ከዚህ መከፋፈል ነፃ ሆነን ፊትለፊት እየወረረ : እየገደለን: ያለውን የጋራ ጠላታችንን ልናሸንፈው የምንችለው ብአንድነት ብቻ ነው:: ሻ/ቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ ሻ/ቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ በምናየው ታላቅ የፋኖ ትግል የዲያስፓራ ትልቁ ስራ ገንዘብ መስብስብ ነው:: እሱም እየቀዘቀዘ ሄዷል:: ጦርነቱን ያራዝምነው እኛው ነን:: ይህ ደግሞ ትልቁና ዋናው የጠላት ስትራተጂ ነው:: ጦርነቱን ማራዘምና ከአማራ ምድር እንዳይወጣ በማድረግ: ፋኖን በመከፋፈል አዳክመዋለሁ ! እበትነዋለሁ ! የሚል የአቢይ አህመድ ትልቁ የወቅቱ ስትራተጂ መሆኑን ተረድተናል::: በዚህም ምክንያት በአጠረ ጊዜ ሊጠናቀቅ የሚችለውን ትግል ዲያስፓራ በምቀኝነት: በቅናት: በሌለ ስልጣን ላይ በመፋተግ: በተቀጣሪነት: በጠባብ አስተሳስብ: ትግላችንን ወደኋላ በመጎተትና እንዲራዘም ብሎም እንዲዳከም በማድረግ ታሪካዊ ወንጀል እየስራ ነው:: ከዚህ መከፋፈል ነፃ ሆነን ፊትለፊት እየወረረ : እየገደለን: ያለውን የጋራ ጠላታችንን ልናሸንፈው የምንችለው በአንድነት ብቻ ነው:: አሸናፊነት ትብብርና የጋራ ስትራተጂ ይጠይቃል:: የተግባር ዲያስፓራ እንሁን:: አማራን እንደ ህዝብ ኢትዮጵያንም እንደ ሀገር ለማዳን ዋናው መሳሪያችን አንድነት ነው:: በውስጣችን ያለውን ልዩነት በመጠቀም አገራችንን ለማጥፋት: በአካባቢያችን ያለውን የሀይል አሰላለፍ ስንመለከት ፍፁም ፍፁም አደገኛ መሆኑን እንገነዘባለን:: በዲያስፓራ መጨቃጨቅና መዘላለፍ እንደ ባህልና እንደ ትልቅ የጦርነት ስትራተጂ ተደር...
Welcome to TBF Blog Chanel! እንኳን በደህና መጡ ወደ TBF Blog Chanel