Skip to main content

Posts

Showing posts from February, 2024

ሻ/ቃ ዳዊት ወ/ጊወርጊስ ስለራሳቸው የጻፉት ።ከታች ያለውን የሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዎርጊስን የግል ፅሁፍ እንመልከት ።

ሻ/ቃ ዳዊት ወ/ጊወርጊስ ስለራሳቸው የጻፉት ።  Dawit W/Giorgis የአማራ ሕዝባዊ ግንባር የውጭ ድጋፍ ሰጪ ግብረ ሀይልን እዚህ ለማድረስ ቁልፍ ሚና በመጫወቴ ደስተኝ ነኝ:: ይህንን እድል ለሰጠኝ ወደር ለሌለው ጀግና እስክንድር ነጋ ምስጋናዬን እቀርባልሁ:: ይህንን  ግዙፍ ሀላፊነት  ለመወጣት ከሚታወቀው  በላይ ያለ እረፍት ሌት  ተቀን  የሰሩትን የስራ ባልደረቦቼን እደንቃለሁ:: አመሰግናለሁ::  እኔ የስራ ሰው ነኝ:: የእወቀትም ሰው ነኝ:: ታሪካዊና ትምህርታዊ  የሆኑ አራት  መፅሀፎችም ፅፌአለሁ:: በእንግሊዝኛም በአማርኛም::አልቀረብኝም:: ቁጥራቸው በጣም ብዙ የሆኑ ምሁራዊ  ፅሁፎችን አሳትሜአለሁ::ከአውስትራሊያ አውሮፓና አሚሪካ ካናዳ የተለያዩ ሚዲያዎች ላይ  ለብዙ አመታት ቀርቤአለሁ:: ፅሁፎቼም በ CNN ሳይቀር ወጥተውልኛል::  አገልግሎቴን ግን የምመዝነው በተግባሬ ነው:: እውቀቴን  በተግባር   በማዋል የተመሰከረልኝ  ነኝ:: እውቀትና ተግባርን በማያያዝ በውትድርና ሙያ፣ በኤርትራ  አስተዳዳሪነት፣ በዲፕሎማሲ፣ በተባበሩት መንግስታትና ለተለያዪ መንግስታት በችሎታ አማካሪ ሆኜ  አገልግያለሁ::  ሰውም የሚያውቀኝ : እኔም እራሴን የማውቀው እንደ  ተግባር  ሰው ነው::እውቀቴን ለተግባሬ መሳሪያ እድርጌ የኖርኩ ከጦርሜዳ እስክ ህይወት  ማዳን ታላላቅ  ዘመቻዎች (humanitarian operations) በእውቀትና በኩራት ያገለግልኩ ነኝ:: ለኢትዮጵያ  አንድነትና ለአገሬ ህዝብ ፍቅሬን በደሜ አስመክሬአለሁ:: በውጊያ ቆስያለሁ:: አድር ባይ ሆኜ  በደርግ የፖለቲካ ሥርዓት መቆየት ስችል  ከሥርዓቱ መራቅ ብቻ ሳይሆን ወጥቼ  ስርአቱን ለማስለወጥ  ረዥምና ውስብስብ ትግል ውስጥ የነበርኩ ነኝ:: ለዚሁ ትግል በሱዳንና በኬንያ ጠረፎች አድርገን  አንዳንድ