Skip to main content

Posts

ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የተጸነሰው ሴራ ይፋ ሆነ ፤ ኢትዮጵያን ከመፈራረስ ለመታደግ በአንድነት መቆም ነው— በዶ/ር አክሎግ ቢራራ

እኔ እስከማውቀው ድረስ፤ የምእራብ አገሮች ለጥቁር አፍሪካ ሕዝቦች ሰላም፤ እርጋታ፤ ክብር፤ ነጻነት፤ ፍትሃዊና ዘላቂ ልማት ቆመው አያውቁም። በተለይ፤ ለመላው የጥቁር ሕዝብ ክብርና ነጻነት ተምሳሌ የሆነችውን የኢትዮጵያን ግዛታዊ አንድነት፤ ሉዐላዊነት፤ የስብጥር ሕዝቧን አብሮነት፤ ሰላም፤ እርጋታ፤ ፍትሃዊ፤ ዘላቂ ብልጽግና ደግፈው አያውቁም። የኢትዮጵያ ጠንካራና አገር ወዳድ መንግሥት ለነሱ ብሄራዊ ጥቅም ስጋት ፈጣሪ ነው። ይኼን ሃቅ በአጼ ኃይለ ሥላሴና በደርግ መንግሥት ወቅትም አይተናል።  ህወሓት/ትህነግ ጆ ባይደን በተመረጡበት ማግስት ክህደት፤ እልቂት ከፈጸመበትና ጦርነት ከጀመረበት አንድ ሳምንት በኋላ ለዚህ አጥፊ፤ ከሃዲና የውጭ ኃይሎች አገልጋይና አሽከር የሆነ ቡድን ግዙፍ ድጋፍ ይሰጡት የነበሩት የምእራብ “ዲሞክራሲ” ነን የሚሉ ባለሥልጥናት ሴራቸውን በምስጢር ቀየሱ።  ኢላማቸው ሁለት አስኳል ጉዳዮች ነበሩ፤ አንድ የጠቅላይ ሚንስትር ዶር ዐብይ አሕመድን መንግሥት መገልበጥና ባለሥልጣናትን ልክ እንደ ሰርቦች ለፍርድ ማቅረብ፤ ሁለት፤ ኢትዮጵያ ልክ እንደ ዩጎስላቭያና እንደ ሶማልያ እንድትበታተን ማድረግ።  እኛ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን በተደጋጋሚ ለምእራብ አገሮች ባለሥልጣናት፤ በተለይ ለአሜሪካ ምክር ቤት አባላት በተደጋጋሚ እባካችሁ ሚዛናዊ አቋም ያዙ፤ በመሬት ላይ ያለውን ሃቅ አንጸባርቁ፤ የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል የትግራይ ሕዝብ ጠላት አይደለም፤ የብሄር ማጥፋት ዘመቻ አያካሂድም፤ የኢትዮጵያ መንግሥት 70 በመቶ የሚሆነውን ሰብአዊ እርዳታ እየሰጠ ነው ወዘተ እያልን ብንጮህም ሰሚ አላገኘነም ነበር። ብዙዎቻችን ግራ ተጋብተን ነበር ለማለት እችላለሁ። ለምን ጀሩቸውን አይከፍቱም፤ አይናቸውን አይገልጡም? እንል ነበር፡ ከጀርባ በረቀቀ ምስ...

