Skip to main content

"SNAP ASSESSMENT ON STRATEGIC-SURPRISE" በዴቭ ዳዊት

ዴቭ ዳዊት ስለ SNAP ASSESSMENT ON STRATEGIC-SURPRISE እንዲህ ሲል ይዘረዝረዋል" ህዝብና ፖለቲካ እስከወዲኛው ከመሠረቱ የሚንዱና ህዝባችንን ከፍተኛ ዋጋ ሊያስከፍሉ የሚችሉ አደጋዎችን በተመለከተ የቀረበ የግል ግምገማ

ክፍል-አንድ 

አንድ አደጋ፥ "Strategic Surprise" ተብሎ ሊገለፅ የሚችለው ተጠባቂ ከመሆን ወይም አለመሆኑ ጋር  በተያያዘ ብቻ ሳይሆን አደጋው ከመከሰቱ በፊት ተጋላጭነትን መርምሮ በቂ ዝግጅት ካለማድረግ ጋር የተያያዘ መሆኑ፤ እንዲሁም የአደጋው መከሰት የሚያስከፍለው ዋጋ (Regrettable outcomes) እጅግ ከፍተኛ መሆኑ ነው። በመሆኑም በእኔ አጭር የግል ግምገማ ከአማራ ህዝብ ጠላቶች ሊወሰድ ከጫፍ በደረሰ የፖለቲካና የኃይል እርምጃ ምክንያት የአማራ ህዝብ ከመቼውም ጊዜ በከፋ ሁኔታ ለ Strategic-surprise ተጋልጧል የሚል እምነት አለኝ። 

እነዚህን ከ Political and Security domain የሚቀዱ አደጋዎች ከወዲሁ በቁመናቸው ልክ አጢኖ በቂ ዝግጅት ማድረግ ካልተቻለ ደግሞ፥ አደጋዎቹ የሚያስከትሉት Potential-Regrets እጅግ ሲበዛ ከባድ ነው። 

ዝርዝር ስትራቴጂካዊ አደጋዎች 

1. የመጀመሪያው ከ Political domain የሚመነጭ Strategic-Surprise ሲሆንየአማራ adversaries ከሚያደርጉት አሰላለፍ የሚቀዳ አደጋ፥ ማለትም፦ ኦህዴድ-መሩ የኦሮሞ ልሂቃንና የወያኔ Offstage Deal and Political Collusion ሲሆን፣ 

2. ሁለተኛው ደግሞ ከ Security domain የሚመነጭ Strategic-Surprise ሲሆን፥ የአማራን ህዝብ ለዳግም ወረራ የመዳረግ እምቅ አቅም ያዘለውና በዋናነትም በተፈጠረለት ምቹ ሁኔታ እየፈረጠመ የመጣው የፋሽስት ወያኔ Kinetic Capability ነው። 

*  እነዚህን ከላይ የተቀመጡ ሁለት ነጥቦች በቅደም ተከተል እያነሳን በዝርዝር እንመልከት። 

1. ኦህዴድ-መሩ የኦሮሞ ልሂቃንና የወያኔ Offstage Deal and Political Collusion 

* ፋሽስት ወያኔ የማዕከላዊ መንግሥቱ አዛዥ-ናዛዥ በነበረበት ወቅት፥ የወንበሩ ማስጠበቂያ አድርጎ ያቀርበው የነበረው ትርክት በሄግልያን-ተቃርኖ ላይ የተመሠረተ ነበር። "በቀኝ በኩል ትምክህተኛው አማራ፥ በግራ በኩል ጠባቡ ኦሮሞ አለ፤ በመሐል አስታራቂነት እኔ አለሁ" የሚል መሠሪነትን ከዕቡይነት ያስተዋደደ ትርክቱን ከሀገር ቤት አልፎ ለውጭ መንግስታት ሳይቀር የሀገሪቱ የህልውና እስትንፋስ እሱና እሱ ብቻ የሆነ አስመስሎ ያቀርብ ነበር። ተረኛው ኦህዴድ ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ በተለይም ከጦርነቱ ማግስት ጀምሮ ኦህዴድ የአማራ ተወካይ ነን የሚሉ የፖለቲካ ኃይሎችን ሽባ ያደረገው ፥ ፍርሃት በመቀስቀስ / "argumentum ad metum" የሚባል fallacious argument በመጠቀም/ ነው። ይህም ማለት፥ አብይ አህመድ የብአዴን ሰዎችን ሰብስቦ "አማራ ተበደለ የሚሉ ሰዎችን አስቁሙ! ወያኔ ኦሮሞን ምንም ሊያደርገው አይችልም፤ አማራን ነበር ሊያጠፋ የነበረው፤ አርፋችሁ ተቀመጡ" ነበር ያለው። "ወያኔ ኦሮሞን ምንም አያደርግም" የሚለውን ለጊዜው እናቆየውና፥ ወያኔ ዕድልና አጋጣሚውን ባገኘ ጊዜ ሁሉ አማራን ለማጥፋት እንደሚሰራ መቼም ቢሆን የማንዘነጋውና የማንዘናጋበት ጉዳይ ነው። ነገር ግን፥ እነአብይ አህመድ የአማራን ህዝብ በወያኔ እያስፈራሩ፥ ለኦህዴድ ፈቃድና ፍላጎት ተንበርካኪ እንዲሆን የሄዱበት ርቀትና አማራን እንወክላለን የሚሉ ኃይሎች ይህንን ተቀብለው ጭፍን ተንበርካኪ ሆነው ህዝባችንን አሳልፈው የሸጡበት መንገድ ትልቅ አደጋ ይዞ መጥቷል። 


