ግራፊክ ምስል ዴቭ ዳዊት |
Dave Dawit
/We are a voice for unprotected civilian Amharas, Not for the willing servant of the fascistic Regime
* በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተጠቀሱት ታሪኮች የአቤልና የሶምሶን ታሪክ፥ አሁናዊውን የአማራ ፖለቲካ ሁኔታ ይገልፀዋል።
አቤል የተገደለው በየዋህነት ወንድሙ ቃየንን አምኖ ወደ መገደያ ሜዳ በመውጣቱ፣ የሞት አደጋ እንደሚደርስበት የሚያውቅበት አንዳችም precedence አለመኖሩና ራሱን የሚከላከልበት አንዳችም ነገር በእጁ ባለመኖሩ ነው። በግፍ የፈሰሰው የአቤል ደም፥ በኢምፓየሯ ኢትዮጵያ በየቀኑ እየፈሰሰ የሚገኘው የብዙ ሺህ ንፁሐን አማራዎች ተምሳሌት ነው።
በአንፃሩ ሶምሶን ከውልደቱ ጀምሮ የእግዚአብሔር ኃይል ያረፈበት ብርቱ ተዋጊ ነበር። ነገር ግን ሶምሶን በአመንዝራይቱ ደሊላ ፍቅር የተሸነፈ ሰውም ነበር። የሶምሶንን የኃይል ምስጢር ለማወቅ አመንዝራይቱ ደሊላ በአማላይ የሽንገላ ቃላቶች ሶምሶንን አታልላ ትጥቁን አስፈታችው። በመጨረሻም ሶምሶን በአመንዝራይቱ ደሊላ ጭን ላይ እንደተኛ ትጥቁን በፈታበት ሁኔታ (የኃይሉ ምስጢር የነበረውን ፀጉሩን ደሊላ በጭኗ ላይ አስተኝታ ላጭታው ስለነበር) በባላንጦቹ ፍልስጤማውያን እጅ ተያዘ። ከዚያ በኋላ ያለው የሶምሶን ታሪክ የባርነትና የውርደት ሞት ነው።
"የአማራ ልዩ ኃይልም" የሶምሶንን የውድቀትና የውርደት ጉዞ አንድ ብሎ ጀምሯል። ትጥቁን አስረክቦ ለፋሽስቱ የኦሮሙማ መንግስት ዙፋን ጠባቂ የመሆን ተስፋ ሰንቆ ሲጓዝ፥ የአመንዝራይቱ ደሊላ ምሳሌ የሆነው ፋሽስታዊው የኦሮሙማ መንግሥት ስልሣ የልዩ ሀይል አባላትን በጅምላ ገድሏቸዋል። ይህ የውርደትና የቁልቁለት ጉዟቸው ጅማሬ እንጂ ፍፃሜያቸው አይደለም‼‼‼
መሣሪያውን ወደ ብ.አ.ዴ.ን (A.N.D.M.) እና ወደ ፋሽስታዊው የኦሮሙማ መንግስት ያዞራል ተብሎ ሲጠበቅ፥ "የፋሽስት ዙፋን እጠብቃለሁ" ብሎ ትጥቅ ለፈታ ሀይል የሚያዝን ልቦና የለኝም‼‼‼
እኛ ዕረፍት አልባ ጩኸት የምንጮኸው እንደ አቤል ደም በግፍ ለሚፈስሰው የህዝባችን ደም እንጂ፥ የፋሽስት ዙፋን ለመጠበቅ ሲል ትጥቁን በአመንዝራይቱ ደሊላ የሽንገላ ምክር ለፈታ ከሃዲ ኃይል አይደለም‼‼‼
ፈጣሪ የአማራን ህዝብ አብዝቶ ይባርክ‼‼‼
ዴቭ ዳዊት
Publisher’s note: views in the article reflect the views of the writer, not the views of tbf.2tbf.org
Comments