Skip to main content

የአማራ እንቅስቃሴ

ይህ ጊዜ የአማራ ሕዝብ ከጨለማ ዘመን ወደባሳ የጨለማ ዘመን የገባበት ዘመን ነው ። በሕዝባችን ላይ በታወጀው የጥፋት አዋጅ ፣ በርካቶች በአማራነታቸው የታረዱበት ፣ ቤት ንብረታቸውን በትነው ለዘመናት ከኖሩባቸው አካባቢዎች የተፈናቀሉበትና በአገራቸው ባይተዋር ሆነው እንዲኖሩ የተወሰነበት የክፉ ዘመን መጀመሪያ ነው።

የአማራ ሕዝብ በጨካኝ ቡድኖች ታይቶና ተሰምቶ በማይታወቅ መልኩ መጠነ ሰፊ ውርጅብኝ እየወረደበትና  በግልጽ የዘር ማጥፋት ወንጀል  እየተፈጸመበት ይገኛል ። ለሕዝባችን የሚጮህለት ኃይል የለም። የሕዝባችን በደል የሚገደው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅትም አልተገኘም ። የአብይ አህመድ  አሸባሪ መንግስት ወዳጅ የሆኑ ኃያላን አገሮችም በሕዝባችን ላይ የታወጀውን የዘር ፍጅት እያዩ እንዳላዩ ማለፍን መርጠዋል። በአጭሩ ለአማራ ሕዝብ ከራሱ ውጪ ማንም እንደማይጮህለት፣ ማንም እንደማይገደው በሚገባ ተረጋግጧል። ለዚህ ነው ሕዝባችን በሕዝብ ደረጃ ተደራጅቶ ከመታገል ውጪ ምርጫ የለውም የምንለው። 



ከዘመነ ወያኔ ጅምሮ እስከ ዘመነ ኦህዴድ/ብልጽግና እንደአማራ ሕዝብ የተበደለ፣ እንደአማራ ሕዝብ በጠላትነት የተፈረጀና ስትራቴጂ ተነድፎ እንዲዳከም  የተሠራበት ሕዝብ የለም ። በአማራ ላይ ሲደርስ የቆየውንና አሁንም የቀጠለውን መከራ የሚዘግብ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃንም ሆነ የሰብአዊ መብት ተንከባካቢ ተቋም አልተገኘም። ሆኖም ባለመደራጀታችን ምክንያት ይህን በሕዝባችን ላይ ሲፈጸም የቆየውን እና አሁን እየተፈጸመ ያለውን የዘር ማጥፋት ጥቃት ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ማስገንዘብ አልቻልንም። ስለዚህ  በአስቸኳይ እንደሕዝብ ተደራጅተንና ሁላችንም የሕዝባችን ዲፕሎማቶች ሆነን ፤ በማያቋርጥ ትግልና ውትወታ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የሕዝባችንን በደል እንዲገነዘብ የማድረጉ ሃላፊነት የኛ ነው ። ነጻነታችንን ማረጋገጥ የምንችለው በራሳችን ትግልና መስዋዕትነት መሆኑ የማያጠራጥር ቢሆንም ፣ የዓለም አቀፍ ማኅበረሰቡን ድጋፍ እስካላገኘን ድረስ ፣ ወይም የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ለአብይ የሚያደርገውን ድጋፍ እንዲገታ እስካላደረግን ድረስ የምንከፍለው መስዋዕትነት ከፍተኛ እንደሚሆን ግልጽ ነው ። ስለሆነም የሕዝባችን ጥያቄ ፍጹም ፍትሐዊ ጥያቄ መሆኑን ፣ የሕዝባችን ትግል ለነጻነት ፣ ለእኩልነትና ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የሚደረግ ትግል መሆኑን  አበክረን ማስገንዘብና የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ከሕዝባችን ጎን እንዲቆም ለማድረግ ያለመታከት መታገል ይኖርብናል።

Comments

Popular posts from this blog

የጋራ ጠላታችንን ልናሸንፈው የምንችለው ብአንድነት ብቻ ነው:: ሻ/ቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ

