Skip to main content

Posts

Showing posts from July, 2024

"ከአሁን በሆላ ፋኖ ወደ አንድነት መምጣት አለባቸው የሚባለው አካሄድ አይሰራም" :: በወዳጄ/ቤተ አማራ ወሎ

ከአሁን  በሆላ  ፋኖ  ወደ  አንድነት    መምጣት  አለባቸው  የሚባለው  አካሄድ  አይሰራም::  ክህደት   ከተፈፀመ  በሆላ  አንዱ  ቡድን  ከሌላው  ስር  ሆኖ  ይቀጥላል  ማለት  የማይቻል   ነው::  ምክኒያቱም 1ኛ:- 27  ቀን  ቁጪ  ብለው   መክረዋል :: እያንዳንዱ  አደረጃጄት  ሰነድ  ፅፈው  አቅርበዋል::  በቀረበው  ሰነድ  ላይ  ከፍተኛ  ውይይት  ተደርጎበት  የሚወድቀው  ወድቆ  የሚፈለገው  ፀድቋል::ቃለ  መሀላ  ፈፅመው   ወደ  ምርጫ   ለመግባት  ተስማምተዋል:: እጃቸውን  አውጥተው   ከመረጡ  በሆላ    ግን    "ጨዋታ  ፈረሰ  ዳቦ  ተቆረሰ"   የሚል  የህፃን  ልጂ  ጨዋታ  ውስጥ  መግባት   የአማራን  ህዝብም  ሆነ  የፋኖን  ትግል  መናቅ  ነው:: ይህ  አልበቃ  ብሎ   "ምርጫው  ከኛ  እውቅና  ውጪ  ነው  እኛ  አናውቀውም"  የሚል   የውሸት    የህፃን  ልጂ  ፕሮፓጋንዳ...

የማንቂያ ድዎል‼️ በ Alen Kassahun

የአማራ ህልውና ከመጥፋት ድኖ ዘላለማዊነቱ የሚረጋገጠው፤ ሌሎች ኢትዮጵያውያን ነገዶች ተጨፍጭፈው ከመጨፍለቅና ከመጥፋት የሚድኑት እና ኢትዮጵያ ከመፍረስና መበታተን ድና ታላቋ ትግራይና ታላቋ ኦሮሚያ በአማራ #መቃብር በኢትዮጵያውያን አፅመርስት ላይ መወለድ ቅዠት የሚሆኑት #ፋኖ አራት ኪሎን በቀጥታ በአሸናፊነት ተቆጣጥሮ  #ስርነቀል ለውጥ በኢትዮጵያ ምድር ሲያውጅ ብቻና ብቻ ነው። ፋኖ በአሸናፊነት 4ኪሎን በመቆጣጠር ስርነቀል ለውጥ ከማወጅ #በፊት የሚታሰብ ውይይት፣ ድርድር፣ የሽግግር መንግስት ምስረታ ወዘተረፈ የፋኖን ግብ በማሰናከል የአማራን ህልውና ትግል ከአሸናፊነት ለማጨናገፍ የሚቆመር ሴራና ድራማ ነው‼️  ይህን የአማራ ህልውና መዳኛ ብቸኛ መርህ በስነ ልቦናችንና አዕምሮአችን በማስረፅ ቀጥዬ ያቀረብሁትን የማንቂያ ድዎል ተግባራዊ እናድርግ‼️ ዘመነ ካሴ እያቀፈ የሚያስተዋውቃቸው የብአዴን ልጆች እነ #አስረስ፣ #ማርሸትና ቡድናቸው በተለያየ ክፍለ አገር የሚገኙ ግብረአበሮቻቸውን አስተባብረው የፋኖ አንድነት መሰረትን ለማለት ማታለያ ድራማቸውን #በመጨረስ ላይ ይገኛሉ። ፎቶው ጸሃፊውን አይወክልም! አስረስ ማረ ዳምጤ በአስተባባሪነት የሚመራው ይሄ #የብአዴን ፋኖ ቡድን ግልፅ አላማው የፋኖ አንድነት መሰረትን በማለት #የሰላም ኮሚቴ ተብሎ በብአዴን ከተሰየመው የሰለጠኑ ካድሬዎች ስብስብ ጋር በአጠቃላይ የፋኖ አንድነት በሚመስል ስም #ለውይይትና ቀጥሎም #ለድርድር ለመሰየም አማራውን ለማታለል የሚያስችለው ሴራ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ እንደሆነ ተደርሶበታል።  ስለዚህ መላው የአማራ ህዝብና የታጠቀው ፋኖ በሙሉ ፋኖ #4ኪሎን በመቆጣጠር ስርነቀል ለውጥ ለማወጅ የሚያደርገውን የመጨረሻ ትንቅንቅ በዋዜማው ለማሰናከል የሚሸረብ #ፀረአማራ ተልኮ አስፈላጊው...