Skip to main content

ከኢትዮጵያ መፍረስ በኋላ የአማራ ህልውና እንዴት ይቀጥል⁉ (ለማይቀረው የአባት ሀገር አማራ ምስረታ እንዘጋጅ ‼)


በዴቭ ዳዊት።

ከኢትዮጵያ መፍረስ በኋላ የአማራ ህልውና እንዴት ይቀጥል⁉

(ለማይቀረው የአባት ሀገር አማራ ምስረታ እንዘጋጅ ‼) 

================ /ክፍል-2/ =============

በክፍል አንድ ግልፅ ለማድረግ እንደሞከርሁት ሀገሪቱ "An empire in a terminal collapse" በሚባለው የአይቀሬው የመፍረስ ዋዜማ ላይ ብትሆንም፥ የአማራ ህዝብ ግን ከገባበት ጥልቅ ድንዛዜ ወጥቶ የራሱን አባት ሀገር እውን ለማድረግ እየሞከረ አለመሆኑ፤ ለዚህም በምክንያትነት ያስቀመጥኋቸው ነጥቦች ሲኖሩ፥ በዚህ ሁለተኛ ክፍል በይደር ካቆምንበት እንደሚከተለው እንቀጥላለን። መልካም ንባብ! 

2. "The Chosen People" Analogy፦ 

* የአማራን ህዝብ "ብፅዕት ኢትዮጵያ" በሚል ቅዠት አስረው በዚህ መጠን እንዲደነዝዝና "Idolatry of Ethiopia" የህዝባችን መገለጫ Trademark እንዲሆን ካደረጉት ዋነኛ ተግዳሮቶች መካከል ራሱን በሃይማኖት በተለይም በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያናችን ጉያ ለበርካታ መቶ አመታት የደበቀ የ Neuro-Pirates መሠሪ ቡድን በህዝባችን ላይ በከፈተው የ Cognitive Warfare አማካኝነት ነው። የአማራ ህዝብ የ Cognitive Warfare ሰለባ መሆኑን አምነን መቀበል ይኖርብናል‼‼‼ መፍትሔ ማምጣት የምንችለውም ከዚህ መራራ እውነት ስንነሳ ብቻ ነው‼‼‼ 

የአማራን ህዝብ የ Cognitive Warfare ሰለባ ማን አደረገው⁉

"When you control a man's thinking you do not have to worry about his actions. You do not have to tell him not to stand here or go yonder. He will find his 'proper place' and will stay in it. You do not need to send him to the back door. He will go without being told. In fact, if there is no back door, he will cut one for his special benefit. His education makes it necessary." 

             ( Carter G. Woodson)

* በአማራ ህዝብ ላይ የተራዘመ የ Cognitive war በመክፈት ከውስጥ ሲገዘግዘው የኖረው ኃይል ራሱን በቤተክርስቲያን ጉያ የደበቀ ከግል ጥቅም በዘለለ አንዳችም ራዕይ የሌለው አቴና-ወጊ የ Neuro-Pirates ስብስብ ነው‼‼‼ 

ይህ በቤተክርስቲያን ጉያ የተሸሸገው Neuro-Pirates ኃይል ከቤተክርስቲያኗ ዶግማዊ አስተምህሮ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የሌለው፣ ለቤተክርስቲያናችንም እንዲሁም 80% ለሚሆነው የእምነቱ ተከታይ ለሆነው የአማራ ህዝብም ዋነኛ ጠላት ሲሆን የዚህ ቡድን ከትናንት እስከ ዛሬ ብቸኛ ፍላጎት በሃይማኖቷ ታዛ ተጠልሎ ህዝባችንን "የተመረጠችው ኢትዮጵያ ጠባቂ ነህ" በማለት መንፈሳዊ ሽፋን በመስጠት ህዝባችንን አደንዝዞ የግል ጥቅሙን ማሳደድ ነው። 

