Skip to main content

ምንም ጫጫታ አያስፈልግም ፤ በዐማራ ላይ እየደረሰ ያለው ባርባራዊ በደል የ70 እና የ80 ዓመት ፕሮጀክት ውጤት ነው። በታደለ ጥበቡ Jan 11, 2022 የተጻፈ

በታደለ ጥበቡ  Jan 11, 2022 የተጻፈ ፤ ምንም ጫጫታ አያስፈልግም፣ ዝም ብለን ለብዙ መቶ ዓመት የሚሻግረንን ሥራ በፀጥታ እንሥራ፣ ዛሬ በዐማራ ላይ እየደረሰ ያለው ባርባራዊ በደል የ70 እና የ80 ዓመት ፕሮጀክት ውጤት ነው።

-በጃን ሆይ ዘመን ኢትዮጵያ ውስጥ ይኖር የነበረው  ኦስትሪያዊ ባሮን ሮማን ፕሮቻዝካ (Paron Roman prochazka)  በ1927 ዓ.ም. ቪየና ላይ  "ኢትዮጵያ የባሩድ በርሜል" በሚል ርእስ አውሮፓውያን ኢትዮጵያን እንዴት ሊወሩና ሊይዙ እንደሚባ በሚያትተው መጽሐፉ፣ 

"ምእራባውያን ወገኖቼ ስሙኝ በምስራቅ አፍሪካ በምትገኘው ኢትዮጵያ ውስጥ አንድ ዐማራ የሚባል ነገድ አለ። ይህ ነገድ እኛ ምእራባውያን በአፍሪካ በምናደርገው የመስፋፋት ፖሊሲ ትልቅ እንቅፋት ነው። ዐማራ ከተደራጀ እንኳን ለአፍሪካ ለእኛም ትልቅ ስጋት ስለሆነ በዚህ ህዝብ ላይ እያንዳንዱ ምእራባዊ ሀገር የሚከተለው ፖሊሲ ከዚህ አንፃር መቃኘት አለበት።” (Abyssenya the powder barrel፣ p. 7) በማለት   ይሄን አስፈሪ ነገድ  ነጮች ተባብረው አስቸኳይ እርምጃ እንዲወስዱበት አሳሰበ።

ጣሊያን ይሄን መጽሐፍ እንደ ግባት በመውሰድ በ1928 ዓ.ም. ኢትዮጵያን ስትወር የከፋፍለህ ግዛ (Divided and Rule) ፖሊሲ ተግባራዊ ማድረግ ጀመረች። ትግሬውን በዐማራው ላይ አነሳሳች። ቺኮዝላቫኪያ ተወላጅ የነበሩት አዶልፍ ፓርለሳክ “Habešská Odyssea”በሚለው መጽሐፉ እንደነገረን  ጣልያኖች በትግርኛ ቋንቋ፣ በትግሬ መንደሮች እንዲህ የሚል ወረቀት ይበትኑ ነበር፣

"ለትግራይ ህዝብ!

"በሀገራችሁ ሰላም አስፍነን ስልጣኔና ብልጽግናን እንድናሰፍን እግዚአብሔር ልኮናል። ይሁን እንጂ ዐማራ ሰው በላ ወታደሮቻቸውን አሰልፈውብን ይኼንን የተቀደሰና ከእግዚአብሔር የተሰጠንን ተልዕኮ እንዳንፈጽም እያወኩን ነው። የተከበርክ የትግራይ ህዝብ ሆይ፣ እነዚህን የዐማራ ቀማኛ ሽፍቶች በመንደርህ ሲዘዋወሩ ብታገኝ እህል ውሃ ሳታቀምስ፣ ጥይትህን እየተኮስክ እንደውሻ ከመንደርህ እንድታባርራቸው እናሳስብሀለን።

እነዚህ የዐማራ ሽፍቶች ወደ መንደራችሁ ተጠግተው የሚበላም ሆነ የሚጠጣ ነገር ሊገዙ ቢቀርቡ አብርሯቸው። አዝናችሁም ምንም ነገር፣ ምንም አይነት ርዳታ እንዳታደርጉላቸው አጥብቀን እናሳስባለን። ከማሃላችሁ ይኼን ትዕዛዛችንን ተላልፎ አንድ ሰው እንኳ ለዐማራ የሽፍታ ወታደር አንዲት አንበሻ ሲልግስ ወይም ሲሸጥ ቢገኝ፣ ምህረት የሌለው ቅጣታችን በሁላችሁም ላይ ላይ ይደርሳል።" (የሃበሻ ጀብዱ፣ 214)

