Skip to main content

ከኢትዮጵያ መፍረስ በኋላ የአማራ ህልውና እንዴት ይቀጥል⁉ (ለማይቀረው የአባት ሀገር አማራ ምስረታ እንዘጋጅ ‼)


በዴቭ ዳዊት

ከኢትዮጵያ መፍረስ በኋላ የአማራ ህልውና እንዴት ይቀጥል⁉

(ለማይቀረው የአባት ሀገር አማራ ምስረታ እንዘጋጅ ‼) 

/ክፍል-1/ 

=============== መግቢያ =============== 

* እኔ ዳዊት ይህንን ፅሁፍ የፃፍሁት እውነትን (no matter how it's bitter and ugly) በድፍረት መጋፈጥ ለማይፈሩ፣ ከስሜት ይልቅ ለዕውቀት የተደላደለ አዕምሮ ላላቸው፣ እንዲሁም አይቀሬ አዲስ ክስተቶችን ለመቀበል ለማይቸገሩ ይልቁንም ከ new reality  ጋር እንዴት  cope up ማድረግ እንዳለባቸው ማሰላሰል ለሚችሉ የአማራ ልጆች ነው። በመሆኑም፦ 

1. Intellectually pygmy የሆኑ፣ 

2. ከእውነት ይልቅ በቅዠት ዓለም መኖር የሚመርጡ፣ 

3. በ imperial nostalgia እየማቀቁ የሀገሪቱን pre-1991 ካርታ በየአደባባዩ ተሸክመው የሚዞሩ ግለሰቦችና ቡድኖች ይህንን ፅሁፍ እንዲያነብቡት ምኞቱም ፍላጎቱም የለኝም‼‼‼ 

=====አዝጋሚው የኢትዮጵያ መፍረስ እውን መሆን ======

* ኢትዮጵያ የመበተኗ ጉዳይ አይቀሬ ነው‼ የኢምፓየሯ መፍረስ fait accompli ከሆነ ውሎ አድሯል። የአማራ ህዝብ ሀገሪቱን በማፍረስ ረገድ አንዳችም ሚና ያልነበረውና በ Karl Jasper የ guilt መስፈርት ብንመዝነው እንኳ Criminally, Morally, Politically and Metaphysically ህዝባችንን ተጠያቂ አልያም ተፀፃች ሊያደርገው የሚችል እንጥፍጣፊ ጉዳይ አይኖርም‼ 

ይልቁንስ የአማራ ህዝብ ከዚህ በኋላ እንኳንስ በምድራዊ ኃይል ይቅርና አማልክትም እንኳ ተሰብስበው በአንዳች ተአምራዊ  panacea ቢያክሟት እንኳ ከፍርሰት ልትድን ስለማትችለው ኢትዮጵያ እርግፍ አድርጎ ትቶ የራሱን አባት ሀገር በፍጥነት ስለመመስረት ማሰብ ያለበት ትክክለኛ ወቅት ላይ እንገኛለን‼‼‼ 

ከሀገሪቱ መፍረስ እውን መሆን ውስጥ እርግጠኛ መልስ ያላገኘው ጥያቄ ቢኖር የመፍረሱ ሂደት የሚጠናቀቀው፦ 

1. In what form? እና 

2. By what time frame? የሚለው ብቻ ነው‼ 

የዚህ ፅሁፌ አላማም በተራ ቁጥር 1 ላይ በተጠቀሰው ነጥብ ዙሪያ የሚያጠነጥን ይሆናል። መልካም ንባብ! 

* ኢትዮጵያን እንደማንኛውም multiethnic and territorially integrated empire ከማየት ይልቅ በራሱ ልሂቅ ለዘመናት  "ብፅዕትና ቅድስት ከሀገራትም የተለየች ሀገር" እንደሆነች ተደርጎ ሲነገረው ለኖረ አማራዊው ህዝባችን፥ ሀገሪቱ በአይቀሬው ሞቷ አፋፍ ላይ ሆና እንኳ ይህንን እውነት ተቀብሎ ከፍርስራሹ መሐል ራሱን እንዴት ማዳን እንዳለበት፤ የራሱን ሉዓላዊ አባት ሀገር ለመመስረትም ቅድመ ዝግጅት ከማድረግ ይልቅ አስፈሪውን መፃኢ ጊዜ በድንዛዜ እጁን አጣጥፎ በመቀመጥ መጠበቁ እጅግ አስደንጋጭ ነው። 