ይህ በዘመን ቅብብሎሽ ራሱን እየተካና እያባዛ የሚሄድ አቴና-ወጊ የ Neuro-Pirates ቡድን ፥ የአማራ ህዝብ ጄኖሳይድ ሲፈፀምበት ወይ ዝምታን ይመርጣል አልያም ጉዳዩን የሃይማኖት ቅርፅ ያለው ለማስመሰል ይጥራል (በሻሸመኔና ሐረር በአማራ ላይ የተፈፀመውን ጄኖሳይድ ወደ ሃይማኖት ለመቀየር የሄደበትን ርቀት እያሰብን) ይህም ካልተሳካለት "ቅድስት ኢትዮጵያ ልትፈተን ግድ ነው" ብሎ በአማራ ህዝብ እልቂት ይሳለቃል። 

ይህ ኃይል በቤተክርስቲያን ውስጥ ይመሽግ እንጂ ቤተክርስቲያናችን ራሷ አደጋ ላይ ስትወድቅ ድምፁን ማሰማት አይፈልግም። ለዚህም ነው ይህ አቴና-ወጊ የ Neuro-Pirates ቡድን የአማራ ህዝብ ብቻ ሳይሆን የቤተክርስቲያናችንም ጠላት ነው የምንለው‼‼ 

ይህ አቴና-ወጊ ቡድን ምናባዊ አይደለምና ከግብሩና ጎልተው ከሚታዩ መሪዎቹ ጋር በማያያዝ መጠሪያ ስም ሰጥተነው ልናልፍ ይገባል‼ 

በመሠረታዊነት ይህ አቴና-ወጊ ቡድን ህዝባችንን "በቅድስት ኢትዮጵያ" ተረት ሲያደነዝዝ የኖረው በሁለት መልኩ ነው፤ 

1. Numerology የሚባልን ነገር እንደ አዲስ ግኝት በማስተጋባት "ይህ ቁጥር ቅዱስ ነው፣ የኢትዮጵያ ቁጥር ምስጢራዊው ቅዱስ ቁጥር በመሆኑ አትፈርስም" የሚል ተረትና ባዶ ጥንቆላ ሲሆን ይህንን ተረት ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲቀባበሉት መጥተው አሁን ዶክተር ሮዳስ ታደሰ በሚባል ተላላኪ ባንዳ በዋናነት እየተቀነቀነና ህዝባችን በዚህ ተረት ደንዝዞ ሀገር አልባ እንዲሆን እየተሰራበት ይገኛል። 

ይህንን በቁጥር የሚጠነቁል አቴና-ወጊ ኃይልና ግብረአበሮቹን ከዚህ በኋላ "ሮዳሳዊያን" በሚል ልንጠራው ግድ ይላል። 

2. ሌላኛው ህዝባችንን በተረት አደንዝዞ ሀገር አልባ ሊያደርግ እየሰራ የሚገኘው አቴና-ወጊ ኃይል "Ethiopia is a spiritually mysterious land" ብሎ ከመስበክ አልፎ "ኢትዮጵያ የተሰወሩ ከተሞች ያላት፣ እግዚአብሔር ከሌላው ዓለም በተለየ ልዩ ጥበቃ እንደሚያደርግላት" የሚሰብክ፣ መፅሐፍ የሚፅፍና ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ህዝባችንን ሲያደነዝዝ የኖረ ኃይል ነው። እንደ ሮዳሳዊያን ክንፍ ሁሉ፥ ይህም ቡድን ከትውልድ ወደ ትውልድ ይህንን ተረት ሲያስቀጥል ኖሮ ዛሬ አውራ መሪ አለው፦ ዶክተር አለማየሁ ዋሴ የተባለ የብአዴን "የአማራ መልሶ ማቋቋም ድርጅት" መሪና በቤተክርስቲያን ጉያ የተሸሸገ ተላላኪ ባንዳ። ስለሆነም ይህንን ክንፍ "አለማየዋዊያን" ብለን ልንጠራው ግድ ይላል። 

