Skip to main content

“አዲሱ የትግራይ ትውልድ የትህነግን ትርክት ሳያራግፍ ከአማራ ጋር ሰላማዊ የጉርብትና አኗኗር መፍጠር አይቻልም”

ለርእዮቱ ጋዜጠኛ ቴውድሮስ ጸጋዬ የተሰጠ መልስ: -

በወንድወሰን ተክሉ 

👉ወልቃይት ጠገዴ ሁመራ ዳንሻና ራያን ከአማራ አስተዳደር ስር አይደለም የተደመሰሰችው ትህነግም ሆነች TDF ይቅርና ተስፋ ያደረጋችኋት አሜሪካም አታስመልስላችሁም-ለሰላማዊ ጉርብትናችን መጀመሪያ የትህነግን ትርክትን መቅበርና ወረራዋን ማውገዝ

የአማራ ልዩ ኃይል ሚሊሺያና ፋኖ በምእራባዊው የትግራይ ግዛት (ወልቃይት ጠገዴ ሁመራ ዳንሻ ) በዘረፋ ላይ ተሰማርተዋል የሚለው የቴድርስ ጸጋዬ የእለተ ቅዳሜ ውንጀላ ለዚህ የአጸፋ ምላሽ ጽሁፌ መሰረት እንደሆነኝ በቅድሚያ መግለጹ ተገቢ ይመስልኛል፡፡

ፎቶውና ሎጎው ጸሃፊውን አይወክልም!

በብርቱ ተሟጋችነቱ በኢትዮጲያ አንድነት አቀንቃኝነቱ እማደንቀውና እማከብረው የርእዮቱ ሚዲያ አዘጋጅ ጋዜጠኛ ቴድሮስ ጸጋዬ በቅዳሜ እለት ፕሮግራሙ ከጋበዘው ክፍሉ ሁሴን ጋር በመሆን መጀመሪያ በአማራ ልዩ ኃይል ሚሊሻና ፋኖ ላይ ቀስና ለስለስ አድርጎ የጀመረውን የነቀፋና ውንጀላን በማጠናከርና ብሎም በማክረር አጠቃላይ ዘለፋዎቹንና ውንጀላዎቹን በአማራ ህዝብ ላይ በማድረግ ከክፍሉ ሁሴን ጋር እየተቀባበሉ አማራንና የአማራ ብሄርተኝነትን ጥንብ እርኩሱን እያወጡ ሲያወግዙ እጅግ እየገረመኝና እየደነቀኝ አደመጥኩ፡፡

የአድናቆቴና አግራሞቴም መፍለቂያ መንስኤም ይህ አንድን ህዝብ በጅምላ ብድግ አድርጎ የመዝለፍ የመወንጀልና ብሎም የመንቀፉ ሁኔታን በተለይ በተለይ ከቴድሮስ ጸጋዬ አንደበት እየተደመጠ ያለ የመሆኑ ጉዳይ ሲሆን ጋዜጠኛ ቴድሮስ ጸጋዬ በኢትዮጲያ ሀገራዊ አንድነትና ህልውና ፣ በአዲስ አበባ የህልውና ትግል፣በአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ላይና ብሎም በኦህዴድ መራሹ የብልጽግና መንግስት ላይ ያለውን የማይናወጥ ጽኑ አቋማዊ መረዳት ይህንን የእለተ ቅዳሜውን ውግዘተ -አማራን በእኔ አላምንም አግራሞት እንዳደመጠው ያደረገኝ ነው፡፡

በእርግጥ ሁላችንም ሁልግዜ በተመሳሳይ አቋማዊ የውሃ ልክ ላይ ተቀምጠን እንዳንገኝ የሚያስገድዱን ከእኛ አቅምና ቁጥጥር ውጪ ያሉ ክስተቶች ሰለባ የምንሆን መሆናችንን ስለምረዳ ዛሬ ቴዲ ባለበት ደረጃ ላይ አይደለም ብዪም እንድገምት ያስቻለኝ ይህ ከላይ የገለጽኩት የጋዜጠኛው ቀደምት አቋሞችን ፈጽሞ ባለመዘንጋትና ብሎም የሁለቱን ጥንታዊ ተጎራባች የሆነውን የአማራና ትግራይ ህዝብ አቀራርቦ ሰላማዊ የጉርብትና ግንኙነትን እውን ለማድረግ ከልቡ አምኖበት የሚጥር ልጅ የመሆኑም ይሁን መስሎ የመገኘቱ ጉዳይ ይህንን አጸፌታዊ ምላሽ እንድጽፍ እንዳስገደደኝ ስገልጽ አማራን ወንጅሎ የመክሰሱ ሁኔታ አዲስ ሆኖብኝ ሳይሆን እንደተለመደው በነውጠኞቹ ህወሃታዊያን የተሰነዘረ ቢሆን ኖሮ እንዳልሰማ የማልፈው መሆኔንም ለመግለጽም ነው፡፡