በእርግጥ የዚህ አይነቱ collective ድንዛዜ ተራ ክስተት ሳይሆን በህዝባችን ላይ ለተራዘመ ጊዜ በተሰራበት ህፅበተ-አዕምሮ (Brain wash) ምክንያት ያፈጠጠ ስቃዩ እንዳይ'ሰማው ሆኖ ለከፍተኛ የስነልቦና ቀውስ ዳርጎታል። ይህ በህዝባችን ውስጥ  ገንግኖ ስቃይንና አደጋን አስረስቶ በማደንዘዝ ህዝባችንን ወደ ፈፅሞ መጥፋት እየነዳ የሚገኘው  የስነልቦና መቃወስ  La Belle Indifférence ("Beautiful Ignorance") ብለን ልንጠራው የምንችለው አይነት አደገኛ ድንዛዜ ነው። 

የአማራ ህዝብ በዚህ መጠን ለምን ደነዘዘ? Collectively የ  La Belle Indifférence ሰለባስ እንደምን ሆነ?  እየሞተች ካለችው ኢምፓየር ጋር አብሬ ካልጠፋሁ ብሎ የራሱን ሀገር ከመገንባት ይልቅ እጁን አጣጥፎ ለምን ተቀመጠ? ብለን ከጠየቅን መልሱ የሚሆነው የ Asymmetric Fear ሰለባ በመሆኑ ነው‼ ይህንን asymmetric fear ደግሞ more specific እናድርገው ካልንና በትክክለኛ ስሙ እንጥራው ካልን የአማራ ህዝብ እንደ ህዝብ በጋራ የ Separation Anxiety Disorder (S.A.D) ሰለባ ሆኗል‼‼‼ "ከኢትዮጵያ ተነጥዬ መኖር አልችልም፣ ኢትዮጵያ በአሁን ቅርጿና የህዝቦቿ ስብስብ ካልቀጠለች መኖር አልችልም" የሚል መሠረተ ቢስ ፍርሃት‼‼‼ 

ይህ unwarranted ፍርሃት እንዲሁ በድንገት በአንድ ሌሊት የተፈጠረ ሳይሆን፥ ከላይ ለመግለፅ እንደሞከርሁት፥ ለዘመናት በዋናነት በራሱና በሌሎች ልሂቃን ስለ ኢትዮጵያና ስለራሱ ሲነገረው በኖረ የመሰሪዎች ተረት ምክንያት ነው። ከእነዚህ የማደንዘዣ ተረቶች መካከልም የተወሰኑትን አንስቶ ማለፍ ከዚህ unwarranted fear bondage ለመላቀቅ በጥቂቱም ቢሆን ይረዳል የሚል እምነት አለኝ። 

1. "The White man's Burden" Analogy፦ የአማራን ህዝብ የስልጣን ወንበሩ ማስጠበቂያ ማድረግ የሚፈልግ ገዢ አምባገነንና በኪነጥበብ ስም የሚገለሙት አዝማሪ ሁሉ ህዝባችንን ሲሸነግለው የኖረው "አማራ የኢትዮጵያ ጠባቂ ነው፣ አማራ ከኢትዮጵያዊነት እንዴት ይወርዳል? ፣ አማራ እየተገደለም ቢሆን ከኢትዮጵያዊነት አይወርድም፣ ሀገር ማቅናት በአማራ ትከሻ ላይ ነው የወደቀው፣..........." ወዘተ በሚል ድሪቶ ተረት ተረት ነው። ተላላው ህዝባችንም ይህንን የብልጣብልጦች ተረት አምኖ 82 ብሔር በሚኖርባትና አማራ በማንነቱ ምክንያት የሚሳደድባትን ሀገር "ዋልታና ማገሯ እኔ ነኝ" ብሎ አምኖ ኖሯል። በመሆኑም በአናቱ ላይ ሀገሪቱ እየፈረሰች እያየ እንኳ ተፈጥሯዊ የሆነ ራስን የማዳንና ትውልድን የማስቀጠል እንዲሁም ማረፊያ አባት ሀገር የመመስረቱን ጉዳይ ለዘመናት ሲሰበክ ከኖረው ተረት ጋር እያመሳከረ ትልቅ ወንጀል የፈፀመ አልያም ይህንን ማሰብ በራሱ እንደ grand dereliction በመቁጠር በፍርሃት ቆፈን ተይዞ ሀገር አልባና "የአፍሪካው ጂፕሲ" ለመባል እያጣጣረ ይገኛል። 