* ሮዳሳዊያንና አለማየዋዊያን ዛሬ በአማራ ህዝብ ላይ እየፈፀሙ ያሉትን አይነት ማደንዘዣ የእስራኤል ራባዮች (Rabbis) በአይሁድ ህዝብ ላይ ለሁለት ሺህ አመታት ሲፈፅሙት የነበረው አይነት ማደንዘዣ ነው። የእስራኤል ራባዮች የአይሁድ ህዝብን "እስራኤል በአንዳች መንፈሳዊ ተአምር ሀገር ሆና ትመሰረታለች፣ በቀጣዩ አመት ፀሎታችንን በኢየሩሳሌም እናደርጋለን" እያሉ ከመስበክ አልፈው የፀሎታቸው መቋጫ እንዲሆን አሳምነውት ነበር። የራባዮቹ "የቀጣይ አመት በኢየሩሳሌም ..." ተረት ግን አይሁድን ለሁለት ሺህ አመታት ከዘግናኝ እልቂትና ሰቆቃ አልታደገውም። አይሁድን የታደገው የፅዮናዊያን ብሔርተኛ እንቅስቃሴ ነው‼‼‼የአይሁድን ህዝብ ባለ ሀገር ያደረገው የራባዮች ተረት ሳይሆን የቴዎዶር ሄርዝልና ጓደኞቹ በተግባር የተደገፈ የፅዮናዊያን ብሔርተኛ ንቅናቄ ነው‼‼‼ 

ያዕቆብ (የአብርሃም የልጅ ልጅ) "እስራኤል" የሚለውን ስያሜ ካገኘ ጀምሮ እስከ ዮሐንስ ራዕይ ድረስ ይህ ስም በመፅሐፍ ቅዱስ ያልተጠቀሰበት ቦታ የለም። ያ ማለት ግን ሀገር አልባ ላለመሆን ወይም ተሳዳጅ ላለመሆን ዋስትና ነው ማለት አልነበረም። 

በተመሣሣይ፥ ሮዳሳዊያንና አለማየዋዊያን "ኢትዮጵያ በመንፈሳዊው ዓለም ፍፁም የተለየ ስፍራ ያላት፣ ህዝቦቿም በፈጣሪ የተመረጡ" አድርገው የሚያስተምሩት ተረታቸው ህዝባችንን ክፉኛ በማደንዘዝ አላስፈላጊ ዋጋ እንዲከፍል ሲያደርገው ኖሯል፤ ዛሬም እያስከፈለው ይገኛል። 

ህዝባችንን ከዚህ የ Neuro-Pirates Cognitive warfare ነፃ ማድረግ ካልቻልን የአማራን ህዝብ ከፈፅሞ መጥፋት መታደግም ሆነ እፎይታ የሚያገኝበትን አባት ሀገር ምስረታ እውን ማድረግ ፈፅሞ አንችልም‼‼‼ 

ስለሆነም ለዘመናት በህዝባችን ላይ ተከፍቶበት የቆየውን cognitive war ለመቀልበስ Reverse Social Engineering መጠቀም ይኖርብናል ‼‼‼ ይህንን ስናደርግ ሰለባ ከሆነው vast majority የህዝባችን ክፍል ብቻ ሳይሆን "ብሔርተኛ" ናቸው ከምንላቸው የቅርብ ጓዶቻችን ሳይቀር ቀላል የማይባል Cognitive Inertia እንደሚጠብቀን ለአፍታም ቢሆን መጠራጠር የለብንም‼‼‼ 

እንደ አማራ ህዝብ ለረጅም ዘመናት የ Cognitive warfare ሰለባ ሆኖ በኖረ ህዝብ ላይ የ Reverse Social Engineering Programme ተግባራዊ በሚደረግበት ጊዜ ነባሩን የጥፋት እሳቤ የሚተካ ገንቢ እሳቤ አስቀድመን ለህዝባችን በሰነቅንለት ራዕይ ልክ ካላዘጋጀን Paradigmatic Vacuum መፈጠሩ አይቀሬ ነው‼‼‼ ይህ አይነቱ  Paradigmatic Vacuum ሳይፈጠር በህዝባችን ልብና አዕምሮ ላይ በፍጥነት  እኛ የምንፈልገውን አምሐራዊ Ultranationalism (in its refinest form) ማስረፅ ይኖርብናል‼‼‼

** ህዝባችን የገባበትን ጥልቅ ድንዛዜ La Belle Indifférence ("Beautiful Ignorance") በሁለት ክፍል በአጭሩ ያየንበትን በዚህ እንቋጭና አይቀሬው የኢምፓየሯ ኢትዮጵያ መበተን in what form ሊከናወን ይችላል የሚለውን፤ እንዲሁም በእያንዳንዱ አማራጭ የኢምፓየሯ የፍርሰት ሁኔታ ውስጥ  የአማራ ህዝብ ዕጣ ፈንታ ምን ሊሆን ይችላል? የሚለውን በክፍል ሶስት የምናየው ይሆናል ለዛሬው በዚህ ይብቃን።

