማራዊ ጥቅምን ሊጻረር የሚችለው አንድ ነጥብ ብቻ ሲሆን ያም የጀግኖቻችን የአማራ ልዩ ኃይል ከግዛታችን ወልቃይት ጠገዴ ሁመራና ራያ ይውጣ የሚለው ያልተጠና አባባል በስተቀር በአሜሪካ በኩል የተንጸባረቁት ስጋቶች በሙሉ ለትግላችን ደጀን ሆኖ የሚደገፈን እንጂ የሚጊጎዳን ፈጽሞ አይደለም፡፡

የተመለሱ ግዛቶቻችንን በተመለክተ እያንዳንዱ አማራ ማወቅ ያለበት መመሪያ ግዛታችንን የሚያስጠብቀው አቢይም ሆነ ሌላ ኃይል ሳይሆን የእኛው የአማራ ህዝብ ብቻና ብቻ መሆኑን ማወቁ ላይ ነው፡፡

መሬታችንን ህወሃት ከሰላሳ አመት በፊት የወሰደችው አማራ ብልተደራጀበት በጉልበቷና በኃይል ሲሆን ዛሬም በእጃችን ያስገባነውን ግዛታችንን የሚነጥቀን የአሜሪካን ትእዛዝዛ የአቢይ ሴራ ሳይሆን የእኛ የአማራ ልጆች ተጠናክሮ ተደራጅቶ መገኘት ብቻ ነው፡፡

እናም የአማራው የህልውና ትግል የአሜሪካንን ወዳጃነትና ድጋፍፍን ይፈልጋል እንጂ ለፋሺስቱ አቢይና ኢዜማ ጥቅምና  ስልጣን ብሎ  አሜሪካንን እያወገዘ ጠላት የሚፈጥርበት ሁኔታ ላይ አይደለንም፡፡


Comments

Popular posts from this blog

"ከአሁን በሆላ ፋኖ ወደ አንድነት መምጣት አለባቸው የሚባለው አካሄድ አይሰራም" :: በወዳጄ/ቤተ አማራ ወሎ

ከአሁን  በሆላ  ፋኖ  ወደ  አንድነት    መምጣት  አለባቸው  የሚባለው  አካሄድ  አይሰራም::  ክህደት   ከተፈፀመ  በሆላ  አንዱ  ቡድን  ከሌላው  ስር  ሆኖ  ይቀጥላል  ማለት  የማይቻል   ነው::  ምክኒያቱም 1ኛ:- 27  ቀን  ቁጪ  ብለው   መክረዋል :: እያንዳንዱ  አደረጃጄት  ሰነድ  ፅፈው  አቅርበዋል::  በቀረበው  ሰነድ  ላይ  ከፍተኛ  ውይይት  ተደርጎበት  የሚወድቀው  ወድቆ  የሚፈለገው  ፀድቋል::ቃለ  መሀላ  ፈፅመው   ወደ  ምርጫ   ለመግባት  ተስማምተዋል:: እጃቸውን  አውጥተው   ከመረጡ  በሆላ    ግን    "ጨዋታ  ፈረሰ  ዳቦ  ተቆረሰ"   የሚል  የህፃን  ልጂ  ጨዋታ  ውስጥ  መግባት   የአማራን  ህዝብም  ሆነ  የፋኖን  ትግል  መናቅ  ነው:: ይህ  አልበቃ  ብሎ   "ምርጫው  ከኛ  እውቅና  ውጪ  ነው  እኛ  አናውቀውም"  የሚል   የውሸት    የህፃን  ልጂ  ፕሮፓጋንዳ...