አማራ በራሱ ከመቆም ይልቅ ለኦህዴድ እንዲንበረከክ ከተደረገ በኋላ፥ ቁማርተኛው ኦህዴድ ከወያኔ ጋር የመጋረጃ ጀርባ ድርድር ወደ ማድረጉ ነው የገባው። የአማራ ግዛቶች ከወራሪው ፋሽስት ወያኔ ነፃ ባልወጡበት ሁኔታ፥ ዘማቹ ኃይል "ባለህበት ቁም" ሲባልና ያንን ተከትሎ የነበረውን stalemate በእርግጠኝነት ተንትኖ ለማቅረብ በአማራ ስም ከተደራጁት ኃይሎች ውስጥ አንዳቸውም አቅሙም እርግጠኛነቱም አልነበራቸውም፣ አሁንም የላቸውም። 

ኦህዴድ በድንገት ተነስቶ ዘማቹን ኃይል "ባለህበት ቁም" ያለውና እንደዚህ አይነት stalemate በአማራ አናት ላይ እንዲፈጠር ያደረገው በወያኔ ላይ የ isolation አቋም ለመያዝ ነው? ያ ከሆነስ የአማራ ርስቶች በወረራ ስር ባሉበት ሁኔታ ነው ወይ ወያኔን isolate አደርገዋለሁ  የሚባለው? ወይስ ውጥረት የማለዘብ (détente) አቋም ነው? ወይስ አማራና ትግሬ እርስበርሱ እንዲጠባበቅ የማድረግ የ Containment ስራ ነው? ወይስ አማራን በአደባባይ በማዘናጋት ኦህዴድ Offstage ከወያኔ ጋር የሚደራደርበት ስልት ነው? ብሎ የጠየቀ አንዳችም በአማራ ስም ተደራጀሁ የሚል ኃይል አልነበረም። እውነታው ግን ኦህዴድ አማራን "እምቢ ካልህ ወያኔ ይመጣብሃል" በሚል የስጋት ቆፈን ውስጥ ከትቶ የፖለቲካ willኡን ከሰበረ በኋላ፥ ከፖለቲካ ድርጅቶችም በላይ በትግሬና በኦህዴድ-መሩ የኦሮሞ ልሂቃን ደረጃ ወደ offstage deal and political collusion ውስጥ ነው የገቡት። ማንን የጦስ ዶሮ በማድረግና በማን ኪሣራ ላይ በመረማመድ እየተደረገ እንደሆነ ደግሞ ሲበዛ ግልጽ ነው‼ አማራን ያገለለ፣ በአማራ ጥቅም ላይ የሚረማመድ እንዲሁም በዋናነት አማራን ጥግ በማስያዝና አማራን የውድመትና ጥፋቱ ሞተር አድርጎ ራስን ነፃ በማውጣት ላይ ያነጣጠረ deal and collusion ነው እየተካሄደ ያለው‼ 

ይህ በኦህዴድና በወያኔ መካከል እየተደረ ያለው አማራን ያገለለ offstage deal and political collusion "ከመጋረጃ ጀርባ" የሚለውን phase ጨርሶ ከቅርፊቱ ለመውጣት በእነ አትሌት ደራርቱ ቱሉ በኩል በሰብዓዊነት ሽፋን በገርደምዳሜ በተነገረ በሁለት ቀናት ውስጥ፥ ኦህዴድ-መሩ የኦሮሙማው መንግስት "ለሰብዓዊነት" በሚል ሽፋን ላልተወሰነ ጊዜ ተኩስ አቆምሁ የሚል አዋጅ ሲያስነግር፥ ፋሽስት ወያኔም ተመሳሳይ truce agreement ላይ መድረሱን ይፋ አድርጓል። 

