የአማራ እና የአፋር ሕዝብ በጨካኝ ቡድኖች ታይቶና ተሰምቶ በማይታወቅ መልኩ መጠነ ሰፊ ውርጅብኝ እየወረደበትና በግልጽ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየተፈጸመበት ይገኛል ። ለሕዝባችን የሚጮህለት ኃይል የለም። የሕዝባችን በደል የሚገደው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅትም አልተገኘም ። በአጭሩ ለአማራ ሕዝብ ከራሱ ውጪ ማንም እንደማይጮህለት በሚገባ ተረጋግጧል። ስለዚህ በሚቀጥለው ሃሙስ በዋሽንግተን ዲሲ በሚደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ተገኝተው ሰብአዊነትዎን እና ወገናይነትዎን ለአማራና ለአፋር ህዝብ ድምጽ ይሆናሉ ወይስ የተፈጸመባቸውን በደል እያሰቡ ብቻዎትን በቤትዎ ተቀምጠው ያዝናሉ?
ከአሁን በሆላ ፋኖ ወደ አንድነት መምጣት አለባቸው የሚባለው አካሄድ አይሰራም:: ክህደት ከተፈፀመ በሆላ አንዱ ቡድን ከሌላው ስር ሆኖ ይቀጥላል ማለት የማይቻል ነው:: ምክኒያቱም 1ኛ:- 27 ቀን ቁጪ ብለው መክረዋል :: እያንዳንዱ አደረጃጄት ሰነድ ፅፈው አቅርበዋል:: በቀረበው ሰነድ ላይ ከፍተኛ ውይይት ተደርጎበት የሚወድቀው ወድቆ የሚፈለገው ፀድቋል::ቃለ መሀላ ፈፅመው ወደ ምርጫ ለመግባት ተስማምተዋል:: እጃቸውን አውጥተው ከመረጡ በሆላ ግን "ጨዋታ ፈረሰ ዳቦ ተቆረሰ" የሚል የህፃን ልጂ ጨዋታ ውስጥ መግባት የአማራን ህዝብም ሆነ የፋኖን ትግል መናቅ ነው:: ይህ አልበቃ ብሎ "ምርጫው ከኛ እውቅና ውጪ ነው እኛ አናውቀውም" የሚል የውሸት የህፃን ልጂ ፕሮፓጋንዳ...
Comments