ስርነቀል ለውጥ ማምጣት የአማራ ብሄርተኝነት የህልውና ትግል ብቸኛ ግብ ነው። በ Alen Kassahun

ምስሉ ጸሃፊውን አይወክልም፡፤ ከ50 አመታት በላይ የተተከለውንና በተግባር እየተፈፀመ ያለውን አማራን ማጥፋትና ኢትዮጵያን ማፍረስ ከስሩ በመንቀል #4ኪሎን ተቆጣጥሮ ስርነቀል ለውጥ ማምጣት የአማራ ብሄርተኝነት የህልውና ትግል ብቸኛ ግብ ነው። ፋኖ በሚያደርገው የህልውና ትግል አማራ ጠልነት የወለደውን የአማራን ዘር ማጥፋት፤ ማፅዳት፤ የሰባዊ መብት ጥሰትና አገር ማፍረስ አለምአቀፍ ወንጀል ከስሩ ነቅሎ ሊቀብረው #በዋዜማው ላይ እንገኛለን። ስለሆነም ፋኖ እያደረገ ያለውን የህልውና ትግል #በድል እንዳይቋጭ  በድርድር፣ በእርቅና በምክክር ሰበብ የፋኖን ድል ለመቀልበስና ለመንጠቅ ከአሜሪካ እስከ አዲስ አበባና መቀሌ ድረስ በሚሸረብ ሴራ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ፤ በስልታዊ አማራነትም ሆነ በአማራ ጠልነት የተሰለፉ ቅጥረኞች ደፋ ቀና እያሉ እንደሚገኙ ግልፅ ነው። ፋኖ #አራት ኪሎን በመቆጣጠር ስርነቀል ለውጥ ለማወጅ በድል ዋዜማ ላይ ሆኖ እያደረገ ያለውን የመጨረሻውን ትንቅንቅ ለማሰናከልና ድሉን ለመሸጥ ተቀጥራችሁ ስለ ድርድር፣ ሽግግር፣ እርቅ፣ ውይይትና በመሳሰሉ አጀንዳዎች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ እየሰሩ የሚገኙ ቅጥረኞችን ከቀጣሪዎች እኩል ማሸነፍና ማስወገድ የህልውና ትግላችን ብቻኛ አማራጭ መሆኑ ለማንም ግልፅ ሊሆን ይገባል። ስለሆነም የዜግነት ፓለቲካ አቀንቃኝ የ3ኛ ወገን ቅጥረኞችን ከጀርባው አሰልፎ የአማራን ብሄርተኝነት የማድፈቅ አጀንዳቸውን አዝሎ ከአማራ ህልውና ትግል መሀል የተገኘው #እስክንድር ነጋ ከአማራ ህልውና ትግል ጓዙን ጠቅልሎ እንዲወጣ ማድረግ ለነገ የሚባል አይደለም። የእስክንድር ነጋ #የእየሱስ ክርስቶስነት ገፀ ባህሪ በሂደት እየተገፈፈ መምጣት አማራ ጠል ሀይሎችን ወደ እቅድ ሁለት ሴራ እንዲገቡ እያስገደደ በመሆኑ የአማራ ብሄርተኛ #እስክንድ...

አለም አቀፍ የፋኖ ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ነኝ የሚለው ቡድን ዓላማ ምንድነው ? በወንድወሰን ተክሉ

ይህ ምስል ጸሃፊውን አይወክልም! «...አማራ ለ450 ዓመታ መንፈሱ የተሰበረ ገበሮ ሕዝብ ነው..» ሀብታሙ ተገኝ (ፕ/ር) « እኔ እስክንድር  የአማራ ሕዝብ ከደረሰበት የህልውና አደጋ እኩል የሚሆን ዓላማ አለው ብዬ አላምንም» አቻምየለህ ታምሩ፤ አለም አቀፍ የፋኖ ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ነኝ የሚለው ቡድን ዓላማ ምንድነው ? በወንድወሰን ተክሉ እራሱን አለም አቀፍ የፋኖ ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ነኝ የሚለው ቡድን የዙም ውይይት ፕሮግራም ክፍል ሁለትን የተመለከተ ምልክታ:- ባለፈው  ወር ብቻ ሳይሆን ባለፈው ዓመት ዴሴምበር 2023 ( ዛሬ ጃንዋሪ 1 ቀን 2024 ነን)  እራሱን አለም አቀፍ የፋኖ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ብሎ የሚጠራው ቡድን «ጸረ አማራ ኢትዮጲያዊነት» በሚል አርእስት ስር ሀብታሙ ተገኝ (ፕ/ር) ዋና ተናጋሪ ተጋባዥ የሆነበትን  የዙም ውይይት አካሂዶ የነበረ ሲሆን የዚህ ውይይት ክፍል ሁለት  ባሳለፍነው ወር ዴሴምበር 23ቀን በማዘጋጀት አቻምየለህ ታምሩና ሀብታሙ ተገኝ (ፕ/ር) ተናጋሪ እንግዳ በማድረግ አካሂዷል። በእርግጥ  ከዚህ ከሁለተኛው የውይይት ፕሮግራም በፊት በተክሌ ይሻው በኩል የዙም ሊንክ ተልክሎኝ በሰዓት ጥበት ምክንያት መገኘት ባልችልም ዛሬ ግን በቻናላቸው ላይ የጫኑትን ይህን ክፍል ሁለት ውይይት ከተመለከትኩ በኋላ ይህን ምልክታዬን  አንባቢው ሊረዳ በሚያስችል መልኩ አንድ ሰዓት ከሰላሳ ደቂቃ የፈጀን ውይይት ይዘት በመጭመቅ እንደሚከተለው አቅርቤያለሁ። ይህ ምስል ጸሃፊውን አይወክልም! 1ኛ - ውይይቱን አዘጋጅን ማንነት በተመለከተ፦  አለም አቀፍ የፋኖ ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ባለፈው መስከረም ወር ላይ  በጌታቸው በየነ ሰብሳቢነት ተመሰረትኩ ብሎ እራሱን ያስተዋወቀ ሲ...