ይህ ሁሉ የሚነግረን ነገር ቢኖር የሁለቱ ኃይሎች አማራን ያገለለ offstage deal and political collusion በአማራ ህዝብና መሠረታዊ ጥቅም ላይ ያንዣበበ Strategic-Surprise እውን እየሆነ መምጣቱን ነው‼‼ 

በእኔ የግል ግምገማ መሠረት፥ ይህንን political strategic-surprise ለመቀልበስና ህዝባችንን ከአስከፊ Potential-Regrets ለመታደግ፥ ቁርጠኝነቱ ካለ ዛሬም ዕድሉ ሙሉ በሙሉ አልተዘጋም‼‼

1.2. የመፍትሔ ሃሳብ

/ Recommendation to avoid strategic-surprise in the Political domain/ 

* የአማራ ፖለቲካ መሠረታዊ ችግሩ ውስጣዊ ደዌው ነው። የአማራ ጠላቶች የሚበረቱብንም ከውጭ ወደ ውስጥ ይዘውብን በሚመጡት ታክቲክና ስትራቴጂ ሳይሆን፥ በአማራ polity ውስጥ ያለውን weak link exploit በማድረግ ነው። አማራን ለኦህዴድ ፈቃድ አንበርክኮ፥ ከአማራ ጀርባ በአማራ ህዝብ ጥቅም ላይ እንዲረማመድና ከወያኔ ጋር እንዲዶልት ያደረገው፥ አማራን እንወክላለን የሚሉ ኃይሎች በአመዛኙ፦ 

- አንድ ላይ መቆም የማይችሉ ጠባብ-ጎጠኞች፣

- ግለኛ ሆድ-አደሮች፣ 

- በአማራነት ራሳቸውን ችለው መቆም የማይችሉ ልምሹዎች (ክልሉ በዚህ አራት አመት ውስጥ በአብይ ያልተቀባ ርዕሰ-መስተዳድር ሹሞ የማያውቅ ሲሆን ድርጅታዊ ጉባኤ ሲያደርጉ፣ ብአዴን በስብሰባው መቋጫ አብይ የግድ የሚገኝ ሲሆን አብንም በተላላኪዎቹ ሹመኞች የግል ጠባቂና የመንግስት የሚዲያ እጀባና ፕሮፓጋንዳ ካልሆነ በቀር እርስበርስ ተደማምጦና ተከባብሮ፣ ከምንም በላይ ደግሞ ህዝብን አክብሮና ለህዝብ ጥቅሞች ቅድሚያ ሰጥቶ በራስ የመቆሙ ነገር ጨርሶ ከማይታሰብበት ደረጃ ደርሷል።) 

- የባንዳነት ፉክክርን መገለጫቸው ያደረጉ አድርባዮች፣ 

- በግል ጥቅም፣ ሹመትና የስልጣን ጥም የታወሩ ሰቀቀናሞች፣ 

- በሌብነትና እርስበርስ በማይተማመኑ አረመኔዎች የተሞሉ ናቸው። 

* ቢያንስ እየመጣ ያለውን አደጋ እጅግ አሳሳቢነት ከግምት በማስገባት ይህንን ደዌና ነቀርሳቸውን ወደጎን አድርገው፥ የአማራን ፖለቲካ ከኦህዴድ ጫማ ስር ለማውጣት፣ ለግል ጥቅማቸው ሲሉ በጎጥ ክፍፍል ሲመርዙት የሚውሉትን ህዝብ አንድነቱን በማስጠበቅ እንደህዝብ "የማልደራደርባቸው ቀይ መስመሮቼ" የሚል አመለካከትና አቋም በፍጥነት እንዲይዝ ማድረግ ካልቻሉ በቀር፥ በዚህ ፍጥነት ሌላ አማራጭ መፍትሔ ሊወለድ አይችልም። 

ይህንን በተግባር ይፈፅማሉ ወይ የሚለው ከጥርጣሬም በዘለለ በእርግጠኝነት ተግባራዊ አያደርጉትም ቢባል ለእውነቱ ይቀርባል። ለዚህ መነሻ የሆነኝ፥ እንደህዝብ የጋራ ህልውናችን አደጋ ውስጥ ወድቆ እንኳ ወገባቸውን ታጥቀው የሚጠመዱበት ተግባር ወይ በጎጠኝነትና አድመኝነት ተቧድነው እርስበርስ መበላላት ላይ ነው አልያም "እግዚኦ" በሚያስብል የዘረፋ ስምሪት ላይ ነው። 