=========== ይቀጥላል ==========

እግዚአብሔር የአማራን ህዝብ አብዝቶ ይባርክ‼‼‼ 

የጠራ ራዕያችንና ቅዱሱ ተልዕኳችን አባት ሀገር አማራን መመስረት ነው‼‼‼

ዴቭ ዳዊት።

Comments

Popular posts from this blog

"ከአሁን በሆላ ፋኖ ወደ አንድነት መምጣት አለባቸው የሚባለው አካሄድ አይሰራም" :: በወዳጄ/ቤተ አማራ ወሎ

ከአሁን  በሆላ  ፋኖ  ወደ  አንድነት    መምጣት  አለባቸው  የሚባለው  አካሄድ  አይሰራም::  ክህደት   ከተፈፀመ  በሆላ  አንዱ  ቡድን  ከሌላው  ስር  ሆኖ  ይቀጥላል  ማለት  የማይቻል   ነው::  ምክኒያቱም 1ኛ:- 27  ቀን  ቁጪ  ብለው   መክረዋል :: እያንዳንዱ  አደረጃጄት  ሰነድ  ፅፈው  አቅርበዋል::  በቀረበው  ሰነድ  ላይ  ከፍተኛ  ውይይት  ተደርጎበት  የሚወድቀው  ወድቆ  የሚፈለገው  ፀድቋል::ቃለ  መሀላ  ፈፅመው   ወደ  ምርጫ   ለመግባት  ተስማምተዋል:: እጃቸውን  አውጥተው   ከመረጡ  በሆላ    ግን    "ጨዋታ  ፈረሰ  ዳቦ  ተቆረሰ"   የሚል  የህፃን  ልጂ  ጨዋታ  ውስጥ  መግባት   የአማራን  ህዝብም  ሆነ  የፋኖን  ትግል  መናቅ  ነው:: ይህ  አልበቃ  ብሎ   "ምርጫው  ከኛ  እውቅና  ውጪ  ነው  እኛ  አናውቀውም"  የሚል   የውሸት    የህፃን  ልጂ  ፕሮፓጋንዳ...

ስርነቀል ለውጥ ማምጣት የአማራ ብሄርተኝነት የህልውና ትግል ብቸኛ ግብ ነው። በ Alen Kassahun

ምስሉ ጸሃፊውን አይወክልም፡፤ ከ50 አመታት በላይ የተተከለውንና በተግባር እየተፈፀመ ያለውን አማራን ማጥፋትና ኢትዮጵያን ማፍረስ ከስሩ በመንቀል #4ኪሎን ተቆጣጥሮ ስርነቀል ለውጥ ማምጣት የአማራ ብሄርተኝነት የህልውና ትግል ብቸኛ ግብ ነው። ፋኖ በሚያደርገው የህልውና ትግል አማራ ጠልነት የወለደውን የአማራን ዘር ማጥፋት፤ ማፅዳት፤ የሰባዊ መብት ጥሰትና አገር ማፍረስ አለምአቀፍ ወንጀል ከስሩ ነቅሎ ሊቀብረው #በዋዜማው ላይ እንገኛለን። ስለሆነም ፋኖ እያደረገ ያለውን የህልውና ትግል #በድል እንዳይቋጭ  በድርድር፣ በእርቅና በምክክር ሰበብ የፋኖን ድል ለመቀልበስና ለመንጠቅ ከአሜሪካ እስከ አዲስ አበባና መቀሌ ድረስ በሚሸረብ ሴራ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ፤ በስልታዊ አማራነትም ሆነ በአማራ ጠልነት የተሰለፉ ቅጥረኞች ደፋ ቀና እያሉ እንደሚገኙ ግልፅ ነው። ፋኖ #አራት ኪሎን በመቆጣጠር ስርነቀል ለውጥ ለማወጅ በድል ዋዜማ ላይ ሆኖ እያደረገ ያለውን የመጨረሻውን ትንቅንቅ ለማሰናከልና ድሉን ለመሸጥ ተቀጥራችሁ ስለ ድርድር፣ ሽግግር፣ እርቅ፣ ውይይትና በመሳሰሉ አጀንዳዎች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ እየሰሩ የሚገኙ ቅጥረኞችን ከቀጣሪዎች እኩል ማሸነፍና ማስወገድ የህልውና ትግላችን ብቻኛ አማራጭ መሆኑ ለማንም ግልፅ ሊሆን ይገባል። ስለሆነም የዜግነት ፓለቲካ አቀንቃኝ የ3ኛ ወገን ቅጥረኞችን ከጀርባው አሰልፎ የአማራን ብሄርተኝነት የማድፈቅ አጀንዳቸውን አዝሎ ከአማራ ህልውና ትግል መሀል የተገኘው #እስክንድር ነጋ ከአማራ ህልውና ትግል ጓዙን ጠቅልሎ እንዲወጣ ማድረግ ለነገ የሚባል አይደለም። የእስክንድር ነጋ #የእየሱስ ክርስቶስነት ገፀ ባህሪ በሂደት እየተገፈፈ መምጣት አማራ ጠል ሀይሎችን ወደ እቅድ ሁለት ሴራ እንዲገቡ እያስገደደ በመሆኑ የአማራ ብሄርተኛ #እስክንድ...