በእንዲህ ያለ የፕሮፓጋንዳ ወረቀት የትግራይ ሰዎች ጣሊያንን ለመፋለም ከጎጃም፣ ከጎንደር፣ ከቤተ አምሐራና ከሸዋ የተንቀሳቀሰውን ኢትዮጵያዊ የዐማራ ጦር ሠራዊት በመንደሮቻቸው አካባቢ ሲደርስ ተኩስ ከፍተውበታል፤ ዘርፈውታል፤ ገድለውታል። 

እንደገና ኦሮሞውን በዐማራው ላይ አነሳሳች።

አልቤርቶ ሰባኪ እንደነገረን የጥላቻው ጠቀሜታ ስለታወቀ ኦሮሞዎችን በዐማራዎች ላይ ማነሳሳት አንዱ  የጣሊያን ፕሮፓጋንዳ ማዕከላዊ ነጥብ ነበር። ኦሮሞዎች በጣሊያን እውነተኛ የረጅም ጊዜ ዕቅድ ላይ ጥርጣሬ ስለነበራቸው ጣሊያኖች የኦሮሞዎችን አመኔታ ለማግኘት ዐማሮችን በኦሮሞዎች ፊት ያሰቃይዋቸው ነበረ። ምንም ዓይነት የመቻቻል ምልክት ወይም ለዐማሮች ወገናዊነት ከኦሮሞዎች እንዳያገኙ ይሰሩ ነበረ። (አልቤርቶ ሰባኪ፣ 178)

ጣሊያን ዐማራን በማስጠላት ኢትዮጵያን ለቅኝ ግዛት ለማመቻቸት ያደረገችው ጥረት በአክራሪ ብሔርተኞች ቅቡል ሆነ። የጣሊያንን ፀረ-ዐማራ ፖሊስ ተጋሪ የሆኑ የሀገር ውስጥ በጥላቻ የሰከሩ ብሔርተኞች በዐማራ ጥላቻ ሕግ እና ተቋም ፈጠሩ።

ጣሊያን አገሩን ወርራ እንደያዘችው፣ ሥራዬ ብላ የለፋችው፣ ኢትዮጵያ የሚል ስም ካለም ካርታ ተፍቆ፣ በካርታ ላይ የነበረው ስም የጣሊያን ምሥራቅ አፍሪቃ “Africa Orientale Italiana" እንዲባል ነበር። ትህነግና ኦነግ ደግሞ "ኢትዮጵያዊነትን ዐማራው የጫነብን ዕዳ ነው" በማለት የኢትዮጵያዊነት አስኳል ከውስጣቸው አውጥተው ጣሉት። እንጀራ የዐማራ ስለሆነ አንበላም አሉ። ሸማ ልብስ ያለበሰን ዐማራ ነው በማለት የለበሱትን ሸማ ለማውለቅ ሞከሩ። ሃይማኖት የዐማራ ነው  በማለት በአጉል ማርክሳዊ-ሌኒናዊነት እግዚአብሔር-አልባ ሆኑ። ትዕቢት ወደ ይሉኝታ-ቢስነት ለወጣቸው። የመንፈስ ኃይላቸው ደቀቀ። ወደ ጭራቅነት ተቀየሩ። 

እነዚህ ጭራቆች የነጻነት ግምባር ንቅናቄ አቋቋሙ። ግን ማን ነው ነጻ የሚወጣው? ከማንስ ነው ነጻ የሚወጣው? ብሎ የሚጠይቅ ሰው አይጠፋም። ዶናልድ ሌቪን ለዚህ ጥያቄ መልስ አለው፤ "የማርክሲዝም የእስታሊንን ርዕዮ ዓለም ለማስፋፋት በነጻነት ግንባር ንቅናቄ የተደራጁ ቡድኖች ወክለነዋል የሚሉትን ጎሣቸውን ከማን ነጻ እንደሚያወጡት አንድ ማመካኛ ጨቋኝ መፍጠር ነበረባቸውና እርሱንም ክፉ ብለው በአእምሯቸው በቀረጹት ዐማራ ላይ አገኙት። (ትልቋ ኢትዮጵያ፣ ገጽ -×)

ነገድና ጎሣቸውን ከዐማራ ጨቋኝነት ነፃ እናወጣዋለን ብለው በነፃ አውጭነት ስም የተቧደኑት የመጨረሻ ግባቸው ኢትዮጵያን ዐማራ አድርጎ ሌላው ሁሉ እንደ ኤርትራ  ከ"ዐማራ" ነጻ እንዲወጣ፤ እንዲገነጠል፣ በየአካባቢው ሪፐብሊክ መንግሥት እንዲመሠረት ነው። የኢትዮጵያ ግንባታና ታሪክ ከዐማራ በተወጣጡ ሰዎች ብቻ የተካሄደ ይመስል የኢትዮጵያን ታሪክ ሁሉ ዐማራ ለሚሉት አስረክበው ባዶ እጃቸውን ነጻ ሊወጡ ነው። እናም  ሁሉም ዐማራውን ከሰሱ፣ ዐማራውን የጋራ ጠላት አድርገው ተነሱ፣  ወደ ዐማራው ተኮሱ፣ ዐማራውን አሳደዱ፣ ዐማራውን ገደሉ፣  በአብዮት ስም፣ በተራማጅነት ስም በዐማራ ህዝብ ላይ ሸፈቱ። 