«የአማራ ብሄርተኝነት ከጥርስና ጥፍር በስተቀር አእምሮ የሌለው የመጣውን ሁሉ በጥላቻና በቀል ተሞልቶ የሚናከስና የሚባጨር ነው... የአማራ ልዩ ኃይል በምእራብ ትግራይ እንደማይኖርበት በማወቅ አጠቃላይ ቤቶችን እያፈራረሰ ወደ ጎንደር በማጋዝ ስፍራውን ለቅቆ ከመውጣቱ በፊት ምድረ በዳ እያደረገ ያለ ነው፡፡ ይህንን የሚያደርገው ደግሞ  ተሸንፌ እለቃለሁ ብሎ በማመኑ ነው...የአማራ ልዩ ኃይል በመቶሺህ የሚቆጠር ትግራዋይን ከምእራባዊ የትግራይ ግዛት አፈናቅሎ አባርራል፡፡ ሴቶችን ለደም ጥራት እያለ የሚደፍር አውሬ ነው...የአማራ ህዝብ የራሱን ጀግኖች እየበላ ሌሎችን እያጀገነ የካባቸው እንደነ ብርሃኑ ነጋ አይነቶች ዛሬ ተመልሰው እያስፈጁ ያሉ እስከመቼስ ተለጣፊና ተከታይ ሆነህ የአቢይና የኢሳያስ ተለጣፊ በመሆን እርዳታን ሆን ብሎ በማገድ ከአምስት ሚ ህዝብ በላይ በማስራብ ተግባር ላይ ትሰለፋለህና …ወዘተ 

ቴዲና እሳት አራጋቢና ቤኒዚን አርከፍካፊ ከሆነው ክፍሉ ሁሴን ከተናገሯቸው ውስጥ የሚጠቀሱ ውስን ናሙናዎች ናቸው፡፡

በተለይ እሳቱን አቀጣጣዩ ክፍሉ ሁሴን አድርባይነት ይውደም በሚል በአንዲት አማራ አክትቪስት የተጻፈ ብሎ ያቀረበውና በትምህረተ ጥቅስ ውስጥ መጨረሻ ላይ ያሰፈርኩትን ይዘት ስናየው ሙሉ በሙሉ ስለአማራ ህዝብ የሚናገር ሆኖ ይታያል፡፡

ብቻ በእለቱ ሁለቱም እየተቀባበሉ አማራን በአማራነቱ እንደ ህዝብ ሲተቹና ሲወነጅሉ ለሰማቸው ሰው እንዴ ርእዮት ሚዲያ መቼ ነው TMH የሆነው ብሎ እራሱን መጠየቁ አይቀሬ ነው፡፡

ለዚህ አንድን ህዝብ ሙሉ በሙሉ መክሰስና መወንጀልን ጉዳይ መሰረት የሆናቸው የሰሞኑ የዲፕሎማቲሲው ጎራ ማለትም ከአውሮፓ ህብረት ከስቴት ዲፓርትመንትና ከአንቶኒ ብሊንከን የተላለፉ መግለጫዎች ሲሆኑ በተለይም የአንቶኒ ብሊንከን የአማራ ልዩ ኃይል ከትግራይ ክልል ይውጣ ብሎ የጠቀሰውና ባለፈው ሳምንት በ CNN የትግራይ ሪፖርታዣዊ ዘገባ ላይ የአማራ ልዪ ኃይል ስም በጭፍጨፋና በአስገድዶ መድፈር በመጠቀሱ ነው ብለው ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡

እናም አሉ ትግራይ በመጥፎ ሁኔታ ላይ መሆኗን በመመልከት አማራው እንዴት እንዲህ አይነት አብሮ እማያኖር ድርጊት ይፈጽማል ሲሉ ነው እንግዲህ ህዝቤን እንደ ህዝብነቱ እያነሱ ሲጥሉ ያመሹት፡፡

ግን ይህ የሁለቱ መንፈስ የአማራንና የትግራይን ህዝብ ሰላማዊ ጉርብትናን እና ብሎም አብሮነትን ጠግኖ ማጠናከር ይቻለዋልን? 

