Skip to main content

Posts

“በዘላቂ ድል ወደ ብልጽግና” የድኅረ ጦርነት መዛነፎችና እርምቶቹ !“ በሬ ሆይ በሬ ሆይ ሳሩን አየህና፣ ገደሉን ሳታይ እልም ካለው ገደል ወደቅክብን ወይ?” - ሀገራዊ ብሂል ፤ ታህሣሥ 2014 ዓ.ም ፤ ሃዋሳ

“በዘላቂ ድል ወደ ብልጽግና” የድኅረ ጦርነት መዛነፎችና እርምቶቹ በሚል ርእስ የአማራ ብልጽግና ሚስጥራዊ ስብሰባ የሚያሳይ ዶሴ  በጀግኖች የአማራ ልጆች እጅ ስር ወድቋል። ይህንን መረጃ ያካፈልከን ወንድማችን ከልብ እናመሰግናለን። እኛም በቀላሉ መነበብ እንዲችል በዚህ መልኩ አቅርበናል ፤ እባክዎት በጥሞና ያንብቡትና ለወዳጅ ዘመድ ሼር ያድርጉት።  ማዉጫ 1. መግቢያ ........................................................................1 2 ሀገራዊ የድኅረ ጦርነት ፈተናዎችና አቅጣጫዎች..... 3 2.1 የአማራ ክልል ሁኔታ .......................................................3 2.2 የአፋር ክልል ሁኔታ .........................................................5 2.3 የትግራይ ክልል ሁኔታ .....................................................6 2.4 የኦሮሚያ ክልል ሁኔታ .....................................................7 2.5   የአዲስ አበባ ሁኔታ ..........................................................8 2.6 የሶማሌ ክልል ሁኔታ.........................................................9 2.7 የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሁኔታ ..................................9 2.8 የጋምቤላ ክልል ሁኔታ....................................................10 2.9 ሲዳማ ክልል ሁኔታ ...........

ምንም ጫጫታ አያስፈልግም ፤ በዐማራ ላይ እየደረሰ ያለው ባርባራዊ በደል የ70 እና የ80 ዓመት ፕሮጀክት ውጤት ነው። በታደለ ጥበቡ Jan 11, 2022 የተጻፈ

በታደለ ጥበቡ  Jan 11, 2022 የተጻፈ ፤ ምንም ጫጫታ አያስፈልግም፣ ዝም ብለን ለብዙ መቶ ዓመት የሚሻግረንን ሥራ በፀጥታ እንሥራ፣ ዛሬ በዐማራ ላይ እየደረሰ ያለው ባርባራዊ በደል የ70 እና የ80 ዓመት ፕሮጀክት ውጤት ነው። -በጃን ሆይ ዘመን ኢትዮጵያ ውስጥ ይኖር የነበረው  ኦስትሪያዊ ባሮን ሮማን ፕሮቻዝካ (Paron Roman prochazka)  በ1927 ዓ.ም. ቪየና ላይ  "ኢትዮጵያ የባሩድ በርሜል" በሚል ርእስ አውሮፓውያን ኢትዮጵያን እንዴት ሊወሩና ሊይዙ እንደሚባ በሚያትተው መጽሐፉ፣  "ምእራባውያን ወገኖቼ ስሙኝ በምስራቅ አፍሪካ በምትገኘው ኢትዮጵያ ውስጥ አንድ ዐማራ የሚባል ነገድ አለ። ይህ ነገድ እኛ ምእራባውያን በአፍሪካ በምናደርገው የመስፋፋት ፖሊሲ ትልቅ እንቅፋት ነው። ዐማራ ከተደራጀ እንኳን ለአፍሪካ ለእኛም ትልቅ ስጋት ስለሆነ በዚህ ህዝብ ላይ እያንዳንዱ ምእራባዊ ሀገር የሚከተለው ፖሊሲ ከዚህ አንፃር መቃኘት አለበት።” (Abyssenya the powder barrel፣ p. 7) በማለት   ይሄን አስፈሪ ነገድ  ነጮች ተባብረው አስቸኳይ እርምጃ እንዲወስዱበት አሳሰበ። ጣሊያን ይሄን መጽሐፍ እንደ ግባት በመውሰድ በ1928 ዓ.ም. ኢትዮጵያን ስትወር የከፋፍለህ ግዛ (Divided and Rule) ፖሊሲ ተግባራዊ ማድረግ ጀመረች። ትግሬውን በዐማራው ላይ አነሳሳች። ቺኮዝላቫኪያ ተወላጅ የነበሩት አዶልፍ ፓርለሳክ “Habešská Odyssea”በሚለው መጽሐፉ እንደነገረን  ጣልያኖች በትግርኛ ቋንቋ፣ በትግሬ መንደሮች እንዲህ የሚል ወረቀት ይበትኑ ነበር፣ "ለትግራይ ህዝብ! "በሀገራችሁ ሰላም አስፍነን ስልጣኔና ብልጽግናን እንድናሰፍን እግዚአብሔር ልኮናል። ይሁን እንጂ ዐማራ ...