የእኛ የአማራ ብሔርተኞች የመጀመሪያ ተልዕኳችንም ይህንን ተረት ተረት ከአማራ ህዝብ ልብና አዕምሮ ፍቆ በማስወገድ መሰሪ ገዢዎችና በኪነጥበብ ስም የሚገለሙቱ አዝማሪዎች በህዝባችን አዕምሮ ውስጥ የሳሏትን ጣዖቷን ኢምፓየር ከእሳቤው ውስጥ ሰባብረን በመጣልና ከፍርሃቱ ነፃ በማውጣት ከእውነታው ጋር በፍጥነት ታርቆ ታሪካዊ ርስቱንና ወሰኑን በማስከበር ሉዓላዊ አማራዊ አባት ሀገሩን እንዲመሠርት ማድረግ ነው‼‼‼

2. "The Chosen People" Analogy፦ 

====== ክፍል ሁለት ይቀጥላል======

* የጠራ ራዕያችን ፥ ሉዓላዊው አባት ሀገር አማራ ተመስርቶ ከጄኖሳይድ የተረፈው ህዝባችን በነፃነት ሲኖር ማየት ነው‼‼‼

ፈጣሪ የአማራን ህዝብ አብዝቶ ይባርክ‼‼‼

ዴቭ ዳዊት።

Comments

Popular posts from this blog

"ከአሁን በሆላ ፋኖ ወደ አንድነት መምጣት አለባቸው የሚባለው አካሄድ አይሰራም" :: በወዳጄ/ቤተ አማራ ወሎ

ከአሁን  በሆላ  ፋኖ  ወደ  አንድነት    መምጣት  አለባቸው  የሚባለው  አካሄድ  አይሰራም::  ክህደት   ከተፈፀመ  በሆላ  አንዱ  ቡድን  ከሌላው  ስር  ሆኖ  ይቀጥላል  ማለት  የማይቻል   ነው::  ምክኒያቱም 1ኛ:- 27  ቀን  ቁጪ  ብለው   መክረዋል :: እያንዳንዱ  አደረጃጄት  ሰነድ  ፅፈው  አቅርበዋል::  በቀረበው  ሰነድ  ላይ  ከፍተኛ  ውይይት  ተደርጎበት  የሚወድቀው  ወድቆ  የሚፈለገው  ፀድቋል::ቃለ  መሀላ  ፈፅመው   ወደ  ምርጫ   ለመግባት  ተስማምተዋል:: እጃቸውን  አውጥተው   ከመረጡ  በሆላ    ግን    "ጨዋታ  ፈረሰ  ዳቦ  ተቆረሰ"   የሚል  የህፃን  ልጂ  ጨዋታ  ውስጥ  መግባት   የአማራን  ህዝብም  ሆነ  የፋኖን  ትግል  መናቅ  ነው:: ይህ  አልበቃ  ብሎ   "ምርጫው  ከኛ  እውቅና  ውጪ  ነው  እኛ  አናውቀውም"  የሚል   የውሸት    የህፃን  ልጂ  ፕሮፓጋንዳ...