ከሁሉ በፊት አስቀድሜ መግለጽ የምፈልገው በጎንደር ክፍለሀገር አስተዳደራዊ ግዛት ውስጥ ባለው ወልቃይት ጠገዴና ሁመራ ያለው ጀግናው የአማራ ልዩ ኃይላችን ሚሊሺያችንና ፋኖ በእነቴዲ የተነገረውን ውንጀላ ፈጽሟል አልፈጸመም የሚል ሙግት ሳልከፍት ምንም ፈጸመ ምን ቴዲና ክፍሉ ምን ያህል አይንና ልበግርድ ብትሆኑ ነው አማራ አማራ አማራ እያላችሁ አጠቃላይ አማራዊን ህዝብ ለማንጓጠጥ ለመወንጅልና ለመተቸት የቻላችሁት?? ብየዬ ለመጠየቅ እወዳለሁ፡፡

አንድም ጊዜ ተሳስተው እንኳን ከአቢይ ጋር ወግኖ የተሰለፈው  ብአዴን ነው ለማለት ያልሞከሩ ሁለት ተናጋሪዎች እርሰብርስ እየተቀባበሉ አማራ አማራ እያሉ የጅምላ ተጠያቂነትንና ተወንጃይነትን ሲሰጡ የትህነግ አማራን እንደህዝብ በጠላትነት የመፈረጅ መርዛኛ ትርክት በእያንዳንዱ የትግራይ ልብ ውስጥ ገዢ ስፍራ ይዞ ያለ ገዢ ሀሳብ መሆኑን ትረዳለህ፡፡

ሾላ በድፍኑ እንውሰድ ብለን እንኳን የጀግኖቻችንን አማራ ልዩ ኃይል ፈጸሙት የተባለውን ውንጀላ ምንም ሳናስተባብል ልክ ናቸው ብለን ብንቀበል እንኳን አሁንም በልዩ ኃይሉ እይታ መላውን የአማራ ህዝብ ጠቅልሎ የአማራን ብሄርተኝነትን «የመጣውን ሁሉ የሚባጨርና የሚናከስ ጥርስና ጥፍር እንጂ ጭንቅላት የሌለው » እያሉ እንዲሳደቡ ፈጽሞ በሞራልም ሆነ በህግ ቅንጣት ታህል መብት የሚሰጣቸው አይደለም፡፡ ህዝብን ከፖለቲካና ከፖለቲከኞች ነጥሎ ያለማየቱ ጥፋት ከሁለቱም በኩል ምንም ማብራሪያ እማያስፈልገው ይቅርታ እንዲጠይቁ ያስፈልጋል ብዬ እንዳምን ችያለሁ፡፡

አማራን በአማራነቱ ብቻ ለሰነዘራችሁት መሰረት የለሽና ለከት የለሽ ውንጀላችሁና ነቀፌታችሁ ይቀታ ልትጠይቁ ይገባል!!!

👉የኢትዮጲያ የበኩር ልጅ የሆነው ታላቁ አማራ መሪ ነው እንጂ ተለጣፊ ተከታይም ሆነ ሌላን አድናቂና አምላኪ አይደለም፡፡

የአማራን ተለጣፊነት ተከታይነትንና የራሱን ጀግኖች ሳይሆን የሌሎችን ጀግኖች አድናቂና አምላኪ አድርገህ የተናገርከው አንተ ክፍሉ ሁሴን የቴድ የዘወትር ተጋባዥ -ከንግግርህ አኳያ ተነስቼ የቀ.ኃ. ሥ ዘመነ መንግስት መገባደጃ አካባቢ የተወለድክ ስለመሆንህ ስረዳ እጅግ ስላንተ አፈርኩ፤ አዘንኩም፡፡ይህንን አባባል የዛሬው የወያኔ ' ትውልድ እድሜው ከ30ያለዘለለ ሰው ቢናገረው ምንም አይመስለኝም፡፡ የሚያውቀው ነገር የለምና ወይም እንዲያውቅ ተደርጎ የተጋተው አማራ ጠል ትርክት ነውና ግን አንተ አማራ ብለህ ስትጠራ ይህ ዛሬ በህይወት ያለውን አንድ ትውልድ ማንነትን ሳይሆን ከብሄረ አማራ የሚባለው ህዝብ ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ ያለውን የአማራን ህዝብ ታሪክ የመግለጽ መሆኑን እያወቅክ -የዛሬው ትውልድ አማራ ወይም በጊዜና በትውልድ ገደባዊ ድንበር ውስጥ ሳትገድብ አማራ እስከመቼ ተከታይና ተለጣፊ ይሆናል ብለህ በድፍረት መናገርህ (እኔ አልጻፍኩትም እንዳትለኝ እራስህ እስካመጣህው ዘንዳ)

