የአቢይ መንግስት ፀረ አማራዊ ጋዜጠኞች አክትቪስቶችና ተሟጎቾች ዘመቻ! የአቢይ መራሹ የብልፅግና መንግስት የመከላከያ ሰራዊቱን ቅሌታዊ ሽንፈትን ተከትሎ በአስር ሺህ የሚቆጠሩ የመከላከያ አባላትንና ብሎም ሲቪል ባለሙያዎችንና የዩንቨርስቲ ተማሪዎችን አዘርክርኮ ከትግራይ በፈረጠጠ ማግስት በአማራ አክትቪስት ጋዜጠኞችና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ላይ በመዝመት ጋሽ ታዲዮስ ታንቱን ጨምሮ ከአስር በላይ ጋዜጠኞችን በኢትዮጲያ አፍሶ ያሰረ ሲሆን በተመሳሳይ ቁጥር የሚሆኑ የማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎችን አካውንትን በዘመቻ መልክ ለማስዘጋት መቻሉን ማወቅ ተችሏል::
ይህ የግራፊክ ምስል ጸሃፊውን አይመለከትም |
ከጋዜጠኛ Getachew Shiferaw ሺፈራው ጀምሮ ጋዜጠኛና አክትቪስት Wondwossen Teklu Wondelove የሰብአዊ መብት ተሟጋች ቤተልሄም ዳኛቸው Yodith Gideon Dave Dawit Asaminew Tsige Follower Melkamu Shumye Loul Mekonnen Bahailu_Tessema
Tina Belay bahailu_tessema Kidist_Garumha እና የመሳሰሉትን በርካታ አማራዊ አካውንቶች በአጭር ተመሳስይ ቀናት ውስጥ ማዘጋት የመቻሉ ጉዳይ የአቢይ መራሹን መንግስት በአማራ ጉዳይ ላይ የመዘዘውን አዲስ ሰይፍ ያመላክታል:: አማራዊያን ጋዜጠኞች አክትቪስቶችና የሰብአዊ መብት ተሟጏቾች በአቢይ ጥርስ ውስጥ እንዲገቡ ያደረጋቸውና አቢይ ከህዝብ ጆሮ ለመደበቅ የፈለገው ምንድነው?
የአቢይ መራሹ የኦህዴድ ብልፅግና መንግስት የመከላከያ ሰራዊቱን እያክለፈለፈ ከትግራይ ያወጣበት ሂደት ምክንያትና ብሎም በክስተቱ ግንባር ቀደም ተጠቂና የውሳኔው ገፈት ቀማሽ የአማራ ህዝብና የመከላከያ ሰራዊቱ አባላት በመሆናቸው ይህ ሁለት የህብረተሰብ ክፍል የመንግስትን ምስጢራዊ እርምጃን እንዳያውቅ ለማድረግ መንግስት ይህንንን እውነት ለህዝብ በማቅረብ ደረጃ ላይ ተግተው በሚሰሩት ጋዜጠኞች አክትቪስቶችና የሰብአዊ መብት ተሟጏቾች ላይ በማነጣጠር ልሳናቸውን ለመዝጋት እንዲጥር አድርጎታል::
አቢይ መራሹ የኦህዴድ ብልፅግና መንግስት ከአቻ የብልፅግና አባላት ማለትም ከአማራው ብልፅግና ብአዴን እና ከመከላከያ ሰራዊቱ እውቅና እና ምክክር ውጪ ከትህነግ ጋር በሚስጢር ሲያደርግ በነበረው ምስጢራዊ ድርድርና ብሎም በጦር ግንባር በደረሰበት እሰቃቂ ሽንፈት ምክንያት እጅግ ግብታዊ ያልተጠና እና በወታደራዊ ሳይንስ እቅድና ስልት ሳይወጣለት በቅስፈታዊ ድንገት ከትግራይ ለቅቆ በመውጣቱ በአስርሺህ የሚቆጠር የመከላከያ ሰራዊት ህይወት ተቆርጦ በመቅረትና ተማርኮ አደጋ ላይ እንዲወድቅ ከማስቻሉም በላይ በአጠቃላይ በአማራ ህዝብ ላይ አዲስ የጥቃት አደጋን የደቀነ በመሆኑ መንግስት ጉዳዩን አዳፍኖ ለማስቀረት ሲል በአማራዊያኑ ጋዜጠኞችና አክትቪስቶች ላይ ለመዝመት እንደቻለ መረዳት ተችሏል::
በዚህ እርምጃውም የአቢይ መራሹ መንስት የሚጨነቀውና የሚጠበበው ህዝብና ሀገር የሚጎዳ የስህተት ውሳኔና ፖሊሲን ከማስተላለፍ ይልቅ የሰራውን ጥፋትና ውድመትን የምያጋልጡበትን ሰዎችና ባለሙያዎች ላይ አነጣጥሮ በማጥቃት እውነታውን ማዳፈን ላይ መሆኑን ተግባሮቹ በትክክል ይመሰክራሉ:: ለምንድነው በአስርሺህ የተቆጠሩ የመከላከያ አባላትና ሲቪሊያን ህይወት ሰለባ በሆነበት ጦርነት ላይ ትኩረት እና ጥንቃቄን ከማድረግ ይልቅ እሱ በእንዝህላልነት በግዴለሽነት በብቃት ማነስና ወዘተ ምክንያቶች በፈጠረው ስህተት የተፈፀመን ሀገርና ህዝብ አፍራሽ ተግባራትን የሚያጋልጡት ላይ ለማነጣጠር የፈለገው ?
የአቢይ መራሹ ኦህዴድ/ብልፅግና መንግስት በአማራ ጋዜጠኞች አክትቪስቶችና የሰብአዊ መብት ተሟጏቾች ላይ በማነጣጠር ዘመቻ ቢከፍተም እሱ ሊደብቀው የፈለገውን እውነት ግን ፈፅሞ ሊደብቅ እንደማይቻለውና ህዝባችንም ማወቅ የሚገባውን እውነት እንዲያውቅ ከማድረግ አኳያ ፈፅሞ ሊያቆመን እንደማይቻለው ደጋግመን ልገልፅለት እንወዳለን::
በመንግስት በጎፈቃድና ይሁንታ እውነትን የምንገልፅና የምንደብቅ ሳይሆን ባለን እማይሻር እማይግሰስና ከቶም እማይሸራርፍ ተፈጥሮአዊ መብታችንና በግልና በማህበረሰብ ፍላጎታችን ብቻ ተመርኩዘን የምንገልፅ መሆናችንን ማንም - ወዳጅም ጠላትም- ሊያውቅ ይገባል:: እውነትን በማፈን ሳይሆን ፍትሃዊ መሆን የሚቻለው ፍትሃዊ ስራን በመስራት ብቻ እና ብቻ ነው!
ድል ለሰፊው የአማራ ህዝብ!
Comments