“Fano: A living saviour of the Amhara people And the Ethiopian spirit” – Written by Pro. Girma Berhanu, Sweden.

Pro. Girma Berhanu, Sweden "Fano: A living saviour of the Amhara people And the Ethiopian spirit -  ፋኖን እወዳለሁ፥ ፋኖንስ አልጠላ፣  ተኳሽ እወዳለሁ፥ ተኳሽም አልጠላ፣  Introduction  Fano is a historical term used in Ethiopian struggles against injustice and foreign invaders. It is mainly shown as a youth movement that has played a significant role in preserving the concept of Ethiopian nationhood. As a youth group, it has emerged from within the Amhara ethnic group and has features of reminiscent of classical political, religious, or even social movements that drive youthful frustrations into acts of agitation until they achieve a measure of reform. Traditionally, the Fano struggle had focused on fending off attacks against Ethiopia. In recent years, Fano has become a household name and a crucial movement tasked with saving the very existence of the Amhara population as well as the integrity of Ethiopia. In this, it differs from other similar youth movements in the country, whose aim is t...

"ምኗ ላይ ተቀምጣ በሽንቷ ሰፌድ ትሰፋላች":- አዲሱ የአቢይ ካቢኔ አሰያዬም ፤ በሸንቁጥ አየለ

ችግሩ ያለዉ የጎሳ ፖለቲካ ርዕዮተ ፍልስፍናዉ ላይ ነዉ::ኢትዮጵያዉያንን ሀገር አልባ ያደረገዉን የጎሳ ፖለቲካ ፍልስፍና መሰረት ላይ የቆመ ካቢኔ ምንም አይነት መልካም ግለሰቦችን ሰብስብቦ ቢያቅፍ ከቶም የሀገር መድሃኒት አያመጣም:: ሆኖም የዚህ ስርዓት የጥቅም ተጋሪዎች እና እግር አጣቢዎች ይሄን የጎሳ ፖለቲካ አስተሳሰብ የተለያዬ የማስመሰያ መቀባቢያ በመቀባት ጸረ ሰዉ የሆነዉን የጎሳ ፖለቲካ አስተሳሰብ ለማስቀጠል እና ህዝብን ለማምታታት ብዙ ሲዳክሩ ይሰተዋላል::በአዲሱ የአቢይ ካቢኔ አሰያዬም የተከናወነዉ ድራማም ይሄዉ ነዉ:: እከሌ ከኦህዴድ:እከሌ ከብአዴን:እንትና ከአብን : እንቶኔ ከኢዜማ: እንቶኔ ደግሞ ከትግራይ ብልጽግና ተሾሙ እያሉ ብዙ የጥቅም ተጋሪዎች እና የአገዛዙ ሚዲያ ብዙ ይቀባጥራሉ::በደስታም እንኳን ደስ አለህ ይባባላሉ::ኢትዮጵያዉያን ግን አሁንም ሀገር አልባ ናቸዉ:: የኢትዮጵያ የችግር ምንጭ ሁሉ አንድ ነዉ::ይሄዉም የጎሳ ፖለቲካ ፍልስፍና ነዉ::መለስ ዜናዊ የሀገሪቱን ጥፋት ያመጣዉ የጎሳ ፖለቲካ ፍልስፍና በማራመድ ነበር::መለስ ዜናዊ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሆኖ በስሩ ብዙ በግለሰብ ደረጃ መጥፎ የማይባሉ ሰዎችን በካቢኔዉ ዉስጥ ሰግስጎ ነበር:: ሆኖም የመለስ ዜናዊ ካቢኔ እያንዳንዱ የሚመራበት መርህ በጎሳ ፖለቲካ ፍልስፍና እና ቀመር ስለሆነ የሚሰሩ ስራዎች ሁሉ በዚሁ መርዛማ ህሳቤ ዙሪያ የሚሽከረከሩ ነበሩ:: አሁንም አቢይ የሾማቸዉ ሰዎች መጥፎ ናቸዉ ጥሩ ናቸዉ የሚለዉ አይደለም ጥያቄዉ:: ወይም ደግሞ ሰዎች ከዬትኛዉ ፓርቲ ተመርጠዉ ተሾሙ አይደለም ጥያቄዉ:: አቢይ የሚመራበትም የፖለቲካ ፍልስፍና እንደ መለስ ዜናዊ ሁሉ የጎሳ ፖለቲካ ፍልስፍና ነዉና ያዉ ዉሃ ቢወቅጡት እንቦጭ ነዉ::ስለዚህ የተሿሚዎቹ መልካምነት ወይም የመጡበት የፓርቲ ቁም ነገ...