ድድብናህንና Shortsighted ከአማራ ጥላቻ ጋር ለውሰህ የተላበስክ መሆንህን አሳየህን እንጂ የእኛን የአማራን ህዝብ የሺህ አመታትን ሀገር እያቀኑ የመምራታችንን ታሪክ አቅም ብቃትና ችሎታን ለቅንጣትም ያህል እንደማይቀንስብን አሊያም እንደማይሰረዝብን ጠንቅቀን የምናውቅ ህዝብ ነን፡፡

የአማራ ተብሎ የሚጠራው ህዝብና የሀገረ ኢትዮጲያ ታሪክ የዘመነ ወያኔው 30አመት ታሪክ ብቻ ያላቸው ናቸው እንዲ አማራን በዚህ በ30እና በ50አመት ታሪኩ ብቻ መዝነህ አማራ ተለጣፊ ተከታይና ሌላውን አድናቂ ብለህ የምትናገረው?

የዛሬው አማራ መኖር የሚገባውን አኗኗር እየኖረ ያለመሆኑ ሀቅነው፡፡ አልክድም፡፡ የዛሬው አማራ ብኩራናዊ መሪነቱን ተነጥቆ እየተመራ ያለ መሆኑ ሀቅ ነው፡፡ ጥያቈ የለውም፡፡ ይህ ተመሪ ያልከው አማራ የዛሬው ትውልድ ይባላል እንጂ አማራ በሚለው መጠሪያ አጠቃላይ የአማራን ህዝብ ታሪክን እንዲገልጽ አይደረግም፡፡

ግን አንድ ነገር አረጋግጥልሃለሁ ብዙም ሳትቆይ በዘመንህ በህይወት እያለህ የዛሬው አማራዊ ትውልድ የአባቶቹን የመሪነት ስፍራን ተቆጣጥሮ ሲመራ ታያለህ፡፡

👉የአማራ ብሄርተኝነት፦

በኢትዮጲያ ካሉት ነፍሰ በላና መርዛማ ብሄርተኝ ኃይሎች ማለትም በትህነግ በተፈጠረው የትግራይ ብሄርተኝነትና በኦነግ በተፈጠረው የኦሮሞ ብሄርተኝነት ጋር ፈጽሞ በይዘትም በቅርጽም በሞራልና በአላማም አቻ ተመሳሳይነት የሌለውንና እጅግ ልዩ Unique የሆነውን የአማራን ብሄርተኝነትን በጥላቻና በቂም ተሞልቶ ከመጣው ጋር ሁሉ የሚናከስበትንና የሚቧጨርበትን ጥርስና ጥፍር እንጂ ማሰቢያ ጭንቅላት የሌለው ብሎ መግለጽ ጥሩ የማሰብና የማገናዘብ ችሎታ ያለው ሰው የመሰለኝ ቴድሮስ ፀጋዬ እራሱ ማሰቢያ ጭንቅላት ያጣ ወይም የተነጠቀ አሊያም የተቀበረበት ሰው መሆኑን ነው ያሳየኝ እንጂ ከተፈጠረ እንኳን እጅግ አጭር የለጋ እድሜ ላይ ያለውን የአማራ ብሄርተኝነትን ይገልጻል ብዪ አላስብም፡፡