JOURNALISM IS NOT CRIME

የአማራ ሚዲያ ማዕከል ጋዜጠኛ  ለድምጽ አልባው ወገናችን ፤ ድምፅ በመሆን የሚታወቀው ጋዜጠኛ አባይ ዘውዱ በነውረኛው የአማራ ብልጽግና ፓርቲ እና በአብይ አህመድ  አፋኝ ቡድኖች አሳፍነው ወዳልታወቀ ቦታ ወስደውታል።  Abay Zewdu, AMC reporter & Journalist Free Abay Zewdu   ድምጽን ለማፈን መሞከር ከቶውንም አይቻልምና ፤ በአስቸኳይ ጋዜጤኛ አባይ ዘውዱን ፍቱት!  Free AMC Journalist

“እውነትን በማፈን ፍትሃዊ መምሰል አችይልም- ፍትሃዊ አሰራርን በመከተልና በመፈፀም እንጂ”! በወንድወሰን ተክሉ

የአቢይ  መንግስት ፀረ አማራዊ ጋዜጠኞች አክትቪስቶችና ተሟጎቾች ዘመቻ! የአቢይ መራሹ  የብልፅግና  መንግስት  የመከላከያ  ሰራዊቱን  ቅሌታዊ  ሽንፈትን  ተከትሎ  በአስር ሺህ  የሚቆጠሩ  የመከላከያ  አባላትንና  ብሎም ሲቪል  ባለሙያዎችንና የዩንቨርስቲ  ተማሪዎችን  አዘርክርኮ  ከትግራይ  በፈረጠጠ  ማግስት በአማራ  አክትቪስት ጋዜጠኞችና የሰብአዊ  መብት  ተሟጋቾች  ላይ  በመዝመት  ጋሽ ታዲዮስ  ታንቱን  ጨምሮ  ከአስር  በላይ ጋዜጠኞችን  በኢትዮጲያ  አፍሶ  ያሰረ  ሲሆን በተመሳሳይ  ቁጥር  የሚሆኑ  የማህበራዊ ሚዲያ  አንቂዎችን አካውንትን በዘመቻ  መልክ ለማስዘጋት  መቻሉን ማወቅ  ተችሏል:: ይህ የግራፊክ ምስል ጸሃፊውን አይመለከትም ከጋዜጠኛ  Getachew Shiferaw ሺፈራው  ጀምሮ ጋዜጠኛና አክትቪስት Wondwossen Teklu Wondelove የሰብአዊ መብት ተሟጋች  ቤተልሄም ዳኛቸው Yodith Gideon Dave Dawit Asaminew Tsige Follower  Melkamu Shumye Loul Mekonnen Bahailu_Tessema  Tina Belay bahailu_tessema Kidist_Garumha እና የመሳሰሉትን  በርካታ አማራዊ አካውንቶች በአጭር  ተመሳስይ  ቀናት  ውስጥ  ማዘጋት  የመቻሉ ጉዳይ  የአቢይ  መራሹን...