ዛሬም ኦነግና ሕወሓት  በዐማራ ህዝብ ላይ እንደሸፈቱ ናቸው። ኦነግ በኦሮሚያ ዐማራውን ይገድላል፣ ያርዳል፣ ያፈናቅላል፣ የነፍስ አባቱ ሕወሓት ደግሞ ዐማራውን በጅምላ ይጨፈጭፋል፣ አዛውንቶችን ይደፍራል፣ ያፈናቅላል፣ ንብረት ያወድማል።

ለዚህም ነው በዐማራ ላይ የተሰራውን  የ70 እና የ80 ዓመት ፀረ-ዐማራ ፕሮጀክት በሚገባ ተረድተን የመቶ እና የሁለት መቶ ዓመት አሻጋሪ የሆነ  ሰርዶ የነካ ሥራ እንስራ የምንለው። ከማንም ጋር አፍ ተካፍተን፣ ተሰዳድበን አንችለውም። ሥራችን ብቻ በተግባር ይገለጥ። 


ለሀሳብ ለአስተያየትና ጥያቄ ቀጥሎ ያለውን  ሊንክ ይጠቀሙ @Tadeletibebut

Comments

Popular posts from this blog

"ከአሁን በሆላ ፋኖ ወደ አንድነት መምጣት አለባቸው የሚባለው አካሄድ አይሰራም" :: በወዳጄ/ቤተ አማራ ወሎ

ከአሁን  በሆላ  ፋኖ  ወደ  አንድነት    መምጣት  አለባቸው  የሚባለው  አካሄድ  አይሰራም::  ክህደት   ከተፈፀመ  በሆላ  አንዱ  ቡድን  ከሌላው  ስር  ሆኖ  ይቀጥላል  ማለት  የማይቻል   ነው::  ምክኒያቱም 1ኛ:- 27  ቀን  ቁጪ  ብለው   መክረዋል :: እያንዳንዱ  አደረጃጄት  ሰነድ  ፅፈው  አቅርበዋል::  በቀረበው  ሰነድ  ላይ  ከፍተኛ  ውይይት  ተደርጎበት  የሚወድቀው  ወድቆ  የሚፈለገው  ፀድቋል::ቃለ  መሀላ  ፈፅመው   ወደ  ምርጫ   ለመግባት  ተስማምተዋል:: እጃቸውን  አውጥተው   ከመረጡ  በሆላ    ግን    "ጨዋታ  ፈረሰ  ዳቦ  ተቆረሰ"   የሚል  የህፃን  ልጂ  ጨዋታ  ውስጥ  መግባት   የአማራን  ህዝብም  ሆነ  የፋኖን  ትግል  መናቅ  ነው:: ይህ  አልበቃ  ብሎ   "ምርጫው  ከኛ  እውቅና  ውጪ  ነው  እኛ  አናውቀውም"  የሚል   የውሸት    የህፃን  ልጂ  ፕሮፓጋንዳ...