የትግራይና የኦሮሞ ብሄርተኛ ኃይሎች መፈጠሪያ አስኳል ጸረ አማራ ጸረ ኢትዮጲያ ተጨቁነናል ተረግጠን ባሪያ ሆነናል እና መሰል በሆኑ መርዘኛና ኔጋቲቭ የመፈጠሪያ ዘርና ፅንስ ውስጥ የተፈጠሩ ኃይሎች በመሆናቸው ገና ሀ ብለው ተወልደው እትብታቸው ከተቆረጠ ጊዜ አንስቶ እስከመንግስትነታቸው ድረስ አማራውን ኦርቶዶክስን የኢትዮጲያን ታሪክ ላይ ግልጽ ጦርነትን ከፍተው ሁልቆ መሳፍርት የሌለው ጉዳት ያደረሱና ዛሬም እያደረሱ ያሉ ሆነው ሳለ ይህንንም ስነባህሪያዊ ማንነታቸውን ለአማራ ብሄርተኝነትና ብሄርተኛ ኃይሎች ሰጥቶ መሳደብ ከማስተዋል ጉድለት አሊያም የትህነጋዊው ትርክት ሰለባነትን ማሳየት ነው፡፡

ሲጀመር የአማራ ብሄርተኝነት እንደ ትግራዩና ኦሮሞው አንድም ህዝብና እሴትን ጠላቴ ነው ብሎ ያልፈረጀ፡፡ኢትዮጲያዊነትንና አንድንም ኢትዮጲያዊያንን ጠላቴ ያላለ በአንጻሩም በትግራዩና በኦሮሞው ብሄርተኛ ኃይሎች አደጋ ላይ የወደቀችን ሀገረ ኢትዮጲያን እና ብሄረ አማራን ህልውና ለመታደግ በአማራነቴ መደራጀትና መታገል ግዴታዪ ነው ብሎ የተፈጠረን Positive Force ከማን ጋር እንደተቧጨረና እንደተናከሰ ባልተገለጸበት ሁኔታ ቴዲ የአማራን ብሄርተኝነትን ልክ እንደ አበደ ውሻ ከመጣው ጋር ሁሉ የሚናከስና የሚቧጨር ብሎ ሲገልጸው፦

1ኛ) የአማራ ብሄርተኛ ኃይልን ከጥንት ጀምሮ ያለ መሆኑንና ሌሎች እየመጡ ሲሄዱ እሱ በቋሚነት የሚኖር መሆኑን

2ኛ) ከአንድና ከአንድ በላይ ከሆኑ ኃይሎችና ህዝብ ጋር የተጋጨ መሆኑን ነው ቴዲ የነገረን፡፡

የአማራ ብሄርተኝነት መቼ ተፈጠረ ከማንስ ጋር ተናከሰ ተቧጨረ ለሚለው ጥያቄ ቴዲ መልስ ይኖረዋል?

👉ከመረብ ምላሽ ምእራባዊ የትግራይ አስተዳደር ወይም የትግራይ ግዛት የሚባል የለም፡፡

ስለዛሬውም ሆነ ነገ የአማራና የትግራይ ሰላማዊ ጉርብትና ስናወራ እኔ ወልቃይት ጠገዴን የጎደር አውራጃ ራያን የወሎ አውራጃ አድርጌ የትግራዩ ቴድሮስ ጸጋዬ ደግሞ ወልቃይት ጠገዴና ራያን ምእራባዊ የትግራይ ግዛት እያለ በሚገልጽበት ሁኔታ ስለሁለቱ ህዝብ ሰላማዊ ጉርብትና እና አብሮነት ፈጽሞ ልናወራ አንችልም፡፡

አዲሱ የትግራይ ትውልድና የፖለቲካ ኤሊቱ የትህነግን መርዘኛ ትርክት ሙሉ በሙሉ በመቅበር አዲሱ የራሱ የሆነ wayward የሚሆን Progressive እይታ አስተሳሰብና አቋምን ይዞ ብቅ ካላለና ዛሬ ቴዲ «የአማራ ልዩ ኃይል ወልቃይት ጠገዴ የእነሱ እንደላሆነና እንደማይቆዩበት ስላወቁ ቤት እያፈረሰ ወደ ጎንደር እያጓጓዘ ነው» ብሎ እየተናገረ በአንቶኒ ብሊንከን ትእዛዝ የአማራ ልዩ ኃይል ይወጣል እያለ እያሰበና እየተመኘ የአማራና የትግራይ ሰላማዊ አብሮነትና ጉርብትናን ልናስብም ሆነ ልናወራ ቅንጦት ነው የሚሆነው፡፡