ስርነቀል ለውጥ ማምጣት የአማራ ብሄርተኝነት የህልውና ትግል ብቸኛ ግብ ነው። በ Alen Kassahun

ምስሉ ጸሃፊውን አይወክልም፡፤ ከ50 አመታት በላይ የተተከለውንና በተግባር እየተፈፀመ ያለውን አማራን ማጥፋትና ኢትዮጵያን ማፍረስ ከስሩ በመንቀል #4ኪሎን ተቆጣጥሮ ስርነቀል ለውጥ ማምጣት የአማራ ብሄርተኝነት የህልውና ትግል ብቸኛ ግብ ነው። ፋኖ በሚያደርገው የህልውና ትግል አማራ ጠልነት የወለደውን የአማራን ዘር ማጥፋት፤ ማፅዳት፤ የሰባዊ መብት ጥሰትና አገር ማፍረስ አለምአቀፍ ወንጀል ከስሩ ነቅሎ ሊቀብረው #በዋዜማው ላይ እንገኛለን። ስለሆነም ፋኖ እያደረገ ያለውን የህልውና ትግል #በድል እንዳይቋጭ  በድርድር፣ በእርቅና በምክክር ሰበብ የፋኖን ድል ለመቀልበስና ለመንጠቅ ከአሜሪካ እስከ አዲስ አበባና መቀሌ ድረስ በሚሸረብ ሴራ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ፤ በስልታዊ አማራነትም ሆነ በአማራ ጠልነት የተሰለፉ ቅጥረኞች ደፋ ቀና እያሉ እንደሚገኙ ግልፅ ነው። ፋኖ #አራት ኪሎን በመቆጣጠር ስርነቀል ለውጥ ለማወጅ በድል ዋዜማ ላይ ሆኖ እያደረገ ያለውን የመጨረሻውን ትንቅንቅ ለማሰናከልና ድሉን ለመሸጥ ተቀጥራችሁ ስለ ድርድር፣ ሽግግር፣ እርቅ፣ ውይይትና በመሳሰሉ አጀንዳዎች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ እየሰሩ የሚገኙ ቅጥረኞችን ከቀጣሪዎች እኩል ማሸነፍና ማስወገድ የህልውና ትግላችን ብቻኛ አማራጭ መሆኑ ለማንም ግልፅ ሊሆን ይገባል። ስለሆነም የዜግነት ፓለቲካ አቀንቃኝ የ3ኛ ወገን ቅጥረኞችን ከጀርባው አሰልፎ የአማራን ብሄርተኝነት የማድፈቅ አጀንዳቸውን አዝሎ ከአማራ ህልውና ትግል መሀል የተገኘው #እስክንድር ነጋ ከአማራ ህልውና ትግል ጓዙን ጠቅልሎ እንዲወጣ ማድረግ ለነገ የሚባል አይደለም። የእስክንድር ነጋ #የእየሱስ ክርስቶስነት ገፀ ባህሪ በሂደት እየተገፈፈ መምጣት አማራ ጠል ሀይሎችን ወደ እቅድ ሁለት ሴራ እንዲገቡ እያስገደደ በመሆኑ የአማራ ብሄርተኛ #እስክንድ...

አለም አቀፍ የፋኖ ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ነኝ የሚለው ቡድን ዓላማ ምንድነው ? በወንድወሰን ተክሉ

ይህ ምስል ጸሃፊውን አይወክልም! «...አማራ ለ450 ዓመታ መንፈሱ የተሰበረ ገበሮ ሕዝብ ነው..» ሀብታሙ ተገኝ (ፕ/ር) « እኔ እስክንድር  የአማራ ሕዝብ ከደረሰበት የህልውና አደጋ እኩል የሚሆን ዓላማ አለው ብዬ አላምንም» አቻምየለህ ታምሩ፤ አለም አቀፍ የፋኖ ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ነኝ የሚለው ቡድን ዓላማ ምንድነው ? በወንድወሰን ተክሉ እራሱን አለም አቀፍ የፋኖ ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ነኝ የሚለው ቡድን የዙም ውይይት ፕሮግራም ክፍል ሁለትን የተመለከተ ምልክታ:- ባለፈው  ወር ብቻ ሳይሆን ባለፈው ዓመት ዴሴምበር 2023 ( ዛሬ ጃንዋሪ 1 ቀን 2024 ነን)  እራሱን አለም አቀፍ የፋኖ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ብሎ የሚጠራው ቡድን «ጸረ አማራ ኢትዮጲያዊነት» በሚል አርእስት ስር ሀብታሙ ተገኝ (ፕ/ር) ዋና ተናጋሪ ተጋባዥ የሆነበትን  የዙም ውይይት አካሂዶ የነበረ ሲሆን የዚህ ውይይት ክፍል ሁለት  ባሳለፍነው ወር ዴሴምበር 23ቀን በማዘጋጀት አቻምየለህ ታምሩና ሀብታሙ ተገኝ (ፕ/ር) ተናጋሪ እንግዳ በማድረግ አካሂዷል። በእርግጥ  ከዚህ ከሁለተኛው የውይይት ፕሮግራም በፊት በተክሌ ይሻው በኩል የዙም ሊንክ ተልክሎኝ በሰዓት ጥበት ምክንያት መገኘት ባልችልም ዛሬ ግን በቻናላቸው ላይ የጫኑትን ይህን ክፍል ሁለት ውይይት ከተመለከትኩ በኋላ ይህን ምልክታዬን  አንባቢው ሊረዳ በሚያስችል መልኩ አንድ ሰዓት ከሰላሳ ደቂቃ የፈጀን ውይይት ይዘት በመጭመቅ እንደሚከተለው አቅርቤያለሁ። ይህ ምስል ጸሃፊውን አይወክልም! 1ኛ - ውይይቱን አዘጋጅን ማንነት በተመለከተ፦  አለም አቀፍ የፋኖ ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ባለፈው መስከረም ወር ላይ  በጌታቸው በየነ ሰብሳቢነት ተመሰረትኩ ብሎ እራሱን ያስተዋወቀ ሲ...