"ከእኛ ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህ?" በዴቭ ዳዊት

"ከእኛ ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህ?" ይህ ምስል የዴቭ ዳዊት ስራ ነው! June 6, 2020 የተፃፈ ከሰሞኑ የአማራ ህዝብ ትግል ከሁለት አመት በፊት በይፋ ተጠልፎ አማራዊ ብሔርተኝነትን ለማዳከምና ለማጥፋት ሲባል ብአዴናዊ ብሔርተኝነት መፈጠሩን፤ እንዲሁም ብአዴናዊው ብሔርተኝነት መገለጫ ባህርይው ምን እንደሚመስል በዝርዝር ተመልክተን ነበር። ከዚያም ጎን ለጎን በአማራ ህዝብ ትግል ውስጥ በአማራዊ ብሔርተኝነት እና በብአዴናዊ ብሔርተኝነት መካከል ግልፅ መስመር ባለመሰመሩ ምክንያት ከፍተኛ የሆነ የጎራ መደበላለቅ መፈጠሩን፥ይህንንም አጋጣሚ ተጠቅሞ በጎጣዊ ውግንና የገነገነው ብአዴናዊው ብሔርተኝነት፥ አማራዊ ብሔርተኝነቱን ለማደብዘዝና ለማፈን ሰፊ ዕድል እንደተፈጠረለት ተመልክተናል። እነሆ ዛሬ ጊዜ እንደፈቀደ የአማራ ህዝብ ብቸኛ መዳኛ የሆነው ግን በብዙ አቅጣጫ ጦርነት ተከፍቶበት ያለው አማራዊ ብሔርተኝነት ውስጣዊ ጠላቱ ስለሆነው ብአዴናዊ ብሔርተኝነት እንዲሁም ብአዴናዊው ብሔርተኝነት በአማራዊው ብሔርተኝነት ላይ የከፈተበትን የጦርነት ስልትና ይዘት እንፈትሻለን። መልካም ንባብ። የአማራ ሕዝብ የዘመናት ትግል የሆነው አማራዊ ብሔርተኝነት፥ እንደ አማራ አቆጣጠር በ1980ዎቹ መጨረሻ የመጀመሪያው የመጠለፍ አደጋ ሲገጥመው የተፈፀመው ደባ ቢኖር #የመሪ_አታጋይ_ድርጅቱን_ህልውና_ማሳጣት /የመዐሕድን/ ነበር። ሁለተኛው ዙር ህዝባዊ ተጋድሎ እየሰፋና ፍሬ ወደ ማፍራቱ ደረጃ ሲደርስ ደግሞ ትግሉ ገና #ሙሉ_ዕድገቱን_የጨረሰ_መሪ_ድርጅት ከመውለዱ በፊት፥ በህዝባዊ ማዕበሉ ከመበላት ለማምለጥ ሲል ብአዴን የአማራን ትግል ጠለፈው።  አማራዊው ብሔርተኝነት የራሱን ሰንደቅ የሚሸከም/Standard bearer/ መሪ ድርጅት ሳይፈጥር የአማራ ሕዝብ ትግል በብአዴን መጠለፉ...

ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የተጸነሰው ሴራ ይፋ ሆነ ፤ ኢትዮጵያን ከመፈራረስ ለመታደግ በአንድነት መቆም ነው— በዶ/ር አክሎግ ቢራራ

እኔ እስከማውቀው ድረስ፤ የምእራብ አገሮች ለጥቁር አፍሪካ ሕዝቦች ሰላም፤ እርጋታ፤ ክብር፤ ነጻነት፤ ፍትሃዊና ዘላቂ ልማት ቆመው አያውቁም። በተለይ፤ ለመላው የጥቁር ሕዝብ ክብርና ነጻነት ተምሳሌ የሆነችውን የኢትዮጵያን ግዛታዊ አንድነት፤ ሉዐላዊነት፤ የስብጥር ሕዝቧን አብሮነት፤ ሰላም፤ እርጋታ፤ ፍትሃዊ፤ ዘላቂ ብልጽግና ደግፈው አያውቁም። የኢትዮጵያ ጠንካራና አገር ወዳድ መንግሥት ለነሱ ብሄራዊ ጥቅም ስጋት ፈጣሪ ነው። ይኼን ሃቅ በአጼ ኃይለ ሥላሴና በደርግ መንግሥት ወቅትም አይተናል።  ህወሓት/ትህነግ ጆ ባይደን በተመረጡበት ማግስት ክህደት፤ እልቂት ከፈጸመበትና ጦርነት ከጀመረበት አንድ ሳምንት በኋላ ለዚህ አጥፊ፤ ከሃዲና የውጭ ኃይሎች አገልጋይና አሽከር የሆነ ቡድን ግዙፍ ድጋፍ ይሰጡት የነበሩት የምእራብ “ዲሞክራሲ” ነን የሚሉ ባለሥልጥናት ሴራቸውን በምስጢር ቀየሱ።  ኢላማቸው ሁለት አስኳል ጉዳዮች ነበሩ፤ አንድ የጠቅላይ ሚንስትር ዶር ዐብይ አሕመድን መንግሥት መገልበጥና ባለሥልጣናትን ልክ እንደ ሰርቦች ለፍርድ ማቅረብ፤ ሁለት፤ ኢትዮጵያ ልክ እንደ ዩጎስላቭያና እንደ ሶማልያ እንድትበታተን ማድረግ።  እኛ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን በተደጋጋሚ ለምእራብ አገሮች ባለሥልጣናት፤ በተለይ ለአሜሪካ ምክር ቤት አባላት በተደጋጋሚ እባካችሁ ሚዛናዊ አቋም ያዙ፤ በመሬት ላይ ያለውን ሃቅ አንጸባርቁ፤ የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል የትግራይ ሕዝብ ጠላት አይደለም፤ የብሄር ማጥፋት ዘመቻ አያካሂድም፤ የኢትዮጵያ መንግሥት 70 በመቶ የሚሆነውን ሰብአዊ እርዳታ እየሰጠ ነው ወዘተ እያልን ብንጮህም ሰሚ አላገኘነም ነበር። ብዙዎቻችን ግራ ተጋብተን ነበር ለማለት እችላለሁ። ለምን ጀሩቸውን አይከፍቱም፤ አይናቸውን አይገልጡም? እንል ነበር፡ ከጀርባ በረቀቀ ምስ...

JOURNALISM IS NOT CRIME

የአማራ ሚዲያ ማዕከል ጋዜጠኛ  ለድምጽ አልባው ወገናችን ፤ ድምፅ በመሆን የሚታወቀው ጋዜጠኛ አባይ ዘውዱ በነውረኛው የአማራ ብልጽግና ፓርቲ እና በአብይ አህመድ  አፋኝ ቡድኖች አሳፍነው ወዳልታወቀ ቦታ ወስደውታል።  Abay Zewdu, AMC reporter & Journalist Free Abay Zewdu   ድምጽን ለማፈን መሞከር ከቶውንም አይቻልምና ፤ በአስቸኳይ ጋዜጤኛ አባይ ዘውዱን ፍቱት!  Free AMC Journalist