Skip to main content

Posts

Showing posts from September, 2024

ከትግራዩ ትህነግ ጋር አብረን እንሰራለን፤ ከጎጃሙ አማራ፤ የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድትጅት በጎጃም እዝ ጋር ግን አብረን አንሰራም፤ የገቡበት ገብተን የማያዳግም እርምጃ እንወስድባቸዋለን ....አስረስ ማረ ዳምጤ ፤ በወንድወሰን ተክሉ

ከትግራዩ ትህነግ ጋር አብረን እንሰራለን፤ ከጎጃሙ አማራ፤ የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድትጅት በጎጃም እዝ ጋር ግን አብረን አንሰራም፤ የገቡበት ገብተን የማያዳግም እርምጃ እንወስድባቸዋለን ....አስረስ ማረ ዳምጤ በጎጃም ምድር ተሸሽጎ ከትህነግ ጋር እየተባበረ በጎጃም ምድር በተወለዱ ፋኖዎቻችን ላይ የሚዘምትን ውስጣዊን ጠላት መንጥረን ማጽዳት አለብን ‼️‼️‼️ ምስሉ ጸሃፊውን አይወክልም። በወንድወሰን ተክሉ አስረስ ማረ ዳምጤ - የአማራ ፋኖ በጎጃም ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ  የትህነጉ መሪ ዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል በቅርቡ ከአማራ ፋኖ እና ከኤርትራው መንግስት ሻእቢያ ጋር አብረን ለመስራት እንፈልጋለን ለሚለው ገለጻው በብርሃን ፍጥነት ብቅ ብሎ «ከህወሃት ጋር አብረን እንሰራለን» በማለት ምላሽ ሰጥቷል፡፡ ይህ የአስረስ ማረ ዳምጤ ምላሽ የአንድ ግለሰብ ሳይሆን የድርጅቱ፤ ማለትም የአማራ ፋኖ በጎጃም ተብሎ የሚጠራ አንድ አደገኛ ተዋጊ ቡድን ድርጅታዊ አቌም መሆኑን መላው የአማራ ህዝብና መላው የአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች በሙሉ ሊያውቁት የሚገባ እውነታ ነው፡፡ በእርግጥ የትህነጉ ዶ/ር ደብረጺዮን ከፋኖ ጋር አብሮ ለመስራት እንፈልጋለን የሚለው አሁናዊ አባባል ዝም ብሎ ከመሬት ተነስቶ የተነገረ ሳይሆን በሁለቱ ፋሺስታዊ ቡድኖች መካከል - ማለትም በዘመነ ካሴ በሚመራው የአማራ ፋኖ በጎጃም እና በዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል በሚመራው የትግራዩ ትህነግ መካከል በተካሄደ ምስጢራዊ ግንኙነትና ስምምነት  መሰረት ዛሬ ዶ/ር ደብረጺዮን በአደባባይ የተናገሩት ሀቅ መሆኑን ማወቅና መረዳት ይገባል፡፡ ባለፈው ሀምሌ ወር ውስጥ የአማራ ፋኖ በጎጃም አመራር ነን የሚሉት አስረስ ማረ እና ማርሸት ጸሀዬ ከትግራዩ ትህነግ ከዶ/ር ደብረጺዮን ጋር ምስጢራዊ ንግግርና ድርድር ማድረጋቸውን ያጋለጥ የ