አለም አቀፍ የፋኖ ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ነኝ የሚለው ቡድን ዓላማ ምንድነው ? በወንድወሰን ተክሉ

ይህ ምስል ጸሃፊውን አይወክልም! «...አማራ ለ450 ዓመታ መንፈሱ የተሰበረ ገበሮ ሕዝብ ነው..» ሀብታሙ ተገኝ (ፕ/ር) « እኔ እስክንድር  የአማራ ሕዝብ ከደረሰበት የህልውና አደጋ እኩል የሚሆን ዓላማ አለው ብዬ አላምንም» አቻምየለህ ታምሩ፤ አለም አቀፍ የፋኖ ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ነኝ የሚለው ቡድን ዓላማ ምንድነው ? በወንድወሰን ተክሉ እራሱን አለም አቀፍ የፋኖ ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ነኝ የሚለው ቡድን የዙም ውይይት ፕሮግራም ክፍል ሁለትን የተመለከተ ምልክታ:- ባለፈው  ወር ብቻ ሳይሆን ባለፈው ዓመት ዴሴምበር 2023 ( ዛሬ ጃንዋሪ 1 ቀን 2024 ነን)  እራሱን አለም አቀፍ የፋኖ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ብሎ የሚጠራው ቡድን «ጸረ አማራ ኢትዮጲያዊነት» በሚል አርእስት ስር ሀብታሙ ተገኝ (ፕ/ር) ዋና ተናጋሪ ተጋባዥ የሆነበትን  የዙም ውይይት አካሂዶ የነበረ ሲሆን የዚህ ውይይት ክፍል ሁለት  ባሳለፍነው ወር ዴሴምበር 23ቀን በማዘጋጀት አቻምየለህ ታምሩና ሀብታሙ ተገኝ (ፕ/ር) ተናጋሪ እንግዳ በማድረግ አካሂዷል። በእርግጥ  ከዚህ ከሁለተኛው የውይይት ፕሮግራም በፊት በተክሌ ይሻው በኩል የዙም ሊንክ ተልክሎኝ በሰዓት ጥበት ምክንያት መገኘት ባልችልም ዛሬ ግን በቻናላቸው ላይ የጫኑትን ይህን ክፍል ሁለት ውይይት ከተመለከትኩ በኋላ ይህን ምልክታዬን  አንባቢው ሊረዳ በሚያስችል መልኩ አንድ ሰዓት ከሰላሳ ደቂቃ የፈጀን ውይይት ይዘት በመጭመቅ እንደሚከተለው አቅርቤያለሁ። ይህ ምስል ጸሃፊውን አይወክልም! 1ኛ - ውይይቱን አዘጋጅን ማንነት በተመለከተ፦  አለም አቀፍ የፋኖ ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ባለፈው መስከረም ወር ላይ  በጌታቸው በየነ ሰብሳቢነት ተመሰረትኩ ብሎ እራሱን ያስተዋወቀ ሲ...