Skip to main content

"ምኗ ላይ ተቀምጣ በሽንቷ ሰፌድ ትሰፋላች":- አዲሱ የአቢይ ካቢኔ አሰያዬም ፤ በሸንቁጥ አየለ

ችግሩ ያለዉ የጎሳ ፖለቲካ ርዕዮተ ፍልስፍናዉ ላይ ነዉ::ኢትዮጵያዉያንን ሀገር አልባ ያደረገዉን የጎሳ ፖለቲካ ፍልስፍና መሰረት ላይ የቆመ ካቢኔ ምንም አይነት መልካም ግለሰቦችን ሰብስብቦ ቢያቅፍ ከቶም የሀገር መድሃኒት አያመጣም::

ሆኖም የዚህ ስርዓት የጥቅም ተጋሪዎች እና እግር አጣቢዎች ይሄን የጎሳ ፖለቲካ አስተሳሰብ የተለያዬ የማስመሰያ መቀባቢያ በመቀባት ጸረ ሰዉ የሆነዉን የጎሳ ፖለቲካ አስተሳሰብ ለማስቀጠል እና ህዝብን ለማምታታት ብዙ ሲዳክሩ ይሰተዋላል::በአዲሱ የአቢይ ካቢኔ አሰያዬም የተከናወነዉ ድራማም ይሄዉ ነዉ::

እከሌ ከኦህዴድ:እከሌ ከብአዴን:እንትና ከአብን : እንቶኔ ከኢዜማ: እንቶኔ ደግሞ ከትግራይ ብልጽግና ተሾሙ እያሉ ብዙ የጥቅም ተጋሪዎች እና የአገዛዙ ሚዲያ ብዙ ይቀባጥራሉ::በደስታም እንኳን ደስ አለህ ይባባላሉ::ኢትዮጵያዉያን ግን አሁንም ሀገር አልባ ናቸዉ::

የኢትዮጵያ የችግር ምንጭ ሁሉ አንድ ነዉ::ይሄዉም የጎሳ ፖለቲካ ፍልስፍና ነዉ::መለስ ዜናዊ የሀገሪቱን ጥፋት ያመጣዉ የጎሳ ፖለቲካ ፍልስፍና በማራመድ ነበር::መለስ ዜናዊ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሆኖ በስሩ ብዙ በግለሰብ ደረጃ መጥፎ የማይባሉ ሰዎችን በካቢኔዉ ዉስጥ ሰግስጎ ነበር::

ሆኖም የመለስ ዜናዊ ካቢኔ እያንዳንዱ የሚመራበት መርህ በጎሳ ፖለቲካ ፍልስፍና እና ቀመር ስለሆነ የሚሰሩ ስራዎች ሁሉ በዚሁ መርዛማ ህሳቤ ዙሪያ የሚሽከረከሩ ነበሩ::

አሁንም አቢይ የሾማቸዉ ሰዎች መጥፎ ናቸዉ ጥሩ ናቸዉ የሚለዉ አይደለም ጥያቄዉ:: ወይም ደግሞ ሰዎች ከዬትኛዉ ፓርቲ ተመርጠዉ ተሾሙ አይደለም ጥያቄዉ::

አቢይ የሚመራበትም የፖለቲካ ፍልስፍና እንደ መለስ ዜናዊ ሁሉ የጎሳ ፖለቲካ ፍልስፍና ነዉና ያዉ ዉሃ ቢወቅጡት እንቦጭ ነዉ::ስለዚህ የተሿሚዎቹ መልካምነት ወይም የመጡበት የፓርቲ ቁም ነገር አይደለም::

ግለሰብ አምላኪ ለሆኑ ሰዎች ግን ይሄ የሰዎች የሹመት ቦታ መለዋወጥ ምናልባት እንደ ቁምነገር ይታያቸዋል::አንዳንዱ ከአዲስ ትሿሚዎች ጋር ያለዉን ትሥስር እያንሰላሰለ ምን ጥቅም እንደሚያገኝ በማሰብ ሽቅብ ሽቅብ እየዘለለ በደስታ ሰክሯል::ኢትዮጵያዉያን ግን አሁንም ሀገር አልባ ናቸዉ::