ከዚህ መከፋፈል ነፃ ሆነን ፊትለፊት  እየወረረ : እየገደለን: ያለውን የጋራ ጠላታችንን ልናሸንፈው የምንችለው ብአንድነት ብቻ ነው:: ሻ/ቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ ሻ/ቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ በምናየው  ታላቅ  የፋኖ ትግል የዲያስፓራ ትልቁ ስራ ገንዘብ መስብስብ ነው:: እሱም እየቀዘቀዘ ሄዷል:: ጦርነቱን ያራዝምነው እኛው ነን:: ይህ ደግሞ ትልቁና ዋናው የጠላት ስትራተጂ ነው:: ጦርነቱን ማራዘምና ከአማራ ምድር እንዳይወጣ በማድረግ: ፋኖን በመከፋፈል አዳክመዋለሁ ! እበትነዋለሁ ! የሚል የአቢይ አህመድ ትልቁ  የወቅቱ ስትራተጂ መሆኑን ተረድተናል::: በዚህም ምክንያት በአጠረ ጊዜ  ሊጠናቀቅ የሚችለውን  ትግል  ዲያስፓራ በምቀኝነት: በቅናት: በሌለ  ስልጣን  ላይ በመፋተግ: በተቀጣሪነት: በጠባብ አስተሳስብ: ትግላችንን ወደኋላ  በመጎተትና  እንዲራዘም ብሎም እንዲዳከም በማድረግ ታሪካዊ ወንጀል እየስራ ነው:: ከዚህ መከፋፈል ነፃ ሆነን ፊትለፊት  እየወረረ : እየገደለን: ያለውን የጋራ ጠላታችንን ልናሸንፈው የምንችለው በአንድነት ብቻ ነው::  አሸናፊነት ትብብርና  የጋራ ስትራተጂ ይጠይቃል:: የተግባር ዲያስፓራ እንሁን:: አማራን እንደ  ህዝብ ኢትዮጵያንም እንደ ሀገር  ለማዳን  ዋናው መሳሪያችን  አንድነት ነው:: በውስጣችን ያለውን ልዩነት በመጠቀም  አገራችንን ለማጥፋት: በአካባቢያችን  ያለውን የሀይል አሰላለፍ ስንመለከት ፍፁም ፍፁም  አደገኛ  መሆኑን እንገነዘባለን:: በዲያስፓራ  መጨቃጨቅና መዘላለፍ  እንደ ባህልና እንደ ትልቅ   የጦርነት ስትራተጂ ተደር...

ዐማራን ወክሎ ከወያኔ ጋር ስለሰላምም ሆነ ስለትጥቅ ትግል አልፎም ስለመንግሥት መሥረታ መነጋገር ፈጽሞ አይቻልም

ዐማራን ወክሎ ከወያኔ ጋር ስለሰላምም ሆነ ስለትጥቅ ትግል አልፎም ስለመንግሥት መሥረታ መነጋገር ፈጽሞ አይቻልም፤ ዐማራ የተጨፈጨፈው በሦስት ዓመት ዕድሜ ውስጥ ብቻ አይደለም። በ17 ዓመት የወያኔ የሽፍተነት ዘመን፣ 27 ዓመት የወያኔ የመንግሥትነት ዘመን ወደኋላ ተጨምሮ ነው። ከውያኔ ጋር ሰላምን ወይም ትጥቅ ትግልን እናደርጋለን የሚሉ ሁሉ ውሾች ናቸው። "ውሻ ወደ ትፋቱ ይመለሳል" በምሣሌ 26፤11 እና 2ኛ ጴጥሮስ2፤22 የተጠቀሰውን መጽሐፋዊ ዘገባ በማንበብ ከውያኔ ጋር የመከሩትን የውሾች ባህሪ ለይቶ መረዳት ነው። ምስሉ ጸሃፊውን አይወክልም 1ኛ. የዐማራን ሕዝብ የመደብ ጠላት አድርጎ ወያኔን በደደቢት የመሠረተውና 17 ዓመት በትጥቅ ትግል 27 ዓመት በመንግሥትነት በደምሩ 44 ዓመት ከሰባት ሚሊዮን በላይ ዐማራን ሕዝብ ያለማቋረጥ ያስጨፈጨፈ፣ ርስቱን የነጠቀ በጀምላ የገደለ ያፈናቀለ፣ የትግራይን ሕዝብ ከኢትዮጵያዊ ቀዳሚ ሕዝብነቱና ማንነቱ ያስከዳ ስብሐት ነጋ ፤   2ኛ. ከዐማራ ሕዝብ ይልቅ የሱዳን ሕዝብ ይሻለናል ብሎ በማይካድራ በጭና ዐማራን በከፍተኛ መራር በሆነ ጭካኔ ያስጨፈጨፈው፣ በመጨረሻ ተረጋግቶ መኖር ሲችል ዕቅድና ዓላማ በሌለው ጦርነት አንድ ሚሊዮን የትግራይ ወጣት ያስጨፈጨፈ፣ የትግራይን ሕዝብም ሆነ የዐማራን ሕዝብ አዘቅት ውስጥ የከተተ ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ፤   3ኛ. የወያኔ ተሿሚ ሆኖ የዐማራን መሬት ፀገዴና ጠገዴ እያለ እየከፋፈለ ለወያኔ ያስረከበ፣ የግጨውን መሬት ለወያኔ በችሮታ ፈርሞ የሰጠ፤ እነ ዶክተር አባቸው ለማስገደል ቅድመ ሁኔታዎችን ከአመቻቸ በኋላ ወደ አሜሪካ ሀገር ሾልኮ ወጥቶ ከተገደሉ በኋላ ተመልሶ ጥቁር ለብሶ የዓዞ እንባ ሲያነባ ሲመጻደቅ የነበረ የሕወሀትም ሆነ የብልጽግና ቀንደኛና ፊ...

በጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)

ሻለቃ ዳዊትን በተለያዩ ምክንያቶችና ወቅቶች እንደ እኔ የተቻቸው ፈልጋችሁ አታገኙም። ያ ወቅት ሌላ ፤ ዛሬ ሌላ፤- ያ ዘመን ከ2010 ዓ.ም በፊት ነው። ሰው የነበረውን መስመር አስተካክሎ ባዲስ አካሄድ ወቅቱ በሚጠይቀው ጎዳና ከተራመደ ሌላ ምን ይፈለጋል? ዛሬ ግን ሻለቃው “ኢምፖስተር” በማለት የሚጠሩት ህቡእና ግልጽ ነብሰገዳይ ቡድን አሰማርቶ ነብስን የሚቀጭና የሚሰውር <<የወያኔ የነገድ አስተዳዳር አስቀጣዩ የኦሮሙማው የጋጠወጥ ማፍያዎች መሪ>> አብይ አሕመድ ከነገሠ ወዲህ ግን “ሻለቃው” አብይ አሕመድን እንቅልፍ ካሳጡት አርበኞች አንዱ ሆነው ብቅ ብለዋል። ያንን በማድረጋቸው “ጥበብ ሳሙኤል” የተባለ የአብይ አሕመድ አለቅላቂና ፀረ አማራና የሕግ ሙያ ትምሕርተ አለበት ተብሎ የሚነገርለት (?) ጋዜጠኛ:- አብይ አሕመድን በመደገፍ በሻለቃው ላይ ያለ ዕረፍት ረዢም ጊዜ ሲዘልፋቸው ያስገረመኝ ያህል፤ ሰሞኑን ደግሞ በሻለቃ ዳዊት ወ/ልደጊዮርጊስ ላይ አዳዲስ ዘላፊዎች ብቅ ብለዋል። “ሻለቃ ሆይ! በትግሉ ውስጥ ዛሬ ይኑሩ አይኑሩ አማራውን ለመታደግ ከፍታዎትን አሳይተዋል ፤የበኩልዎን አድርገዋል ለዚህም <<በአክብሮት ባርኔጣየን አነሳለዎታለሁ፤ አንኳን ደስ አለዎት !!!!>> አርበኛ ብቅ ባለ ቁጥር ሱሪውን የሚጎትቱ ብዙ የፖለቲካ ተውሳኮች አሉ። ሻለቃው በዛው ዕደሜአቸው የሚቻላቸውን በማድረጋቸውና ከፍታቸውን በማሳየታቸው ፤ ይህን በማድረጋቸው ዓይናቸው ከቀላ ውስጥ አንዱ ወደ “ጥንት ትፋቱ” የተመለሰው፤ በቅርቡ ከወያኔም ከኦነጎችም እየተወዳደሰ መተፋፋግ የጀመረው የወያኔው አሽከር “ኤርሚያስ ለገሰ” እና ዶ/ር አምሳሉ የተባለ “ከጎንደሬዎች እጅህን አንሳ” እያለ ሲከራከረኝ የነበረው እስከ ቅርብ ጊዜ ወዲህ የአብይ አሕመድ አወዳሽ የነበ...