Skip to main content

Posts

Showing posts from September, 2021

"ከእኛ ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህ?" በዴቭ ዳዊት

"ከእኛ ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህ?" ይህ ምስል የዴቭ ዳዊት ስራ ነው! June 6, 2020 የተፃፈ ከሰሞኑ የአማራ ህዝብ ትግል ከሁለት አመት በፊት በይፋ ተጠልፎ አማራዊ ብሔርተኝነትን ለማዳከምና ለማጥፋት ሲባል ብአዴናዊ ብሔርተኝነት መፈጠሩን፤ እንዲሁም ብአዴናዊው ብሔርተኝነት መገለጫ ባህርይው ምን እንደሚመስል በዝርዝር ተመልክተን ነበር። ከዚያም ጎን ለጎን በአማራ ህዝብ ትግል ውስጥ በአማራዊ ብሔርተኝነት እና በብአዴናዊ ብሔርተኝነት መካከል ግልፅ መስመር ባለመሰመሩ ምክንያት ከፍተኛ የሆነ የጎራ መደበላለቅ መፈጠሩን፥ይህንንም አጋጣሚ ተጠቅሞ በጎጣዊ ውግንና የገነገነው ብአዴናዊው ብሔርተኝነት፥ አማራዊ ብሔርተኝነቱን ለማደብዘዝና ለማፈን ሰፊ ዕድል እንደተፈጠረለት ተመልክተናል። እነሆ ዛሬ ጊዜ እንደፈቀደ የአማራ ህዝብ ብቸኛ መዳኛ የሆነው ግን በብዙ አቅጣጫ ጦርነት ተከፍቶበት ያለው አማራዊ ብሔርተኝነት ውስጣዊ ጠላቱ ስለሆነው ብአዴናዊ ብሔርተኝነት እንዲሁም ብአዴናዊው ብሔርተኝነት በአማራዊው ብሔርተኝነት ላይ የከፈተበትን የጦርነት ስልትና ይዘት እንፈትሻለን። መልካም ንባብ። የአማራ ሕዝብ የዘመናት ትግል የሆነው አማራዊ ብሔርተኝነት፥ እንደ አማራ አቆጣጠር በ1980ዎቹ መጨረሻ የመጀመሪያው የመጠለፍ አደጋ ሲገጥመው የተፈፀመው ደባ ቢኖር #የመሪ_አታጋይ_ድርጅቱን_ህልውና_ማሳጣት /የመዐሕድን/ ነበር። ሁለተኛው ዙር ህዝባዊ ተጋድሎ እየሰፋና ፍሬ ወደ ማፍራቱ ደረጃ ሲደርስ ደግሞ ትግሉ ገና #ሙሉ_ዕድገቱን_የጨረሰ_መሪ_ድርጅት ከመውለዱ በፊት፥ በህዝባዊ ማዕበሉ ከመበላት ለማምለጥ ሲል ብአዴን የአማራን ትግል ጠለፈው።  አማራዊው ብሔርተኝነት የራሱን ሰንደቅ የሚሸከም/Standard bearer/ መሪ ድርጅት ሳይፈጥር የአማራ ሕዝብ ትግል በብአዴን መጠለፉ...