ፋሺስቱ ኦህዴዳዊው ስርአት

አሜሪካ - የፋሺስቱ ኦህዴዳዊው አፓርታይዳዊው ስርአት - የከረፋ ወንጀሉን መደበቂያና የህዝብን ድጋፍ መዝረፊያ ፈፅሞ አትሆንም! በወንድወሰን ተክሉ አሜሪካንን ፀረ ኢትዮጲያ የሚያደርግ ክስተትም ሆነ ፀረ አሜሪካዊ ኃይል በዛሬይቱ ኢትዮጲያ አለ? በኢትዮጲያነት ስሜት የተሰራው የእስከዛሬው ወንጀል ስቃይና መከራ ከእንግዲህ ላይቀጥል መበጣጠስ ያለበት አሁን ዛሬ ነው:: ፋሺስቱ የአቢይ መራሹ አፓርታይዳዊ ስርአት ከጀሌዎቹ ኢዜማ ጋር በመሆን አሜሪካ ኢትዮጲያን እንደሊቢያ ልታደርግ የተነሳች ቀንደኛ ጭራቅ ናት በማለት የህዝብን attention እና ድጋፍ mobilize ለማድረግ ሲንቀሳቀሱ ታይቷል:: መንጋውም - በተለይ በተለይ ምንም መማር ያልቻለው በስሜት ጋላቢ መንጋ ይህንን መንግስት መር ፕሮፖጋንዳን በማስተጋባት ፈጥኖ ሲሰለፍ ታይቷል:: የግራፊክ ምስሉ ጸሃፊውን አይወክልም! በእርግጥ አሜሪካ ኢትዮጲያን የመበትን አላማ እቅድና ፍላጎት አላትን ? ካላትስ ለምን እና እንዴት  ብሎ ከመጠየቅ የተወረወረለትን አጥንት ለቀም አድርጎ እንደሚሮጥ ውሻ እነዚህ መሰሪዎች የወረወሩለትን የሴራና የፈጠራ ወሬን ብድግ አድርገው ሲያራግቡ ይታያል:: ተመልከቱ ይህ ለብልፅግና መንግስት እነ XYZ የፖለቲካ ኃይሎች ይመቱ በሽብርተኝነት ይፈረጁ ሚዲያዎች ይዘጉ እያለ ጥናት በማቅረብ የኢትዮጲያን ሀገረ ዴሞክራሲን ግንባታን በማደናቀፍ ቀንደኛ ጨፍጫፊ ፋሺስት ስርአትን እየፈጠረ ያለው የኢዜማው ስብስብ ሀገር ወዳድ መስሎ እና እራሱን ለሀገር ተቆርቋሪ አድርጎ አሜሪካንን እየጠራ ሲፎክር አይታችሁ እንኳን መረዳት አትችሉምን? የኢትዮጲያን ህልውና አደጋ ላይ የጣለው የአሜሪካ ተፅእኖ ሳይሆን የአቢይና ኢዜማ ፋሺስታዊ አምባገነንነት ሆኖ ሳለ ዛሬ እነዚሁ ስብስቦች ሀገር በአሜሪካ ጣልቃ ገብነት ልትፈር...

“አዲሱ የትግራይ ትውልድ የትህነግን ትርክት ሳያራግፍ ከአማራ ጋር ሰላማዊ የጉርብትና አኗኗር መፍጠር አይቻልም”

ለርእዮቱ ጋዜጠኛ ቴውድሮስ ጸጋዬ የተሰጠ መልስ: - በወንድወሰን ተክሉ  👉ወልቃይት ጠገዴ ሁመራ ዳንሻና ራያን ከአማራ አስተዳደር ስር አይደለም የተደመሰሰችው ትህነግም ሆነች TDF ይቅርና ተስፋ ያደረጋችኋት አሜሪካም አታስመልስላችሁም-ለሰላማዊ ጉርብትናችን መጀመሪያ የትህነግን ትርክትን መቅበርና ወረራዋን ማውገዝ የአማራ ልዩ ኃይል ሚሊሺያና ፋኖ በምእራባዊው የትግራይ ግዛት (ወልቃይት ጠገዴ ሁመራ ዳንሻ ) በዘረፋ ላይ ተሰማርተዋል የሚለው የቴድርስ ጸጋዬ የእለተ ቅዳሜ ውንጀላ ለዚህ የአጸፋ ምላሽ ጽሁፌ መሰረት እንደሆነኝ በቅድሚያ መግለጹ ተገቢ ይመስልኛል፡፡ ፎቶውና ሎጎው ጸሃፊውን አይወክልም! በብርቱ ተሟጋችነቱ በኢትዮጲያ አንድነት አቀንቃኝነቱ እማደንቀውና እማከብረው የርእዮቱ ሚዲያ አዘጋጅ ጋዜጠኛ ቴድሮስ ጸጋዬ በቅዳሜ እለት ፕሮግራሙ ከጋበዘው ክፍሉ ሁሴን ጋር በመሆን መጀመሪያ በአማራ ልዩ ኃይል ሚሊሻና ፋኖ ላይ ቀስና ለስለስ አድርጎ የጀመረውን የነቀፋና ውንጀላን በማጠናከርና ብሎም በማክረር አጠቃላይ ዘለፋዎቹንና ውንጀላዎቹን በአማራ ህዝብ ላይ በማድረግ ከክፍሉ ሁሴን ጋር እየተቀባበሉ አማራንና የአማራ ብሄርተኝነትን ጥንብ እርኩሱን እያወጡ ሲያወግዙ እጅግ እየገረመኝና እየደነቀኝ አደመጥኩ፡፡ የአድናቆቴና አግራሞቴም መፍለቂያ መንስኤም ይህ አንድን ህዝብ በጅምላ ብድግ አድርጎ የመዝለፍ የመወንጀልና ብሎም የመንቀፉ ሁኔታን በተለይ በተለይ ከቴድሮስ ጸጋዬ አንደበት እየተደመጠ ያለ የመሆኑ ጉዳይ ሲሆን ጋዜጠኛ ቴድሮስ ጸጋዬ በኢትዮጲያ ሀገራዊ አንድነትና ህልውና ፣ በአዲስ አበባ የህልውና ትግል፣በአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ላይና ብሎም በኦህዴድ መራሹ የብልጽግና መንግስት ላይ ያለውን የማይናወጥ ጽኑ አቋማዊ መረዳት ይህንን የእለተ ቅዳሜውን ውግዘተ -አማራን...