ዋናዉ ነጥብ የኢትዮጵያ መከራዋ እና ህመሟ የተቋጠረዉ ከጎሳ ፖለቲካ ፍልስፍና ጋር ነዉና እጎሳ ፖለቲካ ፍልስፍና ላይ ቆሞ እስክስታ የሚመታ ምንም አይነት ካቢኔ ሀገር የሚያድን መድሃኒት ይዞ አይመጣም::

ስለዚህ አቢይ ጀግና ከሆንክ እና የኢትዮጵያን ህመም ማዳን ከፈለግህ የጎሳ ፖለቲካ ፍልስፍናህን በአዋጅ ለዉጥ::ኦህዴድህን አክስም::ካንተ ጋር ያሉ የብልጽግና የጎሳ ፓርቲዎችን እንዲሁም አጋር የጎሳ ፓርቲዎችህም የጎሳ ፓርቲያቸዉን ያክስሙ::የጎሳ ፖለቲካ በህግ ይታገድ::የጎሳ ህገ መንግስታችሁን አፍርሳችሁ በሌላ ቀይሩ::የጎሳ ክልላዊ አስተዳደራችሁን አፍርሱና ኢትዮጵያዉያን ሁሉ ሀገር እንዲኖራቸዉ በሚያደርግ መልክዓ ምድራዊ አስተዳደር ተኩት::ያን ጊዜ የኢትዮጵያዉያን ሁሉ መሪ ትሆናላችሁ:: 

ከዚያ ዉጭ አዲስ ካቢኔ እያላችሁ የምትዘባበቱ ነገር ሁሉ "ምኗ ላይ ተቀምጣ በሽንቷ ሰፌድ ትሰፋላች" እንደሚባለዉ አባባል ዝም ብሎ የገማ የጎሳ ፖለቲካ ካንሰራማ ዉሃ ዉስጥ መንቦጫረቅ መሆኑን እወቁት::እንኳን ሀገር ልታድኑ እናንተንም መዝምዞ የሚያጠፋ መርዛማ ህሳቤ ዉስጥ እየተንቦጫረቃችሁ መሆኑን እወቁት::

ኢትዮጵያን እግዚአብሄር ይባርክ !

Comments

Popular posts from this blog

የጋራ ጠላታችንን ልናሸንፈው የምንችለው ብአንድነት ብቻ ነው:: ሻ/ቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ

ከዚህ መከፋፈል ነፃ ሆነን ፊትለፊት  እየወረረ : እየገደለን: ያለውን የጋራ ጠላታችንን ልናሸንፈው የምንችለው ብአንድነት ብቻ ነው:: ሻ/ቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ ሻ/ቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ በምናየው  ታላቅ  የፋኖ ትግል የዲያስፓራ ትልቁ ስራ ገንዘብ መስብስብ ነው:: እሱም እየቀዘቀዘ ሄዷል:: ጦርነቱን ያራዝምነው እኛው ነን:: ይህ ደግሞ ትልቁና ዋናው የጠላት ስትራተጂ ነው:: ጦርነቱን ማራዘምና ከአማራ ምድር እንዳይወጣ በማድረግ: ፋኖን በመከፋፈል አዳክመዋለሁ ! እበትነዋለሁ ! የሚል የአቢይ አህመድ ትልቁ  የወቅቱ ስትራተጂ መሆኑን ተረድተናል::: በዚህም ምክንያት በአጠረ ጊዜ  ሊጠናቀቅ የሚችለውን  ትግል  ዲያስፓራ በምቀኝነት: በቅናት: በሌለ  ስልጣን  ላይ በመፋተግ: በተቀጣሪነት: በጠባብ አስተሳስብ: ትግላችንን ወደኋላ  በመጎተትና  እንዲራዘም ብሎም እንዲዳከም በማድረግ ታሪካዊ ወንጀል እየስራ ነው:: ከዚህ መከፋፈል ነፃ ሆነን ፊትለፊት  እየወረረ : እየገደለን: ያለውን የጋራ ጠላታችንን ልናሸንፈው የምንችለው በአንድነት ብቻ ነው::  አሸናፊነት ትብብርና  የጋራ ስትራተጂ ይጠይቃል:: የተግባር ዲያስፓራ እንሁን:: አማራን እንደ  ህዝብ ኢትዮጵያንም እንደ ሀገር  ለማዳን  ዋናው መሳሪያችን  አንድነት ነው:: በውስጣችን ያለውን ልዩነት በመጠቀም  አገራችንን ለማጥፋት: በአካባቢያችን  ያለውን የሀይል አሰላለፍ ስንመለከት ፍፁም ፍፁም  አደገኛ  መሆኑን እንገነዘባለን:: በዲያስፓራ  መጨቃጨቅና መዘላለፍ  እንደ ባህልና እንደ ትልቅ   የጦርነት ስትራተጂ ተደር...