‎ 👉ከተከዜ መልስ የትግራይ ግዛት የለም

ሆንግ ኮንግን ለ150 አመታት ያህል ስትገዛት የነበረችው እንግሊዝ እስከወዲያኛውም ለመግዛት ብትፈልግም ሆንግ ኮንግ የቻይና ነበረችና በ1997 ሳትወድ በግድ መለሰች፡፡ ቻይና ስትዳከም ሆንግ ኮንግን ያዘች ግን ቻይና ስትጠናከር መለሰች፡፡

የአማራና ትግራይ ግንኙነት ጉዳይ ለማውራት የወልቃይት ጠገዴ ራያ ጉዳይ ላይ የትግራይ ተወላጆች የትህነግን መርዘኛ ትርክት ቀብረው መቅረብ ሲችሉ ነው፡፡

«የአማራ ልዩ ኃይል መሬቱ እንዳልሆነና እንደማይቆይ ስላወቀ ከምእራብ ትግራይ ቤት እያፈረሰ ወደ ጎንደር እያጓዘ ነው» የሚለው የቴዲ ክስና በአንቶኒ ብሊንከን ድጋፍ መሬታችንን እናስመልሳለን የሚለው ድምጽ የሚያሳየን የህነግን ትርክት ዘላለማዊ የማድረግን እምነትና አቋም ነው፡፡

ይህ ደግሞ ለአማራ ጠላትነትን የማወጅ ያህል ነው፡፡

ዛሬ ባለኝ መረጃ የአማራ ልዩ ኃይል በወልቃይት በጠገዴ በሁመራ በዳንሻ ከጎንደር እያጋዘ በመገንባት ላይ መሆኑን እንጂ ለቅቄ ስለምወጣ ብሎ እያፈረሰ ያለመሆኑን ነው፡

በአዲ ረመጥ ግንቦት 14ቀን የሚከበር የምስጋና ፌስቲቫል ያዘጋጀው ይህንኑ ግንባቷን የሚያረጋግጥ ነው፡፡ 

ከወልቃይት ጠገዴ ሁመራ ራያ የሚወጣ አንድም አማራ የለም፡ አይኖርምም፡፡አማራ ባልተደራጀበት

ወቅት የተደራጀችው ትህነግ እርስታችንን ወረሰች፡፡ ይንን ወረራና ዘረፋን የዛሬው የትግራይ ትውልድ ተገቢና የሚገባ ነው መሬቶቹ በቃ ከሰላሳ ዓመት በፊት ስለያዝናቸው የእኛው ናቸው የሚል ከሆነ የአማራን ሰላማዊ ጉርብትናን እንዳልፈለገና የትህነግን ትርክት መርሁ ያደረገ ይሆናል ማለት ነው፡፡ አማራ ደግሞ የትህነግን ትርክት መሰረት አድርገው ሊያዩትና ብሎም በትህነጋዊ ትርክት ላይ ተመስርተው ሊቀርቡት ለመፈልጉ ትግራይ ሆነ ማን ፈጽሞ ቦታ የለውም፡፡ የትህነግን ትርክት ግብአተ መሬት አስገብቶ በሚታወቅበት ጥንታዊ የአማራ ማንነቱ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ድርሻውን እውቅና ከሚሰጡት ጋር ነው ሰላማዊ ጉርብትናን እና አብሮነትን መመሰረት የሚፈልገው፡፡

የአማራ ተፈጥሮአዊ መብትና ጥቅም የማንንምና የሌላኛውን ህዝብ እውነተኛና ሀቀኛ ጥቅምን የሚጻረርና  የሚጋፋ ፈጽሞ አይደለም፡፡

ይህ ሳይሆን ቀርቶ ለሰላማዊ ጉርብትና እና አብሮኗሪነትና ብሎም የፖለቲካ አላያንስ ግንባር ለመፍጠር ተብሎ አማራው አይደለም ወልቃይት ጠገዴና ራያን ይቅርና ስንዝር እርስቱን ይለቃል ማለት ከንቱነት ነው፡፡

ይህ ፈጽሞ አይታሰብ፡፡የማይሆንና የማይታሰብ ኢኩዌሽን ነው፡፡

እኛን የሚያቀራርበን እኔ የትግራይን ሀቅ እውቅና የምሰጠውን ያክል ከትግራይም ተመሳሳይ እኩልነትን መሰረት ያደረገ የአማራን ሀቅና እውነት እውቅና ሲሰጥ ብቻ ነው፡፡ 

