አሜሪካ - የፋሺስቱ ኦህዴዳዊው አፓርታይዳዊው ስርአት - የከረፋ ወንጀሉን መደበቂያና የህዝብን ድጋፍ መዝረፊያ ፈፅሞ አትሆንም! በወንድወሰን ተክሉ አሜሪካንን ፀረ ኢትዮጲያ የሚያደርግ ክስተትም ሆነ ፀረ አሜሪካዊ ኃይል በዛሬይቱ ኢትዮጲያ አለ? በኢትዮጲያነት ስሜት የተሰራው የእስከዛሬው ወንጀል ስቃይና መከራ ከእንግዲህ ላይቀጥል መበጣጠስ ያለበት አሁን ዛሬ ነው:: ፋሺስቱ የአቢይ መራሹ አፓርታይዳዊ ስርአት ከጀሌዎቹ ኢዜማ ጋር በመሆን አሜሪካ ኢትዮጲያን እንደሊቢያ ልታደርግ የተነሳች ቀንደኛ ጭራቅ ናት በማለት የህዝብን attention እና ድጋፍ mobilize ለማድረግ ሲንቀሳቀሱ ታይቷል:: መንጋውም - በተለይ በተለይ ምንም መማር ያልቻለው በስሜት ጋላቢ መንጋ ይህንን መንግስት መር ፕሮፖጋንዳን በማስተጋባት ፈጥኖ ሲሰለፍ ታይቷል:: የግራፊክ ምስሉ ጸሃፊውን አይወክልም! በእርግጥ አሜሪካ ኢትዮጲያን የመበትን አላማ እቅድና ፍላጎት አላትን ? ካላትስ ለምን እና እንዴት ብሎ ከመጠየቅ የተወረወረለትን አጥንት ለቀም አድርጎ እንደሚሮጥ ውሻ እነዚህ መሰሪዎች የወረወሩለትን የሴራና የፈጠራ ወሬን ብድግ አድርገው ሲያራግቡ ይታያል:: ተመልከቱ ይህ ለብልፅግና መንግስት እነ XYZ የፖለቲካ ኃይሎች ይመቱ በሽብርተኝነት ይፈረጁ ሚዲያዎች ይዘጉ እያለ ጥናት በማቅረብ የኢትዮጲያን ሀገረ ዴሞክራሲን ግንባታን በማደናቀፍ ቀንደኛ ጨፍጫፊ ፋሺስት ስርአትን እየፈጠረ ያለው የኢዜማው ስብስብ ሀገር ወዳድ መስሎ እና እራሱን ለሀገር ተቆርቋሪ አድርጎ አሜሪካንን እየጠራ ሲፎክር አይታችሁ እንኳን መረዳት አትችሉምን? የኢትዮጲያን ህልውና አደጋ ላይ የጣለው የአሜሪካ ተፅእኖ ሳይሆን የአቢይና ኢዜማ ፋሺስታዊ አምባገነንነት ሆኖ ሳለ ዛሬ እነዚሁ ስብስቦች ሀገር በአሜሪካ ጣልቃ ገብነት ልትፈር...
Welcome to TBF Blog Chanel! እንኳን በደህና መጡ ወደ TBF Blog Chanel