አማራን እንወክላለን የሚሉ ኃይሎችና የአማራ ፖለቲካ ፥ ራስን ከመብላት የ Autosacrophagy ደዌ በፍጥነት መፈወስ ካልቻሉና ህዝቡን በአንድ ላይ አንቀሳቅሶ ህዝብ የማይደራደርባቸው ትላልቅ ቀይ መስመሮችን ማስመር ካልቻሉ፣ እንዲሁም "አብይ መሲህአችን ነው" ከሚል የምንፍቅና አመለካከትና ፖለቲካውን ከኦህዴድ ጫማ ስርና ከተንጠልጣይነት ነፃ ካላወጡት በቀር፥ ነገ አይናችን እያየ ልክ እነ ስብሐት ነጋ እንደተፈቱት፣ ወያኔን "ከሃዲው ጁንታ" ከሚል ስያሜ ወደ "የትግራይ አማፂያን" ወደሚል ስያሜ ሲቀይሩት እንዳየነው ሁሉ፥ ቀሪ የወያኔና የኦህዴድ የጋራ ፍላጎት በአማራ ህዝብ ኪሳራ በጫንቃው ላይ መጫናቸው አይቀሬ ነው"‼‼‼

ይቀጥላል



Comments

Popular posts from this blog

"ከአሁን በሆላ ፋኖ ወደ አንድነት መምጣት አለባቸው የሚባለው አካሄድ አይሰራም" :: በወዳጄ/ቤተ አማራ ወሎ

ከአሁን  በሆላ  ፋኖ  ወደ  አንድነት    መምጣት  አለባቸው  የሚባለው  አካሄድ  አይሰራም::  ክህደት   ከተፈፀመ  በሆላ  አንዱ  ቡድን  ከሌላው  ስር  ሆኖ  ይቀጥላል  ማለት  የማይቻል   ነው::  ምክኒያቱም 1ኛ:- 27  ቀን  ቁጪ  ብለው   መክረዋል :: እያንዳንዱ  አደረጃጄት  ሰነድ  ፅፈው  አቅርበዋል::  በቀረበው  ሰነድ  ላይ  ከፍተኛ  ውይይት  ተደርጎበት  የሚወድቀው  ወድቆ  የሚፈለገው  ፀድቋል::ቃለ  መሀላ  ፈፅመው   ወደ  ምርጫ   ለመግባት  ተስማምተዋል:: እጃቸውን  አውጥተው   ከመረጡ  በሆላ    ግን    "ጨዋታ  ፈረሰ  ዳቦ  ተቆረሰ"   የሚል  የህፃን  ልጂ  ጨዋታ  ውስጥ  መግባት   የአማራን  ህዝብም  ሆነ  የፋኖን  ትግል  መናቅ  ነው:: ይህ  አልበቃ  ብሎ   "ምርጫው  ከኛ  እውቅና  ውጪ  ነው  እኛ  አናውቀውም"  የሚል   የውሸት    የህፃን  ልጂ  ፕሮፓጋንዳ...