ይህንን አይነቱን ፍታሃዊ አላያንስ አማራ ከጎረቤቱ ትግራይ ጋር ለመመስረት ይፈልጋል፡፡ነገር ግን አቢያን ለመጣል ሲባል እርስታችንን ትተን የምንፈጥረው ትብብር ፈጽሞ አይኖርም፡፡ አማራ የሚያደርገውን የህልውናን ትግል ያለማንም ትብብርና አላያንስ እራሱ በራሱ አካሂዶ በድል እንደሚወጣው ምንም ጥርጥር የለም፡፡

እናም ከትግራይ ወገኖቻችን በዚህ የአማራ ሀቅ ላይ ጥርት ያለ አቋምና ግልጽ ውሳኔ እንፈልጋለን፡፡

በተረፈ መግለፅ የሚገባን ወሳኝ ነጥብና አቋም ቢኖር የህወሃትን መደምሰስ ሙሉ በሙሉ እንደግፋለን - በተመሳሳይ መልኩ የሻእቢያን ወረራ ፈፅሞ እንቃወማለን::

ስለተከሰተው ጭፍጨፋ ሀዘን ይሰማናል እናዝናለን:: ስለርሃቡ እና አቢይ በትግራይ ላይ ስለሚያራምደው ፖሊሲ እናወግዛለን:: የሰብአዊ መብት ረገጣን ፈፅሞ እንቃወማለን::

አዎን የአማራ የህልውና ትግልና የአማራ ብሄርተኝነትም ለትግራይ ህዝብ ህልውና ቅንጣት ታህል ስጋት የደቀነና ስጋት ላይ የሚጥል ቅንጣት ታህል አደጋን ያላዘለ መሆኑንም አስረግጠን ለመግለፅ እንፈልጋለን::


Comments

Popular posts from this blog

አለም አቀፍ የፋኖ ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ነኝ የሚለው ቡድን ዓላማ ምንድነው ? በወንድወሰን ተክሉ

ይህ ምስል ጸሃፊውን አይወክልም! «...አማራ ለ450 ዓመታ መንፈሱ የተሰበረ ገበሮ ሕዝብ ነው..» ሀብታሙ ተገኝ (ፕ/ር) « እኔ እስክንድር  የአማራ ሕዝብ ከደረሰበት የህልውና አደጋ እኩል የሚሆን ዓላማ አለው ብዬ አላምንም» አቻምየለህ ታምሩ፤ አለም አቀፍ የፋኖ ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ነኝ የሚለው ቡድን ዓላማ ምንድነው ? በወንድወሰን ተክሉ እራሱን አለም አቀፍ የፋኖ ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ነኝ የሚለው ቡድን የዙም ውይይት ፕሮግራም ክፍል ሁለትን የተመለከተ ምልክታ:- ባለፈው  ወር ብቻ ሳይሆን ባለፈው ዓመት ዴሴምበር 2023 ( ዛሬ ጃንዋሪ 1 ቀን 2024 ነን)  እራሱን አለም አቀፍ የፋኖ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ብሎ የሚጠራው ቡድን «ጸረ አማራ ኢትዮጲያዊነት» በሚል አርእስት ስር ሀብታሙ ተገኝ (ፕ/ር) ዋና ተናጋሪ ተጋባዥ የሆነበትን  የዙም ውይይት አካሂዶ የነበረ ሲሆን የዚህ ውይይት ክፍል ሁለት  ባሳለፍነው ወር ዴሴምበር 23ቀን በማዘጋጀት አቻምየለህ ታምሩና ሀብታሙ ተገኝ (ፕ/ር) ተናጋሪ እንግዳ በማድረግ አካሂዷል። በእርግጥ  ከዚህ ከሁለተኛው የውይይት ፕሮግራም በፊት በተክሌ ይሻው በኩል የዙም ሊንክ ተልክሎኝ በሰዓት ጥበት ምክንያት መገኘት ባልችልም ዛሬ ግን በቻናላቸው ላይ የጫኑትን ይህን ክፍል ሁለት ውይይት ከተመለከትኩ በኋላ ይህን ምልክታዬን  አንባቢው ሊረዳ በሚያስችል መልኩ አንድ ሰዓት ከሰላሳ ደቂቃ የፈጀን ውይይት ይዘት በመጭመቅ እንደሚከተለው አቅርቤያለሁ። ይህ ምስል ጸሃፊውን አይወክልም! 1ኛ - ውይይቱን አዘጋጅን ማንነት በተመለከተ፦  አለም አቀፍ የፋኖ ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ባለፈው መስከረም ወር ላይ  በጌታቸው በየነ ሰብሳቢነት ተመሰረትኩ ብሎ እራሱን ያስተዋወቀ ሲሆን ጌታቸው በየነ ማለት ደግሞ በወቅቱ የ I AM ሰብሳቢ የነበረ እና

