እኔ እስከማውቀው ድረስ፤ የምእራብ አገሮች ለጥቁር አፍሪካ ሕዝቦች ሰላም፤ እርጋታ፤ ክብር፤ ነጻነት፤ ፍትሃዊና ዘላቂ ልማት ቆመው አያውቁም። በተለይ፤ ለመላው የጥቁር ሕዝብ ክብርና ነጻነት ተምሳሌ የሆነችውን የኢትዮጵያን ግዛታዊ አንድነት፤ ሉዐላዊነት፤ የስብጥር ሕዝቧን አብሮነት፤ ሰላም፤ እርጋታ፤ ፍትሃዊ፤ ዘላቂ ብልጽግና ደግፈው አያውቁም። የኢትዮጵያ ጠንካራና አገር ወዳድ መንግሥት ለነሱ ብሄራዊ ጥቅም ስጋት ፈጣሪ ነው። ይኼን ሃቅ በአጼ ኃይለ ሥላሴና በደርግ መንግሥት ወቅትም አይተናል። ህወሓት/ትህነግ ጆ ባይደን በተመረጡበት ማግስት ክህደት፤ እልቂት ከፈጸመበትና ጦርነት ከጀመረበት አንድ ሳምንት በኋላ ለዚህ አጥፊ፤ ከሃዲና የውጭ ኃይሎች አገልጋይና አሽከር የሆነ ቡድን ግዙፍ ድጋፍ ይሰጡት የነበሩት የምእራብ “ዲሞክራሲ” ነን የሚሉ ባለሥልጥናት ሴራቸውን በምስጢር ቀየሱ። ኢላማቸው ሁለት አስኳል ጉዳዮች ነበሩ፤ አንድ የጠቅላይ ሚንስትር ዶር ዐብይ አሕመድን መንግሥት መገልበጥና ባለሥልጣናትን ልክ እንደ ሰርቦች ለፍርድ ማቅረብ፤ ሁለት፤ ኢትዮጵያ ልክ እንደ ዩጎስላቭያና እንደ ሶማልያ እንድትበታተን ማድረግ። እኛ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን በተደጋጋሚ ለምእራብ አገሮች ባለሥልጣናት፤ በተለይ ለአሜሪካ ምክር ቤት አባላት በተደጋጋሚ እባካችሁ ሚዛናዊ አቋም ያዙ፤ በመሬት ላይ ያለውን ሃቅ አንጸባርቁ፤ የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል የትግራይ ሕዝብ ጠላት አይደለም፤ የብሄር ማጥፋት ዘመቻ አያካሂድም፤ የኢትዮጵያ መንግሥት 70 በመቶ የሚሆነውን ሰብአዊ እርዳታ እየሰጠ ነው ወዘተ እያልን ብንጮህም ሰሚ አላገኘነም ነበር። ብዙዎቻችን ግራ ተጋብተን ነበር ለማለት እችላለሁ። ለምን ጀሩቸውን አይከፍቱም፤ አይናቸውን አይገልጡም? እንል ነበር፡ ከጀርባ በረቀቀ ምስ...
Welcome to TBF Blog Chanel! እንኳን በደህና መጡ ወደ TBF Blog Chanel