Skip to main content

Posts

የአማራ ህዝብ ትግል ዳራ እና የትግል አቅጣጫዎች የመነሻ ሃሳብ ሰነድ ፤ በመስከረም አበራ

ይዘት መግቢያ የሰነዱ አስፈላጊነት የአማራ ህዝብ በኢትዮጵያ አብዮተኞች ዕይታ- ከትናንት እስከ ዛሬ ኢትዮጵያዊ ብሄርተኝት፣የዘውግ ብሄርተኝነት እና የአማራ ህዝብ መስተጋብር የዘውግ ፖለቲካ ከ1983-2010ዓም በአማራ ህዝብ ላይ ያደረሰው ጉዳትና የጋረጠው ፈተና በድህረ-ህወሃት የአማራ ህዝብ የገጠሙት ፈተናዎች የአማራን ህዝብ ጥያቄ በኢትዮጵያዊ ብሄርተኛ ፓርቲዎች ማዕቀፍ ውስጥ መመለስ ያልተቻለው ለምንድን ነው? የአማራ ንቅናቄ አስፈላጊነት እና ተፈጥሮ የአማራ ንቅናቄ ትግል ውስንነቶች የአማራ ንቅናቄ ሃይሎች በትግል ጉዟቸው ከግንዛቤ ሊያስቧቸው የሚገቧቸው አንኳር ጉዳዮች የአማራ ህዝብ ያለበት ወቅታዊ ሁኔታ የአማራ ህዝብ ዋነኛ ጥያቄዎችና የመደራደሪያ ነጥቦች በብሄራዊ የምክክር መድረኩ የአማራ ህዝብ በማን ይወከል? በምክክር መድረኩ የአማራ ተደራዳሪዎች ሊገጥማቸው የሚችሉ ተግዳሮቶችና የመፍትሄ አቅጣጫዎች ብሄራዊ ምክክር ለአማራ ህዝብ ሊያመጣው የሚችለው ፋይዳ የአማራ ንቅናቄ የወደፊት ትግል እንዴት መቃኘት አለበት? መደምደሚያ ምስሉ ጸሃፌውን አይወክልም 1. መግቢያ የአማራ ህዝብ1 ከኢትዮጵያ የሃገረ-መንግስትነት ታሪክ ጋር ጥብቅ የስነ-ልቦና ቁርኝት ያለው ህዝብ ነው፡፡በመሆኑም ለምዕተ-ዓመታት ከአማራ ማንነቱ ይልቅ በኢትዮጵያዊ ማንነቱ ላይ ትኩረት ያደረገ የፖለቲካ ተሳትፎ ሲያራምድ የኖረ ህዝብ ነው፡፡ይህ ማለት ግን ኢትዮጵያ ባለፈችበት የታሪክ ምዕራፎች ሁሉ ልዩ ተጠቃሚነት ያለው ህዝብ ነበር ማለት አይደለም፡፡ይልቅስ በሃገሪቱ የተነሱ አገዛዞች በሌሎች የሃገሪቱ ህዝቦች ላይ ያደርሱት የነበሩት በደልና ጫና ሁሉ በአማራ ህዝብ ላይም ደርሷል፡፡ በመሆኑም ሌሎቹ የሃገሪቱ ህዝቦችና የአካባቢ መሪዎች የተበደሉ ሲመስላቸው በነገስታቱ ላይ ያካሂዱ የነበረው አመፅ አሁን የአማራ