በመንግስት የተደገፈ ሽብርተኝነት

 ኦነግ (OLF) የተባለው ነፍሰ ገዳይ ቡድን ፤ በአብይ አህመድ የስውር መዋቅር ውስጥ ፤ በዘመናዊ መሳሪያ ተደራጅተውና ተጠናክረው ያሉ  የኦሮሙማ ተስፋፊ አሸባሪ ቡድን ናቸው። በመንግስት መኪና ተጭነው ፤ ሙሉ የውታደራዊ ሎጀስቲክ ቀርቦላቸው ፤ በነጻነት በሃገሪቱ ክፍል እየተዘዋወሩ  የንፁሀን አማራ ደም የሚያፈሱ ፤ የተረኛው የአብይ አህመድ ነፍሰ ገዳይ ውታደሮች ናቸው።  በአማራ ህዝብ ላይ የሚያደርሰውን ዘግኛኝ ጭፍጨፋና የዘር ማጥፋት ወንጀል ለአለም ህዝብ ለማሳወቅ ሁላችንም በምንችለው መንገድ መስራት ይኖርብናል ። ከዚህ በላይ የሚታየው ቪዲዬ በአማራ ህዝብ ላይ የተፈጸመውን የጅምላ ግድያና የንብረት ውድመት የሚያሳይ ነው ። የቪዲዬ ማጫወቻ ምልክት ይጫኑትና  ይመልከቱት ፤ ከዚያም ለወዳጅ ዘመድ ሼር ያድርጉት ፤ እናመሰግናለን! 

Untold Massacres Against Ethnic Amharas

ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ እጅግ በጣም ግልጽ የሆነው የጂኦንሳይድ ምሳሌ ፤ የዓለም ህዝብ እያየውና እየሰማው በአማራ ህዝብ ላይ  ተፈጽሟል ፡፡ በአብይ አህመድ ፤ በስውር የሚመራው የኦነግ ሸኔ በመባል የሚታወቀው ጨካኝ አሸባሪ ቡድን ፤ የአማራን ከጎረቤቶቻቸው በመለየት ፣ ለብዙ ዓመታት አብረው ከኖሩባቸው ሰዎች ፣ ባህል ፣ ቋንቋ እና ፣ ሀይማኖትን ከሚጋሩዋቸው ሰዎች በገጀራ ታርደዋቸዋል ፤ ከነህይወታቸው በአሰቃቂ ሁኔት በእሳት አቃጥለዋቸዋል ፡፡ ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል ፣ እና ለምን? Read full report from the "Untold Massacres Against Ethnic Amharas In Ethiopia; Quarterly Report on the Human Right Violations Against the Amhara People of Ethiopia.”: January – March 2021, Amhara Association of America.