ስርነቀል ለውጥ ማምጣት የአማራ ብሄርተኝነት የህልውና ትግል ብቸኛ ግብ ነው። በ Alen Kassahun

ምስሉ ጸሃፊውን አይወክልም፡፤ ከ50 አመታት በላይ የተተከለውንና በተግባር እየተፈፀመ ያለውን አማራን ማጥፋትና ኢትዮጵያን ማፍረስ ከስሩ በመንቀል #4ኪሎን ተቆጣጥሮ ስርነቀል ለውጥ ማምጣት የአማራ ብሄርተኝነት የህልውና ትግል ብቸኛ ግብ ነው። ፋኖ በሚያደርገው የህልውና ትግል አማራ ጠልነት የወለደውን የአማራን ዘር ማጥፋት፤ ማፅዳት፤ የሰባዊ መብት ጥሰትና አገር ማፍረስ አለምአቀፍ ወንጀል ከስሩ ነቅሎ ሊቀብረው #በዋዜማው ላይ እንገኛለን። ስለሆነም ፋኖ እያደረገ ያለውን የህልውና ትግል #በድል እንዳይቋጭ  በድርድር፣ በእርቅና በምክክር ሰበብ የፋኖን ድል ለመቀልበስና ለመንጠቅ ከአሜሪካ እስከ አዲስ አበባና መቀሌ ድረስ በሚሸረብ ሴራ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ፤ በስልታዊ አማራነትም ሆነ በአማራ ጠልነት የተሰለፉ ቅጥረኞች ደፋ ቀና እያሉ እንደሚገኙ ግልፅ ነው። ፋኖ #አራት ኪሎን በመቆጣጠር ስርነቀል ለውጥ ለማወጅ በድል ዋዜማ ላይ ሆኖ እያደረገ ያለውን የመጨረሻውን ትንቅንቅ ለማሰናከልና ድሉን ለመሸጥ ተቀጥራችሁ ስለ ድርድር፣ ሽግግር፣ እርቅ፣ ውይይትና በመሳሰሉ አጀንዳዎች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ እየሰሩ የሚገኙ ቅጥረኞችን ከቀጣሪዎች እኩል ማሸነፍና ማስወገድ የህልውና ትግላችን ብቻኛ አማራጭ መሆኑ ለማንም ግልፅ ሊሆን ይገባል። ስለሆነም የዜግነት ፓለቲካ አቀንቃኝ የ3ኛ ወገን ቅጥረኞችን ከጀርባው አሰልፎ የአማራን ብሄርተኝነት የማድፈቅ አጀንዳቸውን አዝሎ ከአማራ ህልውና ትግል መሀል የተገኘው #እስክንድር ነጋ ከአማራ ህልውና ትግል ጓዙን ጠቅልሎ እንዲወጣ ማድረግ ለነገ የሚባል አይደለም። የእስክንድር ነጋ #የእየሱስ ክርስቶስነት ገፀ ባህሪ በሂደት እየተገፈፈ መምጣት አማራ ጠል ሀይሎችን ወደ እቅድ ሁለት ሴራ እንዲገቡ እያስገደደ በመሆኑ የአማራ ብሄርተኛ #እስክንድ...

አለም አቀፍ የፋኖ ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ነኝ የሚለው ቡድን ዓላማ ምንድነው ? በወንድወሰን ተክሉ

ይህ ምስል ጸሃፊውን አይወክልም! «...አማራ ለ450 ዓመታ መንፈሱ የተሰበረ ገበሮ ሕዝብ ነው..» ሀብታሙ ተገኝ (ፕ/ር) « እኔ እስክንድር  የአማራ ሕዝብ ከደረሰበት የህልውና አደጋ እኩል የሚሆን ዓላማ አለው ብዬ አላምንም» አቻምየለህ ታምሩ፤ አለም አቀፍ የፋኖ ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ነኝ የሚለው ቡድን ዓላማ ምንድነው ? በወንድወሰን ተክሉ እራሱን አለም አቀፍ የፋኖ ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ነኝ የሚለው ቡድን የዙም ውይይት ፕሮግራም ክፍል ሁለትን የተመለከተ ምልክታ:- ባለፈው  ወር ብቻ ሳይሆን ባለፈው ዓመት ዴሴምበር 2023 ( ዛሬ ጃንዋሪ 1 ቀን 2024 ነን)  እራሱን አለም አቀፍ የፋኖ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ብሎ የሚጠራው ቡድን «ጸረ አማራ ኢትዮጲያዊነት» በሚል አርእስት ስር ሀብታሙ ተገኝ (ፕ/ር) ዋና ተናጋሪ ተጋባዥ የሆነበትን  የዙም ውይይት አካሂዶ የነበረ ሲሆን የዚህ ውይይት ክፍል ሁለት  ባሳለፍነው ወር ዴሴምበር 23ቀን በማዘጋጀት አቻምየለህ ታምሩና ሀብታሙ ተገኝ (ፕ/ር) ተናጋሪ እንግዳ በማድረግ አካሂዷል። በእርግጥ  ከዚህ ከሁለተኛው የውይይት ፕሮግራም በፊት በተክሌ ይሻው በኩል የዙም ሊንክ ተልክሎኝ በሰዓት ጥበት ምክንያት መገኘት ባልችልም ዛሬ ግን በቻናላቸው ላይ የጫኑትን ይህን ክፍል ሁለት ውይይት ከተመለከትኩ በኋላ ይህን ምልክታዬን  አንባቢው ሊረዳ በሚያስችል መልኩ አንድ ሰዓት ከሰላሳ ደቂቃ የፈጀን ውይይት ይዘት በመጭመቅ እንደሚከተለው አቅርቤያለሁ። ይህ ምስል ጸሃፊውን አይወክልም! 1ኛ - ውይይቱን አዘጋጅን ማንነት በተመለከተ፦  አለም አቀፍ የፋኖ ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ባለፈው መስከረም ወር ላይ  በጌታቸው በየነ ሰብሳቢነት ተመሰረትኩ ብሎ እራሱን ያስተዋወቀ ሲ...