The Anti Semitic stand of the OLF : Speech at the Jerusalem Center for Public Affairs in Jerusalem

By Dawit Giorgis The most dangerous crisis in Africa is one unfolding in the Horn of Africa, in Ethiopia. It is a complicated crisis triggered by extremist elements to create an ethnocentric government, which makes one ethnic group superior to all others. The country has been sucked into a quagmire of unending internal wars and terrors that have taken countless  lives, and is characterized by one of the most gruesome crimes in history.  The country has become a failed state, with no  functional central government,  run by a group of ethnic warlords from the Oromia region, where the current PM has been elected.   After the collapse of the brutal regime of the Tigrai People’s Liberation Front (TPLF) by a popular uprising over four years ago, the Oromo-dominated government under Prime Minister Abiy Ahmed has endangered the very foundation of the country. The social fabric of this age-old nation is torn asunder, and the history of the land,  which is rooted in biblical  teachings, is under

"ከአሁን በሆላ ፋኖ ወደ አንድነት መምጣት አለባቸው የሚባለው አካሄድ አይሰራም" :: በወዳጄ/ቤተ አማራ ወሎ

ከአሁን  በሆላ  ፋኖ  ወደ  አንድነት    መምጣት  አለባቸው  የሚባለው  አካሄድ  አይሰራም::  ክህደት   ከተፈፀመ  በሆላ  አንዱ  ቡድን  ከሌላው  ስር  ሆኖ  ይቀጥላል  ማለት  የማይቻል   ነው::  ምክኒያቱም 1ኛ:- 27  ቀን  ቁጪ  ብለው   መክረዋል :: እያንዳንዱ  አደረጃጄት  ሰነድ  ፅፈው  አቅርበዋል::  በቀረበው  ሰነድ  ላይ  ከፍተኛ  ውይይት  ተደርጎበት  የሚወድቀው  ወድቆ  የሚፈለገው  ፀድቋል::ቃለ  መሀላ  ፈፅመው   ወደ  ምርጫ   ለመግባት  ተስማምተዋል:: እጃቸውን  አውጥተው   ከመረጡ  በሆላ    ግን    "ጨዋታ  ፈረሰ  ዳቦ  ተቆረሰ"   የሚል  የህፃን  ልጂ  ጨዋታ  ውስጥ  መግባት   የአማራን  ህዝብም  ሆነ  የፋኖን  ትግል  መናቅ  ነው:: ይህ  አልበቃ  ብሎ   "ምርጫው  ከኛ  እውቅና  ውጪ  ነው  እኛ  አናውቀውም"  የሚል   የውሸት    የህፃን  ልጂ  ፕሮፓጋንዳ   እንዲሰራጪ  አድርገዋል::ከዚህ  በሆላ   ይህ  ቡድን  የታላቁ  እና  የጠቢቡ   የአማራ  ህዝብ  መሪ  ነኝ    ብሎ   አይኑን   በጨው   አጥቦ  ለመምጣት  እንዴትስ  ይደፍራል ????   የድምጽ ቅንብሩ ጸሃፊውን አይወክልም።  2ኛ:- የፋኖ  ወታደራዊ  ጦር  ዋና  አዛዢ   የሆነው  ሻለቃ  ዝናቡ  የራሳቸውን   ድክመት  እና  ሴራ  በአማራ  ህዝብ  ላይ  ለማሸከም   የአማራን  ህዝብ  በጂምላ    ይህ   "ጎጃም  ጠልነት  ነው"   ብሎ  ከወነጄለ  በሆላ   ይቅርታ  ሳይጠየቅበት   በጋራ  ለአንድ  አላማ  እንዴትስ     መስራት  ይቻላል???  የአማራ   ጪምብላቸውን  አውልቀው  እንዴትስ  በመቅፅበት  ወደ  ጎጣቸው   ተወርውረው  ሊገቡ  ቻሉ???  አጄንዳቸው   እንዴትስ