ስርነቀል ለውጥ ማምጣት የአማራ ብሄርተኝነት የህልውና ትግል ብቸኛ ግብ ነው። በ Alen Kassahun

ምስሉ ጸሃፊውን አይወክልም፡፤ ከ50 አመታት በላይ የተተከለውንና በተግባር እየተፈፀመ ያለውን አማራን ማጥፋትና ኢትዮጵያን ማፍረስ ከስሩ በመንቀል #4ኪሎን ተቆጣጥሮ ስርነቀል ለውጥ ማምጣት የአማራ ብሄርተኝነት የህልውና ትግል ብቸኛ ግብ ነው። ፋኖ በሚያደርገው የህልውና ትግል አማራ ጠልነት የወለደውን የአማራን ዘር ማጥፋት፤ ማፅዳት፤ የሰባዊ መብት ጥሰትና አገር ማፍረስ አለምአቀፍ ወንጀል ከስሩ ነቅሎ ሊቀብረው #በዋዜማው ላይ እንገኛለን። ስለሆነም ፋኖ እያደረገ ያለውን የህልውና ትግል #በድል እንዳይቋጭ  በድርድር፣ በእርቅና በምክክር ሰበብ የፋኖን ድል ለመቀልበስና ለመንጠቅ ከአሜሪካ እስከ አዲስ አበባና መቀሌ ድረስ በሚሸረብ ሴራ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ፤ በስልታዊ አማራነትም ሆነ በአማራ ጠልነት የተሰለፉ ቅጥረኞች ደፋ ቀና እያሉ እንደሚገኙ ግልፅ ነው። ፋኖ #አራት ኪሎን በመቆጣጠር ስርነቀል ለውጥ ለማወጅ በድል ዋዜማ ላይ ሆኖ እያደረገ ያለውን የመጨረሻውን ትንቅንቅ ለማሰናከልና ድሉን ለመሸጥ ተቀጥራችሁ ስለ ድርድር፣ ሽግግር፣ እርቅ፣ ውይይትና በመሳሰሉ አጀንዳዎች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ እየሰሩ የሚገኙ ቅጥረኞችን ከቀጣሪዎች እኩል ማሸነፍና ማስወገድ የህልውና ትግላችን ብቻኛ አማራጭ መሆኑ ለማንም ግልፅ ሊሆን ይገባል። ስለሆነም የዜግነት ፓለቲካ አቀንቃኝ የ3ኛ ወገን ቅጥረኞችን ከጀርባው አሰልፎ የአማራን ብሄርተኝነት የማድፈቅ አጀንዳቸውን አዝሎ ከአማራ ህልውና ትግል መሀል የተገኘው #እስክንድር ነጋ ከአማራ ህልውና ትግል ጓዙን ጠቅልሎ እንዲወጣ ማድረግ ለነገ የሚባል አይደለም። የእስክንድር ነጋ #የእየሱስ ክርስቶስነት ገፀ ባህሪ በሂደት እየተገፈፈ መምጣት አማራ ጠል ሀይሎችን ወደ እቅድ ሁለት ሴራ እንዲገቡ እያስገደደ በመሆኑ የአማራ ብሄርተኛ #እስክንድ...

አለም አቀፍ የፋኖ ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ነኝ የሚለው ቡድን ዓላማ ምንድነው ? በወንድወሰን ተክሉ

ይህ ምስል ጸሃፊውን አይወክልም! «...አማራ ለ450 ዓመታ መንፈሱ የተሰበረ ገበሮ ሕዝብ ነው..» ሀብታሙ ተገኝ (ፕ/ር) « እኔ እስክንድር  የአማራ ሕዝብ ከደረሰበት የህልውና አደጋ እኩል የሚሆን ዓላማ አለው ብዬ አላምንም» አቻምየለህ ታምሩ፤ አለም አቀፍ የፋኖ ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ነኝ የሚለው ቡድን ዓላማ ምንድነው ? በወንድወሰን ተክሉ እራሱን አለም አቀፍ የፋኖ ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ነኝ የሚለው ቡድን የዙም ውይይት ፕሮግራም ክፍል ሁለትን የተመለከተ ምልክታ:- ባለፈው  ወር ብቻ ሳይሆን ባለፈው ዓመት ዴሴምበር 2023 ( ዛሬ ጃንዋሪ 1 ቀን 2024 ነን)  እራሱን አለም አቀፍ የፋኖ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ብሎ የሚጠራው ቡድን «ጸረ አማራ ኢትዮጲያዊነት» በሚል አርእስት ስር ሀብታሙ ተገኝ (ፕ/ር) ዋና ተናጋሪ ተጋባዥ የሆነበትን  የዙም ውይይት አካሂዶ የነበረ ሲሆን የዚህ ውይይት ክፍል ሁለት  ባሳለፍነው ወር ዴሴምበር 23ቀን በማዘጋጀት አቻምየለህ ታምሩና ሀብታሙ ተገኝ (ፕ/ር) ተናጋሪ እንግዳ በማድረግ አካሂዷል። በእርግጥ  ከዚህ ከሁለተኛው የውይይት ፕሮግራም በፊት በተክሌ ይሻው በኩል የዙም ሊንክ ተልክሎኝ በሰዓት ጥበት ምክንያት መገኘት ባልችልም ዛሬ ግን በቻናላቸው ላይ የጫኑትን ይህን ክፍል ሁለት ውይይት ከተመለከትኩ በኋላ ይህን ምልክታዬን  አንባቢው ሊረዳ በሚያስችል መልኩ አንድ ሰዓት ከሰላሳ ደቂቃ የፈጀን ውይይት ይዘት በመጭመቅ እንደሚከተለው አቅርቤያለሁ። ይህ ምስል ጸሃፊውን አይወክልም! 1ኛ - ውይይቱን አዘጋጅን ማንነት በተመለከተ፦  አለም አቀፍ የፋኖ ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ባለፈው መስከረም ወር ላይ  በጌታቸው በየነ ሰብሳቢነት ተመሰረትኩ ብሎ እራሱን ያስተዋወቀ ሲ...