ዐማራን ወክሎ ከወያኔ ጋር ስለሰላምም ሆነ ስለትጥቅ ትግል አልፎም ስለመንግሥት መሥረታ መነጋገር ፈጽሞ አይቻልም

ዐማራን ወክሎ ከወያኔ ጋር ስለሰላምም ሆነ ስለትጥቅ ትግል አልፎም ስለመንግሥት መሥረታ መነጋገር ፈጽሞ አይቻልም፤ ዐማራ የተጨፈጨፈው በሦስት ዓመት ዕድሜ ውስጥ ብቻ አይደለም። በ17 ዓመት የወያኔ የሽፍተነት ዘመን፣ 27 ዓመት የወያኔ የመንግሥትነት ዘመን ወደኋላ ተጨምሮ ነው። ከውያኔ ጋር ሰላምን ወይም ትጥቅ ትግልን እናደርጋለን የሚሉ ሁሉ ውሾች ናቸው። "ውሻ ወደ ትፋቱ ይመለሳል" በምሣሌ 26፤11 እና 2ኛ ጴጥሮስ2፤22 የተጠቀሰውን መጽሐፋዊ ዘገባ በማንበብ ከውያኔ ጋር የመከሩትን የውሾች ባህሪ ለይቶ መረዳት ነው። ምስሉ ጸሃፊውን አይወክልም 1ኛ. የዐማራን ሕዝብ የመደብ ጠላት አድርጎ ወያኔን በደደቢት የመሠረተውና 17 ዓመት በትጥቅ ትግል 27 ዓመት በመንግሥትነት በደምሩ 44 ዓመት ከሰባት ሚሊዮን በላይ ዐማራን ሕዝብ ያለማቋረጥ ያስጨፈጨፈ፣ ርስቱን የነጠቀ በጀምላ የገደለ ያፈናቀለ፣ የትግራይን ሕዝብ ከኢትዮጵያዊ ቀዳሚ ሕዝብነቱና ማንነቱ ያስከዳ ስብሐት ነጋ ፤   2ኛ. ከዐማራ ሕዝብ ይልቅ የሱዳን ሕዝብ ይሻለናል ብሎ በማይካድራ በጭና ዐማራን በከፍተኛ መራር በሆነ ጭካኔ ያስጨፈጨፈው፣ በመጨረሻ ተረጋግቶ መኖር ሲችል ዕቅድና ዓላማ በሌለው ጦርነት አንድ ሚሊዮን የትግራይ ወጣት ያስጨፈጨፈ፣ የትግራይን ሕዝብም ሆነ የዐማራን ሕዝብ አዘቅት ውስጥ የከተተ ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ፤   3ኛ. የወያኔ ተሿሚ ሆኖ የዐማራን መሬት ፀገዴና ጠገዴ እያለ እየከፋፈለ ለወያኔ ያስረከበ፣ የግጨውን መሬት ለወያኔ በችሮታ ፈርሞ የሰጠ፤ እነ ዶክተር አባቸው ለማስገደል ቅድመ ሁኔታዎችን ከአመቻቸ በኋላ ወደ አሜሪካ ሀገር ሾልኮ ወጥቶ ከተገደሉ በኋላ ተመልሶ ጥቁር ለብሶ የዓዞ እንባ ሲያነባ ሲመጻደቅ የነበረ የሕወሀትም ሆነ የብልጽግና ቀንደኛና ፊ...

በጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)

ሻለቃ ዳዊትን በተለያዩ ምክንያቶችና ወቅቶች እንደ እኔ የተቻቸው ፈልጋችሁ አታገኙም። ያ ወቅት ሌላ ፤ ዛሬ ሌላ፤- ያ ዘመን ከ2010 ዓ.ም በፊት ነው። ሰው የነበረውን መስመር አስተካክሎ ባዲስ አካሄድ ወቅቱ በሚጠይቀው ጎዳና ከተራመደ ሌላ ምን ይፈለጋል? ዛሬ ግን ሻለቃው “ኢምፖስተር” በማለት የሚጠሩት ህቡእና ግልጽ ነብሰገዳይ ቡድን አሰማርቶ ነብስን የሚቀጭና የሚሰውር <<የወያኔ የነገድ አስተዳዳር አስቀጣዩ የኦሮሙማው የጋጠወጥ ማፍያዎች መሪ>> አብይ አሕመድ ከነገሠ ወዲህ ግን “ሻለቃው” አብይ አሕመድን እንቅልፍ ካሳጡት አርበኞች አንዱ ሆነው ብቅ ብለዋል። ያንን በማድረጋቸው “ጥበብ ሳሙኤል” የተባለ የአብይ አሕመድ አለቅላቂና ፀረ አማራና የሕግ ሙያ ትምሕርተ አለበት ተብሎ የሚነገርለት (?) ጋዜጠኛ:- አብይ አሕመድን በመደገፍ በሻለቃው ላይ ያለ ዕረፍት ረዢም ጊዜ ሲዘልፋቸው ያስገረመኝ ያህል፤ ሰሞኑን ደግሞ በሻለቃ ዳዊት ወ/ልደጊዮርጊስ ላይ አዳዲስ ዘላፊዎች ብቅ ብለዋል። “ሻለቃ ሆይ! በትግሉ ውስጥ ዛሬ ይኑሩ አይኑሩ አማራውን ለመታደግ ከፍታዎትን አሳይተዋል ፤የበኩልዎን አድርገዋል ለዚህም <<በአክብሮት ባርኔጣየን አነሳለዎታለሁ፤ አንኳን ደስ አለዎት !!!!>> አርበኛ ብቅ ባለ ቁጥር ሱሪውን የሚጎትቱ ብዙ የፖለቲካ ተውሳኮች አሉ። ሻለቃው በዛው ዕደሜአቸው የሚቻላቸውን በማድረጋቸውና ከፍታቸውን በማሳየታቸው ፤ ይህን በማድረጋቸው ዓይናቸው ከቀላ ውስጥ አንዱ ወደ “ጥንት ትፋቱ” የተመለሰው፤ በቅርቡ ከወያኔም ከኦነጎችም እየተወዳደሰ መተፋፋግ የጀመረው የወያኔው አሽከር “ኤርሚያስ ለገሰ” እና ዶ/ር አምሳሉ የተባለ “ከጎንደሬዎች እጅህን አንሳ” እያለ ሲከራከረኝ የነበረው እስከ ቅርብ ጊዜ ወዲህ የአብይ አሕመድ አወዳሽ የነበ...